1“ያህዌ አሮንን እንዲህ አለው፣ “አንተ፣ ወንዶች ልጆችህና የአባትህ ቤቶች በቤተ መቅደሱ ላይ ለሚሰራው በደል ተጠያቂ ትሆናላች፡፡ በክህነቱ ላይ ለሚፈፀሙ በደሎች ሁሉ ግን አንተና ከአንተ ጋር ያሉ ወንዶች ልጆች ብቻ ተጠያቂ ትሆናላችሁ፡፡
2ከአባትህ ነገድ የሆኑት ሌዋዊያንን በሚመለከት ከአንተ ጋር ይሆኑና አንተና ልጆችህ በምስክሩ ድንኳን ፊት ስታገለግሉ እንዲረዷችሁ አምጣቸው፡፡
3እነርሱ አንተንና መላውን ድንኳን ያገልግሉ፡፡ ሆኖም፣ ወደ ተቀደሰው ስፍራ ማናቸውም ነገሮች አይቅረቡ ወይም ከመሰዊያው ጋር አይነካኩ፣ አለበለዚያ እነርሱና አንተም ጭምር ትሞታላችሁ፡፡
4እነርሱ ከአንተ ጋር ሆነው ለመገናኛው ድንኳንና ከድንኳኑ ጋር ለተያያዙ ስራዎች ሁሉ እንክብካቤ ማድረግ አለባቸው፡፡ መጻተኛው ወደ አንተ አይጠጋ፡፡
5አንተ ለተቀደሰው ስፍራና ለመሰዊያው ሀላፊነት መውሰድ አለብህ፣ እንደገና ቁጣዬ በእስራኤል ሰዎች ላይ እንዳይመጣ ይህን አድርግ፡፡
6ከእስራኤል ትውልዶች መሀል ሌዋውያንን የመረጥኩት እኔ ራሴ ነኝ፡፡ እነርሱ ከመገናኛው ድንኳን ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ለመስራት ለእኔ የተሰጡ ለእናንተ ስጦታዎች ናቸው፡፡
7ከመሰዊያውና በመጋረጃው ውስጥ ያሉትን አገልግሎቶች ሁሉ በሚመለከት ግን የክህነቱን ስራ የምትሰሩት አንተና ወንዶች ልጆችህ ብቻ ናችሁ፡፡ አንተ ራስህ እነዚያን ሀላፊነቶች መወጣት አለብህ፡፡ እኔ ክህነቱን ስጦታ አድርጌ ሰጥቼሃለሁ፡፡ ማናቸውም መጻተኛ ወደዚህ ቢጠጋ ይገደል፡፡”
8ከዚያ ያህዌ አሮንን እንዲህ አለው፣ “ለእኔ የሚወዘወዙትን መስዋዕቶችና የእስራኤል ሰዎች ለእኔ የሰጧቸውን ቅዱስ መስዋዕቶች አያያዝ ሀላፊነቶች ሰጥቼሃለሁ፡፡ እነዚህን ስጦታዎች ቀጣይ ድርሻህ አድርጌ ለአንተና ለወንዶች ልጆችህ ሰጥቻለሁ፡፡
9ለያህዌ ሙሉ ለሙሉ ከተለዩ ከእነዚህ ስጦታዎች ውስጥ ሙሉ ለሙሉ የማይቃጠሉት የአንተ ናቸው፡፡ ህዝቡ የሚያመጣው ማናቸውም መስዋዕት፣ የእህል ቁርባኑን፣ የኃጢአት መስዋዕቱን፣ እና የበደል መስዋዕቱን ሁሉ ጨምሮ፣ እነዚህ እጅግ ቅዱስ የሆኑ ለእኔ የሚለይዋቸውና የሚያመጧቸው ስጦታዎች የአንተና የወንዶች ልጆችህ ይሆናሉ፡፡
10አንተ የምትመገባቸው እነዚህ ስጦታዎች፣ ሙሉ ለሙሉ ለእኔ የተለዩ ናቸው፡፡ በመሀል የሚገኝ ማናቸውም ወንድ እነዚህን ስጦዎች ይብላ፡፡ እነርሱ በእናንተ ዘንድ ለእኔ የተለዩ ተደርገው ይቆጠሩ፡፡
