መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘኁልቁ 21

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በኔጌብ የሚኖረው ከነዓናዊው የዓረድ ንጉስ እስራኤል ወደ አታሪም እየመጣ በመንገድ ላይ መሆኑን ሲሰማ፣ ከእስራኤል ጋር ተዋግቶ አንዳንዶቹን በምርኮ ወሰደ፡፡
2እስራኤል ለያህዌ እንዲህ ብሎ ማለ፣ “በእነዚህ ህዝቦች ላይ ድል ብትሰጠን፣ ከዚያም ከተማቸውን ሙሉ ለሙሉ እናጠፋለን፡፡”
3ያህዌ የእስራኤልን ድምጽ ሰምቶ በከነዓናዊያን ላይ ድልን ሰጣቸው፡፡ ሙሉ ለሙሉ እነርሱንና ከተማቸውን አጠፉ፡፡ ያ ስፍራ ሖርማ ተብሎ ተጠራ፡፡
4ከሖር ተራራ ተነስተው ኤዶም ምድር ዙሪያ ለመድረስ በቀይ ባህር መንገድ ተጓዙ፤ ህዝቡ በመንገድ ሳለ እጅግ ተስፋ ቆረጡ፡፡
5በእግዚአብሔርና በሙሴ ላይ እንዲህ ሲሉ አጉረመረሙ፡፡ “በበረሃ እንሞት ዘንድ ለምን ከግብጽ አወጣችሁን በዚህ ዳቦ የለም፣ አንዳች ውሃ የለም፣ ደግሞም ይህን የማይረባ ምግብ ጠልተነዋል፡፡”
6ከዚያ ያህዌ በሰዎቹ መካከል መርዛም እባቦችን ሰደደ፡፡ እባቦቹ ሰዎችን ነደፉ፤ ብዙ ሰዎችም ሞቱ፡፡
7ሰዎች ወደ ሙሴ መጥተው እንዲህ አሉ፣ “እኛ በድለናል ምክንያቱም በያህዌና በአንተ ላይ በተቃውሞ ተናግረናል፡፡ እባቦቹን ከእኛ እንዲያርቅ ወደ ያህዌ ጸልይልን፡፡” ስለዚህም ሙሴ ለህዝቡ ጸለየ፡፡
8ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “እባብ አብጅና በምሰሶ ላይ አንጠለጠለው፡፡ እንዲህ ይሆናል፣ የተነደፈ ሁሉ ያንን ከተመለከተ ይድናል፡፡”
9ስለዚህም ሙሴ የናስ እባብ አበጅቶ በምሰሶ ላይ አንጠለጠለው፡፡ እባብ ማናቸውንም ሰው በነከሰ ጊዜ፣ ሰውየው ወደ ናሱ እባብ ከተመለከተ ይድናል፡፡
10ከዚያ የእስራኤል ሰዎች ተጉዘው በአቦት ሰፈሩ፡፡
11ከአቦት ተጉዘው በስተምስራቅ በሞአብ አንጻር በዒዮዓባሪም በምድረ በዳ ሰፈሩ፡፡
12ከዚያ ተጉዘው በዘሬድ ሸለቆ ሰፈሩ፡፡
13ከዚያ ተጉዘው እስከ አሞራዊያን ድንበር በሚዘልቀው በምድረበዳ ባለው በአሮን ወንዝ ሌላኛው ዳርቻ ሰፈሩ፡፡ የአርኖን ወንዝ በሞዐብና አሞራዊያን መሀል የሞአብን ወሰን ያበጃል፡፡
14በያህዌ የጦርነት መጽሐፍ ጥቅልል፣ በሱፋ ውስጥ የሚገኘው ዋሄብ እና የአርኖን ሸለቆዎች፣
15ወደ ዔር ከተማና ወደ ሞአብ ዳርቻ የሚወስዱ የሸለቆዎች ቁልቁለት” ተብሎ የተፃፈው ስለዚህ ነው፡፡
16ከዚያ ተነስተው ወደ ብኤር ተጓዙ፣ ይህም ስፍራ የውሃ ጉድጓድ የሚገኝበትና ያህዌ ሙሴን፡ - “ውሃ እሰጣቸው ዘንድ ሰዎቹን በአንድነት ሰብስባቸው” ብሎ የተናገረበት ነው፡፡
17ከዚያ እስራኤል ይህን መዝሙር ዘመረ፡፡ “አንተ ምንጭ ሆይ ፍለቅ፡፡ ስለዚህ እናንተም ዘምሩ፡፡
18መሪዎቻችን የቆፈሩት ጉድጓድ፣ የተከበሩ የህዝብ አለቆች በበትረ መንግስታቸውና በበትሮቻቸው የማሱት ጉድጓድ፡፡” ከዚያ ከምድረበዳው ተነስተው ወደ መቴና ተጓዙ፡፡
