መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘኁልቁ 19

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ያህዌ ለሙሴና ለአሮን ተናገረ፤ እንዲህም አለ፣
2”ይህ እናንተን የማዛችሁ ትዕዛዝ መታሰቢየ ነው፡፡ የእስራኤል ሰዎች ወደ አንተ ቀንበር ተጭኟት የማታውቅ፣ እንከን ወይም ነውር የሌለባት ቀይ ጊደር እንዲያመጡ ንገራቸው፡፡
3ጊደሯን ለካህኑ ለአልዓዛረ ስጠው፡፡ ከሰፈር ውጭ ያውጣት አንድ ሰው በፊቱ ይረዳት፡፡
4ካህኑ አልአዛር ከጊደሯ ደም በጣቱ ወስዶ በመገናኛው ድንኳን ፊት ባለው አቅጣጫ ሰባት ጊዜ ይርጨው፡፡
5ሌላ ካህን እርሱ እያየ ጊደሯን ያቃጥላት፡፡ ቆዳዋን፣ ስጋ እና ደሟን ከፈርሷ ጋር ያቃጥል፡፡
6ካህኑ የዝግባ እንጨት፣ ሂሶጵ፣ እና ደማቅ ሱፍ ይውሰድና ጊደሯ በምትቃጠልበት እሳት ውስጥ ይጨምር፡፡
7ከዚየ ልብሱን ይጠብ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፡፡ ከዚያ እስከ ምሽት እርኩስ ሆኖ ከቆየበት ወደ ሰፈር መመለስ ይችላል፡፡
8ጊደሯን ያቃጠለው ሰው ልብሱን በውሃ ይጠብ ገላውንም ይታጠብ፡፡ እስከ ምሽት እርኩስ ሆኖ ይቆያል፡፡
9ንጹህ የሆነ አንድ ሰው የጊደሯን አመድ አፍሶ ከሰፈር ውጭ ንጹህ በሆነ ስፍራ ይድፋው፡፡ ይህ አመድ ለእስራኤል ሰዎች ለማህበረሰቡ ይጠበቅ፡፡ አመዱ ከኃጢአት መስዋዕት የተገኘ እንደመሆኑ፣ ከኃጢአት ለመንጻት በውሃ ይበጠብጡታል፡፡
10የጊደሯን አመድ ያፈሰው ሰው ልብሱን ይጠብ፡፡ እስከ ምሽት እርኩስ ሆኖ ይቆያል፡፡ ይህ ለእስራኤላዊያንና ከእነርሱ ጋር ለሚኖሩ መጻተኞችም ቋሚ ህግ ይሆናል፡፡
11ማንም የሞተን ሰው አካል የነካ ሁሉ ለሰባት ቀናት እርኩስ ነው፡፡
12እንዲህ ያለው ሰው በሶስተኛውና በሰባተኛው ቀን ራሱን ያንጻ፡፡ ከዚያ ንጹህ ይናል፡፡ ነገር ግን በሶስተኛው ቀን ራሱን ካላነጻ፣ በሰባተኛው ቀን ንጹህ አይሆንም፡፡
13የሞተን ሰው የነካ ማንም ቢሆን፣ የሞተን ሰው የነካ ሁሉ፣ እናም ራሱን ያላነጻ ይህ ሰው የያህዌን ማደሪያ ያረክሳል፡፡ ያ ሰው ከእስራኤል ተለይቶ ይጥፋ፤ ምክንያቱም ከእርኩሰት የሚያነጻው ውሃ አልተረጨበትም፡፡ እርኩስ ሆኖ ይቆያል፣ ያለመንጻቱ በእርሱ ላይ ይቆያል፡፡
14አንድ ሰው በድንኳን ውስጥ በሚሞትበት ጊዜ ህጉ ይህ ነው፡፡ ወደ ድንኳኑ የገባ እያንዳንዱ ሰውና ቀድሞውኑም በድንኳኑ ውስጥ የነበረ ሰው ለሰባት ቀናት ንጹህ አይደለም፡፡
15ያልተከደነና ያልተሸፈነ ማናቸውም ዕቃ ይረክሳል፡፡
16በተመሳሳይ፣ በሰይፍ የተገደለንም ሰው ሆነ ማናቸውንም በሌላ ሁኔታ የሞተን ሰው፣ ወይም የሞተን ሰው አጽም፣ ወይም መቃብር የነካ ማናቸውም ከድንኳን ውጭ ያለ ሰው ለሰባት ቀናት ንጹህ አደለም፡፡
17ለረከሰ ሰው ይህን አድርግ፡ ከተቃጠለው የኃጢአት መስዋዕት ጥቂት አመድ ውሰድና በንጹህ ውሃ በዕቃ ውስጥ በጥብጠው፡፡
18ንጹህ የሆነ ሰው ሂሶጵ ይውሰድና ውሃው ውስጥ ይንከረው፤ ከዚያም በድንኳኑ ላይ፣ በድንኳኑ ውስጥ ባሉ ዕቃዎች ሁሉ ላይ፣ በዚያ በሚገኙ ሰዎች ላይ፣ እንዲሁም የሞተ ሰውን አጽም፣ የተገደለን ሰው፣ የሞተን ሰው ወይም መቃብር በነካ ሰው ላይ ይርጨው፡፡
19በሶስተኛው ቀንና በሰባተኛው ቀን፣ ንጹህ የሆነው ሰው ንጹህ ያልሆነውን ሰው ይርጨው፡፡ ያልነጻው ሰው በሰባተኛው ቀን ራሱን ያንጻ፡፡ ልብሱን ይጠብ ገላውንም በውሃ ይታጠብ፡፡ ምሽት ላይ ንጹህ ይሆናል፡፡
20ነገር ግን ሳይነጻ የሚቆይ ማናቸው ሰው፣ ራሱን ለማንጻት ያልፈቀደ ሰው ያ ሰው ከማህበረሰቡ ተለይቶ ይጥፋ፣ ምክንቱም የያህዌን መቅደስ አርክሷል፡፡ ከእርኩሰት የሚያነጻው ውሃ በእርሱ ላይ አልተረጨምና እርኩስ ሆኖ ይቆያል፡፡
21ለእነዚህ ሁኔታዎች ይህ ቀጣይ ህግ ይሆናል፡፡ ለመንጻት የሚሆንን ውሃ የሚረጨው ሰው ልብሶቹን ይጠብ፡፡ የሚያነጻውን ውሃ የሚነካ ሰው እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡
22ማናቸውም ንጹህ ያልሆነ ሰው የነካው ነገር እርኩስ ይሆናል፡፡ ያንን የነካ ሰው እስከ ምሽት እርኩስ ይሆናል፡፡”
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።