11እነዚህ የእናንተ ስጦታዎች ናቸው፡፡ ከእስራኤል ሰዎች ከሚሰበሰቡ መስዋዕቶች ውስጥ የተለዩት ስጦታዎቻቸው ሁሉ፣ በእኔ ፊት የተወዘወዙና ለእኔ የቀረቡ ስጦዎች ሁሉ የእናንተ ናቸው፡፡ እነዚህን ለእናንተ፣ ለወንዶች ልጆቻችሁ፣ እና ለሴቶች ልጆቻችሁ፣ ቀጣይ ድርሻችሁ አድርጌ ሰጥቻለሁ፡፡ እያንዳንዱ በቤተሰብህ ውስጥ የመንጻት ሥርዓት የፈፀመ ሁሉ ከእነዚህ ስጦታዎች መመገብ ይቻላል፡፡
12ከዘይቱ ምርጥ የሆነውን፣ ከአዲሱ ወይንና ሰብል ምርጡን፣ ህዝቡ ለእኔ ካቀረበው በኩራቱን፣ እነዚህን ሁሉ ለእናንተ ሰጥቻለሁ፡፡
13ለእኔ የሚያመጡት፣ በምድራቸው ካለው በመጀመሪያ የደረሰው ፍሬ ሁሉ የአንተ ነው፡፡ በቤተሰብህ ውስጥ ያለ ንጹህ የሆነ ሁሉ እነዚህን ነገሮች መብላት ይችላል፡፡
14በእስራኤል ማናቸው ፈጽሞ የተሰጠ ነገር የአንተ ይሆናል፡፡
15እያንዳንዱ ማህጸን የሚከፍት ሁሉ፣ ሰዎች ለያህዌ የሰጡት በኩር ሁሉ፣ የሰውም ይሁን የእንስሳ በኩር የአንተ ይሆናል፡፡ የሆነ ሆኖ፣ ሰዎቹ መጀመሪያ የተወለደውን ሁሉ መልሰው ይግዙ፣ ንጹህ ያልሆኑ እንስሳትን በኩራት መልሰው ይግዙ፡፡
16በሰዎች ተመልሰው የሚገዙ አንድ ወር ከሞላቸው በኋላ መልሰው ይገዙ፡፡ ከዚያ ሰዎቹ በመቅደሱ ሰቅል ዋጋ መልሰው ከሀያ ጌራ ጋር እኩል ዋጋ ባለው በአምስት ሰቅሎች ዋጋ ሊገዟቸው ይችላሉ፡፡
17ነገር ግን የላም በኩር፣ ወይም የበግ በኩር፣ ወይም የፍየል በኩር ከሆነ እነዚህን እንስሳት መልሰህ አትግዛ፤ እነዚህ ለእኔ የተሰዉ ናቸው፡፡ ለእኔ ጣፋጭ መዓዛ ለማቅረብ፣ ደማቸውን በመሰዊያ ላይ እርጨው፣ ስባቸውን በእሳት የቀረበ መስዋዕት አድርገህ ኣቃጥለው፡፡
18ስጋቸው ለአንተ ይሁን፡፡ ልክ እንደ ሚወዘወዘው ፍርምባና እንደ ቀኙ ወርች ስጋቸው የአንተ ይሆናል፡፡
19የእስራኤል ሰዎች ለእኔ ያቀረቧቸውን ቅዱስ የሆኑ መስዋዕቶች ሁሉ እኔ፤ ለአንተ፣ ለወንድ ልጆችህ እና ለሴት ልጆችህ ቀጣይ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ፡፡ ለጨው ኪዳንና ለዘለዓም የአንድነት መስዋዕት ሆነው በፊቴ ከአንተና ከትውልድህ ጋር ይኖራሉ፡፡”
20ያህዌ አሮንን እንዲህ አለው፣ “አንተ በህዝቡ ምድር ርስት አይኖርህም፣ ወይንም ደግሞ በህዝቡ መሀል የሀብት ድርሻ አይኖርህም፡፡ በእስራኤል ህዝብ መሀል እኔ ድርሻህና ርስትህ ነኝ፡፡
21እስራኤላዊያን የሚያመጡትን አስራት ሁሉ፣ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለሚሰጡት አገልግሎት ድርሻቸው አድርጌ ለሌዊ ትውልድ ሰጥቻቸዋለሁ፡፡
