1ያህዌ በሲና ምድረ በዳ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሙሴን ተናገረው፡፡ ይህ የሆነው የእስራኤል ህዝብ ከግብጽ ምድር በወጣበት በሁለተኛው አመት በሁለኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ነበር፡፡ ያህዌ እንዲህ አለ፣
2“በየነገዱ፣ በየአባቶቻቸው ቤተሰቦች የእስራኤል ወንዶች ቆጠራ ይደረግ፡፡ በስም ቁጠራቸው፡ እያንዳንዱ ወንድ፣ በሰው ቁጠር፣
3ሀያ አመት የሞላው ወይም ከዚያ በላይ የሆነ ወንድ ሁሉ ይቆጠር፡፡ ለእስራኤል ወታደር ሆኖ ሊዋጋ የሚችለውን ሁሉ ቁጠር፡፡ አንተና አሮን በታጣቂ ቡድኖቻቸው የወንዶችን ቁጥር መዝግቡ፡፡
4ከእያንዳንዱ ጎሳ አንድ ሰው፣ የነገድ አለቃ ከአንተ ጋር የጎሳው መሪ ሆኖ ያገልግል፡፡ እያንዳንዱ መሪ ለጎሳው የሚዋጉትን ወንዶች ይምራ፡፡
5ከአንተ ጋር ሆነው መዋጋት ያለባቸው መሪዎች ስሞቻቸው እነዚህ ናቸው፡ ከሮቤል ጎሳ፣ የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር፣
6ከስምዖን ጎሳ የሱሪሰዳይ ልጅ ሰለሚኤል፤
7ከይሁዳ ጎሳ፣ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን፤
8ከይሳኮር ጎሳ የሶገር ልጅ ናትናኤል፤
9ከዛብን ጎሳ፣ የኬሎን ልጅ ኤልያብ፤
10ከኤፍሬም ጎሳ፣ የዮሴፍ ልጅ፣ የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ፤ ከምናሴ ጎሳ፣ የፍዳሱር ልጅ ገማልኤል፤
11ከብንያም ጎሳ የዮሴፍ ልጅ፣ የጌዲዮን ልጅ አቢዳን፤
12ከዳን ጎሳ የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር፣
13ከአሴር ጎሳ፣ የኤክራን ልጅ ፉግኤል፣
14ከጋድ ጎሳ የራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ፤
15እና ከንፍታሌም ጎሳ፣ የዔናን ልጅ አኪሬ” ናቸው፡፡
16ከሕዝቡ የተመረጡት ወንዶች እነዚህ ነበሩ እነርሱ የአባቶቻቸውን ጎሳዎች ይመራሉ፡፡ በእስራኤል የነገዶች መሪዎች ነበሩ፡፡
17ሙሴና አሮን በስም የተመዘገቡትን እነዚህን ወንዶች ወሰዱ፣
18ከእዚህ ወንዶች ጋር በሁለተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን የእስራኤል ወንዱን ሁሉ ሰበሰቡ፡፡ ከዚያም ሃያ አመት የሞላውና ከዚያ በላይ የሆነ እያንዳንዱ ወንድ የትውልድ ሐረጉን ተናገረ፡፡ እያንዳንዱ የነገዱን ስም እና የትውልድ ሐረጉን መጥራት ነበረበት፡፡
19ከዚያም ሙሴ በሲና ምድረ በዳ ያህዌ እንዲያደርገው ባዘዘው መሠረት ቁጥራቸውን መዘገበ፡፡
20የእስራኤል በኩር ከሆነው ከሮቤል ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉት ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡
21ከሮቤል ጎሳ 46500 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡
22ከስምኦን ትውልዶች ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉት ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡
23ከስምዖን ጎሳ 59300 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡
24ከጋድ ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡
25ከጋድ ጎሳ 45650 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡
26ከይሁዳ ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስም ተቆጠሩ፡፡
27ከይሁዳ ጎሳ 7460 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡
28ከይሳኮር ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡
29ከይሳኮር ጎሳ 54400 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡
30ከዛብሎን ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡
31ከዛብን ጎሳ 57400 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡
32ከዮሴፍ ልጅ ከኤፍሬም ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡
33ከኤፍሬም ጎሳ 40500 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡
34ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፤
35ከምናሴ ጎሳ 32200 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡
36ከብንያም ትውልዶች ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፤
37ከብንያም ጎሳ 35400 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡
38ከዳን ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡
39ከዳን ጎሳ 62700 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡
40ከአሴር ትውልዶች፣ ወደ ጦርት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡
41ከአሴር ጎሳ 41500 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡
42ከንፍታሌም ትውልዶች፣ ወደ ጦርነት መሄድ የሚችሉ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ከየጎሳቸውና፣ ከየቤተሰባቸው መዛግብት እያንዳንዳቸው በስማቸው ተቆጠሩ፡፡
43ከንፍታሌም ጎሳ 53400 ወንዶች ተቆጠሩ፡፡
44ሙሴና አሮን እነዚህን ወንዶች ሁሉ አስራ ሁለቱን የእስራኤል ጎሳዎች ከሚመሩ አስራ ሁለት ሰዎች ጋር ሆነው ቆጠሩ፡፡
45ስለዚህም ሃያ አመትና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያላቸው ለጦርነት መውጣት የሚችሉ የእስራኤል ወንዶች ሁሉ በየቤተሰባቸው ተቆጠሩ፡፡
46የቆጠሯቸው ወንዶች 603550 ናቸው፡፡
47ከሌዊ ትውልድ የሆኑት ግን አልተቆጠሩም፣
48ምክንያቱም ያህዌ ሙሴን እንዲህ ብሎት ነበር፣
49“የሌዊን ጎሳ አትቆጥርም ወይም እነርሱን በእስራኤል ህዝብ ቆጠራ ውስጥ አታስገባቸው፡፡
50ይልቁንም፣ ሌዋውያንን የቃልኪዳኑን ስርዓቶች በቤተመቅደስ እንዲፈጽሙ መድባቸው፣ እንደዚሁም በቤተመቅደስ ውስጥ የሚገኙ መገልገያዎችንና ማናቸውንም ነገሮች እንዲንከባከቡ ሹማቸው፡፡ ሌዋውያን ጽላቱን ይሸከሙ፣ እንዲሁም የቤተመቅደሱን ዕቃዎች ይሸከሙ፡፡
51ቤተመቅደሱ ወደ ሌላ ስፍራ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ፣ ሌዋውያኑ ይንቀሉት፡፡ ቤተመቅደሱ ሲተከል፣ ሌዋውያን ይትከሉት፡፡ ወደ ቤተ መቅደሱ የሚጠጋ ማናቸውም እንግዳ ይገደል፡፡
52እስራኤላውያን ድንኳኖቸውን ሲተክሉ፣ እያንዳንዱ ሰው ወደ ራሱ የጦር ቡድን ዐርማ አጅግ ቀርቦ ይስራ፡፡
53ሆኖም፣ ሌዋውያኑ ቁጣዬ በእስራኤላውያን ላይ እንዳይሆን ድንኳናቸውን በቃል ኪዳኑ ማደሪያ ዙሪያ ይትከሉ፡፡ ሌዋውያኑ የቃልኪዳኑን ማደሪያ ሀላፊዎች ናቸው፡፡”
54እስራኤላውያን እነዚህን ሁሉ ነገሮች አደረጉ፡፡ ያህዌ በሙሴ በኩል ያዘዛቸውን ነገሮች ሁሉ አደረጉ፡፡