1የእስራአል ህዝብ ከከተማዋ ከዮርዳኖስ ወንዝ ሌላ ዳርቻ ኢያሪኮ አጠገብ ወደሚገኘው የሞአብ ሜዳ ደርሰው እስኪሰፍሩ ደረስ ተጓዙ፡፡
2የሴፎር ልጅ ባላቅ እስራኤል በአሞራዊያን ላይ ያደረገውን ሁሉ አየ፡፡
3ሞአብ የእስራኤልን ህዝብ በጣም ፈርቶ ነበር ምክንያቱም ብዙ ነበሩ፣ እናም ሞአብ በእስራኤል ህዝብ ተሸብሮ ነበር፡፡
4የሞብ ንጉስ ለምድያም ሽማግሌዎች፣ “ይህ ብዙ ህዝብ፣ በሬ በሜዳ ላይ ያለን ሳር በልቶ እንደሚጨርስ በዙሪያችን ያለውን ሁሉ በልቶ ይጨርሳል፡፡” አለ፡፡ በዚያን ጊዜ የሴፎር ልጅ ባላቅ የሞዓብ ንጉስ ነበር፡፡
5እርሱም በአገሩና በወገኖቹ መሀል በኤፍራጦስ ወንዝ አጠገብ በፋቱራ ወደተቀመጠው የቢያር ልጅ በልዓም መልዕክተኞችን ላከ፡፡ አስጠርቶትም እንዲህ አለው፣ “እነሆ፣ ከግብጽ አንድ ህዝብ ወደዚህ መጥቷል፡፡ የምድርን ፊት ሸፍነዋል፣ ደግሞም እዚሁ አጠገቤ ናቸው፡፡
6ስለዚህ አሁን መጥተህ ይህን ህዝብ ርገምልኝ፣ ምክንያቱም ከእኔ አቅም በላይ ናቸው፡፡ ምናልባት ከረገምክልኝ በኋላ እነርሱን ለማጥቃትና ከምድሪቱ ለማባረር እችል ይሆናል፡፡ የባረከው ሁሉ እንደሚባረክ አውቃለሁ፣ የረገምከው ሁሉ እንደሚረገም አውቃለሁ፡፡”
7ስለዚህ የሞአብ ሽማግሌዎችና የምድያም ሽማግሌዎች የምዋርቱን ዋጋ ይዘው ሄዱ፡፡ ወደ በለዓም መጥተው የባላቅን ቃል ነገሩት፡፡
8በለዓምም እንዲህ አላቸው፣ “ዛሬ ምሽት እዚህ እደሩ፡፡ ያህዌ የሚለኝን አሳውቃችኋለሁ፡፡” ስለዚህም የሞብ መሪዎች ያን ምሽት ከበለዓም ዘንድ ተቀመጡ፡፡
9እግዚአብሔር ወደ በለዓም መጥቶ እንዲህ አለው፣ “ወደ አንተ የመጡት እነዚህ ሰዎች እነማን ናቸው”
10በለዓም ለእግዚአብሔር እንዲህ ሲል መለሰለት፣ “የሞአብ ንጉስ የሴፎር ልጅ ባላቅ፣ እነርሱን ወደ እኔ ልኳቸዋል፡፡ እንዲህም አለ፣
11‘እነሆ፣ ከግብጽ የመጡ ሰዎች የምድሬን ገጽ ሸፍነዋል፡፡ አሁን መጥተህ እነርሱን ርገምልኝ፡፡ ይህ ከሆነ ምናልባት እነርሱን መዋጋትና ማባረር እችል ይሆናል፡፡”
12እግዚአብሔር ለበለዓም እንዲህ መለሰለት፣ “ከእነዚህ ሰዎች ጋር መሄድ የለብህም፡፡ የእስራአልን ህዝብ መርገም የለብህም ምክንያቱም እነርሱ የተባረኩ ናቸው፡፡”
13በለዓም በጠዋት ተነስቶ ለባላቅ መሪዎች እንዲህ አላቸው፣ “ወደ ምድራችሁ ተመልሳችሁ ሂዱ ምክንያቱም ያህዌ ከእናንተ ጋር እሄድ ዘንድ አልፈቀደልኝም፡፡
