1ያህዌ ለሙሴና ለአሮን እንደገና እንዲህ አለ፣
2“እያንዳንዱ እስራኤላዊ በየአባቶቻቸው ቤቶች በአርማው ስር በቦታው ይሰፈር፡፡ በመገናኛው ድንኳን ዙሪያ በሁሉም አቅጣጫ ይሰፍራሉ፡፡
3ፀሐይ በምትወጣበት፣ በመገናኛው ድንኳን በስተምስራቅ ይሁዳ በቦታው ይሰፍራል፡፡ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን የይሁዳ ህዝብ መሪ ነው፡፡
4የይሁዳ ህዝብ ቁጥር 74600 ነው፡፡
5የይሳኮር ጎሳ ከይሁዳ ቀጥሎ ይስፈር፡፡ የሶገር ልጅ ናትናኤል የይሳኮርን ሰራዊት ይምራ፡፡
6በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 54400 ነው፡፡
7የዛብሎን ጎሳ ከይሳኮር ቀጥሎ ይስፈር፡፡ የኬሎን ልጅ ኤልያብ የኤሎንን ሰራዊት ይምራ፡፡
8በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 57400 ነው፡፡
9ጠቅላላው የይሁዳ ሠራዊት ቁጥር 186400 ነው፡፡ እነርሱ በቅድሚያ ይወጣሉ፡፡
10በስተደቡብ አቅጣጫ የሮቤል ምድብ በስፍራው ይሆናል፡፡ የሮቤል ምድብ መሪ የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር ነው፡፡
11በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 46500 ነው፡፡
12ስምዖን ከሮቤል ቀጥሎ ይሰፍራል፡፡ የስምዖን ህዝብ መሪ የሱሪሰዳይ ልጅ ስለሚኤል ነው፡፡
13በእርሱ ምድብ የሚገኘው የሰራዊት ቁጥር 59, 300 ነው፡፡
14የጋድ ጎሳ ይቀጥላል፡፡ የጋድ ህዝብ መሪ የራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ ነው፡፡
15በእርሱ ምድብ የሚገኘው የሰራዊት ቁጥር 45650 ነው፡፡
16በሮቤል ምድብ የሚገኙት በክፍላቸው መሠረት 151450 ናቸው፡፡ እነርሱ ቀጥለው ይወጣሉ፡፡
17ቀጥሎ፣ የመገናኛው ድንኳን ሌዋውያንን ከሁሉም ምድብተኞች መሃል አድርጎ ከሰፈር ይወጣል፡፡ ወደ ሰፈር በገቡበት ስርዓት ከሰፈር ይውጡ፡፡ እያንዳንዱ ሰው በዐርማው ስር በስፍራው ይሁን፡፡
18የኤፍሬም ሰፈር ክፍሎች በስፍራቸው ይሁኑ፡፡ የኤፍሬም ህዝብ መሪ የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ ነው፡፡
19በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 40500 ነው፡፡
20ከእነርሱ የሚቀጥለው የምናሴ ጎሳ ነው፡፡ የምናሴ መሪ የፍርዱሱር ልጅ ገማልኤል ነው፡፡
21በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 32200 ነው፡፡
22ቀጣይ የሚሆነው የብንያም ጎሳ ነው፡፡ የብንያም መሪ የጋዴዮን ልጅ አቢዳን ነው፡፡
23በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 35400 ነው፡፡
24በኤፍሬም ምድብ የሚኙት በክፍላቸው መሰረት 108100 ናቸው፡፡ እነርሱ ሶስተኛ ሆነው ይወጣሉ፡፡
25በሰሜን የዳን ሰፈር ምድብተኞች ይሰፍራሉ፡፡ የዳን ህዝብ መሪ የአሚሳዓይ ልጅ አብዔዘር ነው፡፡
26በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 62700 ነው፡፡
27የአሴር ጎሳ ህዝብ ሰፈር ከዳን ቀጥሎ ነው፡፡ የአሴር መሪ የኤክራን ልጅ ፋግኤል ነው፡፡
28በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 41500 ነው፡፡
29ቀጣዩ የንፍታሌም ጎሳ ነው፡፡ የንፍታሌም መሪ የዔናን ልጅ አኪሬ ነው፡፡
30በእርሱ ክፍል የሰራዊቱ ቁጥር 53400 ነው፡፡
31ከዳን ጋር በሰፈር የሚገኙት ቁጥራቸው 157600 ነው፡፡ እነርሱ በዐርማቸው ስር ከሰፈር በመጨረሻ ይወጣሉ፡፡”
32በየቤተሰባቸው የተቆጠሩት እስራኤላውያን እነዚህ ናቸው፡፡ በየክፍሎቻቸው በሰፈሮቻቸው የተቆጠሩት በጠቅላላ 603550 ናቸው፡፡
33ነገር ግን ሙሴና አሮን በእስራኤል ሕዝብ መሀል ሌዋውያንን አልቆጠሩም፡፡ ይህም ያህዌ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ነበር፡፡
34የእስራኤል ሕዝብ ያህዌ ሙሴን ያዘዘውን ነገር ሁሉ አደረጉ፡፡ በየአርማቸው ስር ሰፈሩ፡፡ በአባቶቻቸው ቤቶች መሠረት በየነገዳቸው ከሰፈር ወጡ፡፡