መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘኁልቁ 20

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1የእስራኤል ሰዎች፣ መላው ማህበረሰብ በመጀመሪያው ወር ወደ ሲና ምድረ በዳ ሄደው በቃዴስ ሰፈሩ፡፡ማርያም በዚያ ሞታ ተቀበረች፡፡
2ማህበረሰቡ ውሃ ተጠማ፣ ስለዚህ በሙሴና በአሮን ላይ አምጸው ተሰበሰቡ፡፡
3ህዝቡ በሙሴ ላይ አጉረመረሙ፡፡ እንዲህም አሉ፣ “ወገኖቻችን እስራኤላውያን በያህዌ ፊት በሞቱበት ጊዜ እኛም ብንሞት ኖሮ ይሻል ነበር!
4እዚህ እንሞት ዘንድ የያህዌን ማህበረሰብ፣ እኛንና ከብቶቻችንን ለምን ወደዚህ ምድረበዳ አመጣችሁን?
5ወደዚህ አስፈሪ ስፍራ ልታመጡን ለምን ከግብጽ እንድንወጣ አደረጋችሁን? እዚህ፤ እህል፣ በለስ፣ ወይም ወይም ሮማን የለም፡፡ የሚጠጣም ውሃ የለም፡፡”
6ስለዚህ ሙሴና አሮን ከጉባኤው ፊት ወጥተው ሄዱ፡፡ ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ ሄደው በግምባራቸው ተደፉ፡፡ ከዚያ የያህዌ አንጸባራቂ ክብር ታያቸው፡፡
7ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
8“በትርህን ውሰድና አንተና ወንድምህ አሮን ማህበረሰቡን ሰብስቡ፡፡ በፊታቸው ለዓለቱ ተናገር፣ ውሃ እንዲያፈስም አለቱን እዘዘው፡፡ ከዚያ ዓለት ውሃ አውጥተህ ትሰጣቸዋለህ፣ ማህበረሰቡና ከብቶቻቸው ይጠጡ ዘንድ ውሃ ስጣቸው፡፡”
9ሙሴ ያህዌ እንዳዘዘው ከያህዌ ፊት በትሩን ወሰደ፡፡
10ከዚያ ሙሴና አሮን ጉባኤውን በአለቱ ፊት ሰበሰቡ፡፡ ሙሴ ጉባኤውን እንዲህ አለ፣ “እናንተ አመጸኞች፣ አሁን ስሙ፡፡ ከዚህ ዓለት ለእናንተ ውሃ ማውጣት አለብን?”
11ከዚያ ሙሴ እጁን አንስቶ በበትሩ አለቱን ሁለት ጊዜ መታው፣ እናም ብዙ ውሃ ወጣ፡፡ ማህበረሰቡ ጠጣ፣ እንዲሁም ከብቶቻቸው ጠጡ፡፡
12ከዚያ ያህዌ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፣ “እኔን ስላላመናችሁ ወይም በእስራኤል ሰዎች ዐይኖች ፊት ቅዱስ አድርጋች ስላለያችሁኝ፣ ይህን ጉባኤ ወደ ሰጠኋችሁ ምድር አታስገቧቸውም፡፡”
13ይህ ቦታ የመሪባ ውሃ ተብሎ ተጠራ፣ ምክንያቱም በዚያ የእስራኤል ሰዎች ከያህዌ ጋር ተጣልተው ነበር፣ እርሱም ራሱን በቅድስናው ገለፀላቸው፡፡
14ሙሴ ከቃዴስ መልዕክተኞችን ወደ ኤዶም ንጉስ ላከ፡ ወንድምህ እስራኤል ይህን ይላል፡ “በእኛ ላይ የደረሱትን አስቸጋሪ ነገሮች ታውቃለህ፡፡