14ስለዚህም የሞብ መሪዎች ተመልሰው ወደ ባላቅ ሂዱ፡፡ እንደህም አሉት፣ “በለዓም ከእኛ ጋር ለመምጣት አልፈቀደም፡፡”
15ባላቅ እንደገና ከመጀመሪያዎቹ መልዕክተኞች የከበሩ ብዙ መሪዎችን ላከ፡፡
16እነርሱም ወደ በለዓም መጥተው እንዲህ አሉት፣ “የሴፎር ልጅ ባላቅ እንዲህ ብሏል፣ ‘እባክህ ወደ እኔ ለመምጣት አንዳች ነገር አያግድህ፣
17ምክንያቱም እጅግ ከፍ ያለ ክፍያ እከፍልሃለሁ፣ ታላቅ ክብርም እሰጥሃለሁ፣ ደግሞም እንዳደርገው የምትነግረኝን ሁሉ አደርጋሁ፡፡ ስለዚህ እባክህ መጥተህ ይህን ህዝብ ርገምልኝ”
18በለዓለም ለባላቅ ሰዎች እንዲህ ሲል መለሰላቸው፣ “ባላቅ ብርና ወርቅ የሞላበትን ቤተ መንግስቱን ቢሰጠኝ እንኳን ከአምላኬ፣ ከያህዌ ቃል አልፌ መሄድ አልችልም፣ ደግሞም እርሱ ከነገረኝ አሳንሼ ወይም ጨምሬ አላደርግም፡፡
19ስለዚህ አሁን፣ እባካችሁ ያህዌ የሚለኝን ተጨማሪ ነገር አውቅ ዘንድ ዛሬ ምሽትም ደግሞ በዚህ እደሩ፡፡”
20እግዚአብሔር በምሽት ወደ በለዓም መጥቶ እንዲህ አለው፣ “እነዚህ ሰዎች ወደ አንተ እስከ መጡ ድረስ ተነስተህ ከእነርሱ ጋር ሂድ፡፡ ነገር ግን እንድታደርገው የምነግርህን ብቻ አድርግ፡፡”
21በለዓም በጠዋት ተነስቶ አህያውን ጫንና ከሞአብ መሪዎች ጋር ሄደ፡፡
22ነገር ግን በመሄዱ፣ የእግዚአብሔር ቁጣ ነደደ፡፡ የያህዌ መልአክ፣ በአህያው ላይ ተቀምጦ የሚሄደውን በለዓምን ሊቃወመው በመንገድ ላይ ቆመ፡፡ የበለዓም ሁለቱ አገልጋዮቹም አብረውት ነበሩ፡፡
23አህያዋ የያህዌን መልአክ የተመዘዘ ሰይፉን ይዞ በመንገድ ላይ ቆሞ አየችው፡፡ አህያዋ ከመንገድ ዘወር ብላ ወደ ሜዳው ሄደች፡፡ በለዓለም አህያይቱን ወደ መንገድ እንድትለስ መታት፡፡
24የያህዌ መልአክ በመንገዱ ጠባብ መተላፊያ ላይ በወይን እርሻው መሀል፣ በስተቀኙና በስተግራው ግድግዳ ባለበት ስፍራ ቆመ፡፡
25አህያይቶ የያህዌን መልአክ አየች፡፡ ወደ ግድግዳው ተጠግታ የበለዓምን እግር አጣበቀችው፡፡ በለዓም እንደገና አህያይቱን መታት፡፡
26የያህዌ መልአክ እንደ ገና ራቅ ብሎ ሄዶ ወደ የትኛውም አቅጣጫ መዞሪያ በሌለበት ሌላ ጠባብ መተላፊያ ስፍራ ቆመ፡፡
27አህያይቱ የያህዌን መልአክ አይታ ከበለዓም በታች ተኛች፡፡ የበለዓም ቁጣ ነደደ፣ በበትሩም አህያይቱን መታት፡፡
28ያህዌ የአህያይቱን አፍ ስለከፈተ መናገር ቻለች፡፡ በለዓምን እንዲህ አለችው፣ “እነዚህን ሶስት ጊዜያት እንድትመታኝ የሚያደርግ ምን ነገር አደረግሁብህ”