19ከመቴና ተነስተው ወደ ነሃሊኤል፣ ከነሃሊኤል ወደ ባሞት እና ከባሞት በሞአብ ምድር ወደሚገኘው ሸለቆ ተጓዙ፡፡
20በፈስጋ ተራራ ጫፍ ሆኖ ምድረበዳው ቁልቁል የሚታይበት ይህ ስፍራ ነው፡፡
21ከዚያ እስራኤል ወደ አሞራዊያን ንጉስ ወደ ሴዎን እንዲህ ብለው መልእክተኞችን ላኩ፣
22”በምድርህ እንለፍ፡፡ ወደ እርሻዎች ወይም ወደ ወይን አትክልቶች አንገባም፡፡ ከጉድጓዶችህ ውሃ አንጠጣም፡፡ ድንበርህን እስክናልፍ ድረስ በንጉሱ አውራ መንገድ እንጓዛለን፡፡”
23ንጉስ ሴዎን ግን እስራኤልን በድንበሩ እንዲያልፉ አልፈቀደም፡፡ ይልቁንም፣ ሴዎን ወታደሮቹን አሰባስቦ በምድረ በዳ እስራኤልን ለመውጋት ወጣ፡፡
24እስራኤል የሴዎንን ጦር በሰይፍ ወግቶ ከአርኖን እስከ ያቦቅ ወንዝና እስከ አሞን ሰዎች ወሰን ድረስ ምድሩን ወሰደ፡፡ የአሞን ሰዎች ድንበር ግን የተመሸገ ነበር፡፡
25እስራኤል የአሞራዊያንን ከተሞች ሁሉ፣ ሐስቦንንና መንደሮቹን ጭምር ይዞ በእነዚያ ውስጥ ተቀመጠ፡፡
26ሐስቦን ከሞአብ የቀድሞ ንጉስ ጋር የተዋጋው የአሞራዊያን ንጉስ የሴዎን ከተማ ነበረች፡፡ ሴዎን እስከ አርኖን ወንዝ ድረስ ያለውን ምድሩን ሁሉ ወሰደበት፡
27በምሳሌያዊ ንግግር የተናገሩ፣ “ወደ ሐሴቦን ኑ፡፡ የሴዎን ከተማ እንደ ገና ትገንባና ዳግም ትታነጽ፡፡
28እሳት ከሐሴቦን ተንቦገቦገ፣ ነበልባል ከሴዎን ከተማ የሞአብን ዔር አጠፉ፣ ደግሞም የአርን ተራሮች ባለቤቶችን በላ፡፡
29ሞአብ ዋይታ ሆነብህ! የከሞስ ህዝብ እናንተ ጠፋችሁ፡፡ ለአሞራውያን ንጉስ ለሴዎን ወንዶች ልጆቹን ለሽሽት ሴቶች ልጆቹን ለምርኮ አሳልፎ ሰጥቷል፡፡
30እኛ ግን ሴዎንን አሸንፈናል፡፡ ሐስቦን እስከ ዴናን ድረስ ወድማለች፡፡ ወደ ሜድባ እስከምታደርሰው ኖፋ ድረስ ሁሉንም አሸንፈናቸዋል፡፡”
31ስለዚህ እስራኤል በአሞራዊያን ምድር መኖር ጀመረ፡፡
32ከዚያ ሙሴ ሰዎችን ምድሪቱን እንደያዙ ወደ ኢያዜር ላከ፡፡ እነርሱ መንደሮቿን ማረኩ በዚያ የነበሩትንም አሞራዊያን አባረሩ፡፡
33ከዚያ ወደ ባሳን በሚስደው መንገድ ዞረው ሄዱ፡፡ የባሳን ንጉስ ዐግ በእነርሱ ላይ ዘመተ፣ እርሱና ሰራዊቱ ሁሉ በኤድራይ ሊዋጓቸው ወጡ፡፡
34በዚያን ጊዜ ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “እርሱን አትፈራው፣ ምክንያቱም እኔ በእርሱ፣ በሰራዊቱና በምድሩ ላይ ሁሉ ላይ ድል ሰጥቼሃለሁ፡፡ በሔስቦን እንደነበረው በአሞራዊያን ንጉስ በሴዎን ላይ እንዳደረከው በእርሱ ላይ አድርግበት፡፡”
35ስለዚህም እርሱን፣ ወንዶች ልጆቹን እና መላውን ሰራዊቱን አንድም ሰው በህይወት እስከ ማይተርፍለት ድረስ ፈጇቸው፡፡ ከዚያም ምድሩን ወረሱ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።