15አባቶቻችን ወደ ግብፅ ወርደው ለዘመናት በግብጽ መኖራቸውን ታውቃለህ፡፡ ግብጻውያን በእኛና በአባቶቻችን ላይ እጅግ ከፉብን፡፡
16እኛ ወደ ያህዌ ስንጮህ፣ እርሱ ድምጻችንን ሰምቶ መልዓክ ልኮ ከግብጽ አወጣን፡፡ እነሆ፣ በምድርህ ዳርቻ በምትገኘው በቃዴስ እንገኛለን፡፡
17በምድርህ እንድናልፍ እንድትፈቅድልን እጠይቅሃለሁ፡፡ በእርሻዎች ወይም በወይን ሥፍራዎች ውስጥ አናልፍም፣ አሊያም ከጉድጓዶቻችሁ ውሃ አንጠጣም፡፡ የንዱን አውራ ጎዳና ይዘን እንሄዳለን፡፡ ድንበርህን እስክናልፍ ድረስ ወደ ግራም ወደ ቀኝም አንልም፡፡”
18የኤዶም ንጉስ ግን እንዲህ ሲል መለሰለት፣ “በዚህ በኩል ማለፍ አትችሉም፡፡ ይህን ብታደርጉ፣ ሰይፍ ይዤ እወጣባችኋለሁ፡፡”
19ከዚያ የእስራኤል ሰዎች እንዲህ አሉት፣ “እኛ በአውራ ጎዳናው እንሄዳለን፡፡ እኛም ሆን ከብቶቻችን ውሃህን ብንጠጣ፣ ለዚያም እንከፍላለን፡፡ ሌላ ምንም ነገር ሳናደርግ በእግራችን እንለፍ፡፡”
20የኤዶም ንጉስ ግን እንዲህ ሲል መለሰ፣ “በዚህ በኩል አታልፉም፡፡” ስለዚህም የኤዶም ንጉስ በብርቱ ክንድ አያሌ ወታደሮች ይዞ በእስራኤላዊያን ላይ መጣባቸው፡፡
21የኤዶም ንጉስ እስራኤላውያን በድንበሩ አቋርጠው እንዳያልፉ ተቃወመ፡፡ በዚህ ምክንያትና እስራኤል ከኤዶም ምድር ተመለሱ፡፡
22ስለዚህ ህዝቡ ከቃዴስ ተነስቶ ተጓዘ፡፡ የእስራኤል ህዝብ፣ መላው ማህበረሰብ ወደ ሖር ተራራ መጣ፡፡
23ያህዌ በሖር ተራራ ለሙሴና አሮን ተናገራቸው፡፡ እንዲህም አለ፣
24”አሮን ለእስራኤል ህዝብ ወደ ሰጠኋት ምድር አይገባምና ወደ አባቶቹ ይሰበሰባል፡፡ ይህም የሚሆነው እናንተ ሁለታችሁም በመሪባ ውሃ በእኔ ቃሎች ላይ ስላመፃችሁ ነው፡፡
25አሮንንና ልጁን አልዓዛርን ይዘህ ወደ ሖር ተራራ አምጣቸው፡፡
26የአሮንን የክህነት ልብስ ከእርሱ ላይ አውልቀህ ልጁን አልዓዛርን አልብሰው፡፡ አሮን በዚያ ይሞትና ወደ ወገኖቹ ይሰበሰባል፡፡”
27ሙሴ ያህዌ እንዳዘዘው አደረገ፡፡ መላው ማህበረሰብ እያየ ወደ ሖር ተራራ ወጡ፡፡
28ሙሴ የአሮንን የክህነት ልብሶች ከእርሱ አውልቆ ልጁን አልዓዛርን አለበሰው፡፡ አልዓዛር በተራራው አናት ላይ በዚያ ሞተ፡፡ ከዚያ ሙሴና አልዓዛር ከተራራው ወደ ታች ወረዱ፡፡
29መላው ማህበረሰብ አሮን እንደ ሞተ ባየ ጊዜ፣ ጠቅላላው አገሩ ለሰላሳ ቀናት ለአሮን አለቀሰ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።