1ከዚያ ከዮሴፍ ልጅ ለምናሴ ነገድ የአፌር ወንድ ልጅ የገለአድ ወንድ ልጅ የማኪር ወንድ ልጅ የምናሴ ወንድ ልጅ የሰለጵዓድ ሴት ልጆች ወደ ሙሴ መጡ የሰለዓድ ሴት ልጆች ስሞች እነዚህ ነበሩ፡፡ ማህላህ፣ ኑዓ፣ ዔግላ፣ ሚልካና ቲርጳ፡፡
2እነርሱም በሙሴ፣ በካህኑ አልዓዛር፣ በመሪዋች፣ እና በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ በመላው ማህበረሰቡ ፊት ቆሙ፡፡ እንዲህም አሉ፣
3“አባታችን በምድረበዳው ሞተ፡፡ እርሱ በቆሬ አመጽ በያህዌ ፊት አምጸው በአንድነት ከተነሱት መሀል አልነበረም፡፡ የሞተው በራሱ ኃጢአት ነበር፣ አባታችን የሞተው በራሱ ኃጢአት ምክንያት ነበር፡፡
4ስለምን ወንድ ልጅ ስለሌለው የአባታችን ስም ከጎሳው አባላት ተለይቶ ይጠፋል? በአባታችን ቤተዘመዶች መሀል መሬት ስጠን፡፡”
5ሙሴ ጉዳያቸውን ያህዌ ፊት አቀረበ፡፡
6ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣
7”የሰለጰዓድ ሴት ልጆች የተናገሩት ትክክል ነው፡፡ በአባታቸው ዘመዶች መሃል በእርግጥ ርስት አድርገህ መሬት ስጣቸው፣ ደግሞም የአባታቸው ርስት ወደ እነርሱ መተላፉን አረጋግጥ፡፡
8ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‘አንድ ሰው ወንድ ልጅ ሳይኖው ቢሞት፣ ርስቱ ወደ ሴት ልጁ እንዲተላፍ አድርጉ፡፡
9ሴት ልጅ ባይኖረው፣ ርስቱን ለወንድሞቹ ስጡ፡፡
10ወንድሞች ባይኖት፣ ርስቱን ለአባቱ ወንድሞች ስጡ፡፡
11አባቱ ወንድሞች ባይኖሩት ርስቱን በጎሳው ውስጥ ለቅርብ ዘመዱ ስጡ፣ ያም ሰው ይውሰደው፡፡ ይህም ያህዌ እንዳዘዘኝ፣ ለእስራኤል ህዝብ በአዋጅ የፀና ህግ ይሆናል፡፡’”
12“ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “ወደ ዓባሪም ተራሮች ወጥተህ ለእስራኤል ህዝብ የሰጠሁትን ምድር ተመልከት፡፡
13ከተመለከትካት በኋላ፣ አንተም ደግሞ ወደ ሰዎችህ እንደ ወንድምህ አሮን ሁሉ ትሰበስባለህ፡፡
14ይህ ይሆናል፤ ምክንያቱም በጺን ምድረበዳ እናንተ ሁለታችሁ በትእዛዛቶቼ ላይ አምጻችኋል፡፡ በዚያ፣ ውሃው ከአለቱ ሲፈስስ በቁጣህ ምክንያት በመላው ማህበረሰብ ዐይኖች ፊት እኔን በቅድስና ማክበር አልቻልክም፡፡” ይህ በጺን ምድረበዳ በቃዴስ የሚገኝ የመሪባ ውሃ ነው፡፡
15ከዚያ ሙሴ ለያህዌ እንዲህ አለ፣
16“የሰዎች ሁሉ መንፈስ አምላክ ያህዌ ሆይ፣ በዚህ ማህበረሰብ ላይ መሪ የሚሆን ሰው ሹም፣
17በፊታቸው የሚወጣና የሚገባ ሰው፣ እየመራ የሚያስወጣቸውና የሚያስገባቸው፣ ህዝብህ እረኛ እንደሌላቸው በጎች እንዳይሆን ሰው ሹምለት፡፡”
18ያህዌ ሙሴን፣ “የእኔ መንፈስ የሚኖርበትን፣ የነዌን ልጅ ኢያሱን ውሰድና እጆችህን በእርሱ ላይ ጫን፡፡
19በካህኑ አልዓዛር ፊትና በመላው ማህበረሰብ ፊት አቁመህ እንዲመራቸው በፊታቸው ሹመው፡፡
20ከአንተ ስልጣን በእርሱ ላይ አድርግ፣ ስለዚህም መላው የእስራኤል ማህበረሰብ እርሱን ይታዘዙታል፡፡
21እርሱም በኡሪም በመጠየቅ ፍቃዴን ለማወቅ በካህኑ አልዓዛር ፊት ይሄዳል፡፡ ህዝቡ፣ እርሱና ከእርሱ ጋር መላው የእስራኤል ሰዎች፣ መላውም ማህበረሰብ የሚወጣውና የሚገባው በእርሱ ትዕዛዝ ይሆናል፡፡
22ስለዚህም ሙሴ ያህዌ እርሱን እንዳዘዘው አደረገ፡፡ ኢያሱን ወስዶ በካህኑ አልዓዛርና በመላው ማህበር ፊት አቆመው፡፡
23ያህዌ እንዲያደርግ እንዳዘዘው ሁሉ እጆቹን በላዩ ጫነና እንዲመራ ሾመው፡፡