22ከአሁን አንስቶ ከእስራኤል ህዝቡ ወደ መገናኛው ድንኳን አይቅረብ፣ ከቀረቡ በኃጢአታቸው ሀላፊነትን ይወስዳሉ፤ እናም ይሞታሉ፡፡
23ከመገናኛው ድንኳን ጋር የተያያዙ ሥራዎችን ሌዋውያን ይስሩ፡፡ ይህን በሚመለከት ለማናቸውም ኃጢአት ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡ ይህ በእናተ ህዝብ ትውልዶች ሁሉ ቀዋሚ ህግ ይሆናል፡፡ በእስራኤል ህዝብ መሀል ሌዋውያን ርስት ሊኖቸው አይገባም፡፡
24እስራኤላዊያን መባ አድርገው ለእኔ ያቀረቡትን አስራት እኔ ለሌዋውያን ርስታቸው አድርጌ የሰጠሁት እነዚህን ነው፡፡ ለዚህም ነው እንዲህ የምላቸው፣ ‘እነርሱ በእስራኤል ህዝብ መሀል ርስት አይኖራቸውም፡፡’”
25ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
26”ለሌዋውያን እንዲህ በላቸው፣ ‘ከእነርሱ የአንተ ርስት አድርጎ ያህዌ ለእናንተ የሰጣችሁን አስራት ከእስራኤል ሰዎች ስትቀበሉ፣ ከዚያ አስራት ለእርሱ አንድ አስረኛውን መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፡፡
27እናንተ የምታቀርቡት መስዋዕት በእናንተ ዘንድ ከአውድማ እንደ ቀረበ የእህል አስራት ወይም ከወይን መጥመቂያ እንደ ቀረበ አስራት ሊቆጠር ይገባዋል፡፡
28እንደዚሁም ከእስራኤል ሰዎች ከተቀበላችሁት አስራት ሁሉ ለያህዌ መባ ማቅረብ አለባችሁ፡፡ ከእነዚህም ለካህኑ ለአሮን ለእግዚአብሔር ከቀረበው ስጦታ መስጠት አለባች፡፡
29ከተቀበላችሁት ስጦታ ሁሉ፣ ከእያንዳንዱ ለያህዌ መባ መስጠት አለባችሁ፡፡ ይህንን ምርጥ ከሆነው ሁሉና ለእናንተ ከሰጠኋችሁ እጅግ ከተቀደሱት ነገሮች ማድረግ አለባችሁ፡፡’
30ስለዚህም እንደዚህ በላቸው፣ ‘ከተቀበላችሁት ምርጡን ስታቀርቡ፣ ይህ በሌዋውያን ዘንድ ከአውድማ እንደቀረበ ምርትና ከወይን መጥመቂያ እንደቀረበ ሊቆጠር ይገባል፡፡
31የተቀረውን ስጦታዎቻችሁን በማንኛውም ስፍራ ልትበሉ ትችላላችሁ፣ እናንተና ቤተሰቦቻችሁ ብሉት፣ ምክንያቱም በመገናኛው ድንኳን ለምትሰጡት አገልግሎት ክፍያችሁ ነው፡፡
32ከተቀበላችሁት ምርጥ የሆነውን ለያህዌ ካቀረባችሁ፣ ያን በመብላታችሁና በመጠጣታችሁ ምንም አይት በደል በራሳችሁ ላይ አታመጡም፡፡ ነገር ግን የተቀደሱ የእስራኤል ህዝቦች ስጦታዎች አታቃሉ፣ አሊያ ትሞታላች፡፡