29በለዓም አህያይቱን፣ “በእኔ ላይ የማይረባ ድርጊት ስለፈጸምሽ ነው፡፡ በእጄ ላይ ሰይፍ ቢኖር እወድ ነበር፡፡ በእጄ ላይ ሰይፍ ቢኖር ኖሮ፣ ይህን ጊዜ ገድዬሽ ነበር” አላት፡፡
30አህያይቱ በለዓምን እንዲህ አለችው፣ “እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ስትቀመጥብኝ የኖርክብኝ አህያህ አይደለሁምን? ከዚህ በፊት እንዲህ ያለ ነገር በአንተ ላይ የማድረግ ልማድ ነበረኝን?” በለዓም “እይ” አለ፡፡
31ከዚያ ያህዌ የበለዓምን ዐይኖች ከፈተ፣ እናም የያህዌ መልአክ በእጁ ሰይፉን ይዞ በመንገዱ ላይ ቆሞ አየ፡፡ በለዓም ዝቅ ብሎ በግምባሩ ተደፋ፡፡
32የእግዚአብሔር መልአክ እንዲህ አለው፣ “አህያህን ለምን በእዚህ ሶስት ጊዜያት መታሀት የምቃወምህ ሆኜ መጥቻለሁ ምክንያቱም ድርጊቶችህ በፊቴ መጥፎዎች ነበሩ፡፡
33አህያይቱ አይታኝ በእነዚህ ሶስት ጊዜያት ከእኔ ዞር አለች፡፡ እርሷ ዞር ባትልልኝ ኖሮ፣ በእርግጥ አንተን እገድልህና የእርሷን ነፍስ እተው ነበር፡፡”
34በለዓም ለያህዌ መልአክ እንዲህ አለ፣ “እኔ በድያለሁ፡፡ እኔን ተቃውመህ በፊቴ ቆመህ እንደነበር አላወቅሁም፡፡ አሁን እንግዲህ፣ ይህ ጉዞ አንተን ደስ ካላሰኘ፣ ወደመጣሁበት እመለሳለሁ፡፡”
35የያህዌ መልአክ ግን በለዓምን እንዲህ አለው፣ “ከሰዎቹ ጋር ጉዞህን ቀጥል፡፡ ነገር ግን እኔ የምነግርህን ብቻ መናገር አለብህ፡፡” ስለዚህም በለዓም ከባላቅ መሪዎች ጋር ሄደ፡፡
36ባላቅ የበለዓምን መምጣት ሲሰማ፣ ሞአብ ውስጥ ወዳለችው በድንበር ላይ ወደምትገኘው አርኖን ከተማ ሊቀበለው ወጣ፡፡
37ባላቅ በለዓምን እዲህ አለው፣ “እንዲጠሩህ ሰዎችን ወደ አንተ አልላኩም ነበርን? ለምን ወደ እኔ አልመጣህም? እኔ ላከብርህ አልችልምን?”
38ከዚያም በለዓም ለባላቅ መለሰለት፣ “በእርግጥ ወደ አንተ መጥቻለሁ፡፤ አሁን አንዳች ነገር ለመናገር እኔ አንዳች ሀይል አለኝን? መናገር የምችለው እግዚአብሔር በአፌ ላይ ያስቀመጠውን ቃል ብቻ ነው፡፡”
39በለዓም ከባላቅ ጋር ሄደ፣ እነርሱም ወደ ቂርያት ሐጾት ደረሱ፡፡
40ከዚያ ባላቅ በሬዎችንና በጎችን ሰዋ፣ ለበለዓምና ከእርሱ ጋር ለነበሩ መሪዎችም ሰጣቸው፡፡
41ማለዳ፣ ባላቅ በለዓምን ወደ ካሞት በኣል ይዞት ሄደ፡፡ በለዓም ከዚያ ሆኖ ማየት የሚችለው በሰፈሮቻቸው ካሉት እስኤላዊያን ጥቂቶቹን ብቻ ነበር፡፡