መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘኁልቁ 17

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
2”ለእስራኤል ሰዎች ተናገራቸው፡፡ ከእነርሱ በትሮችን ውሰድ፣ ከየነገዱ አባቶች አንድ በትር ውሰድ፡፡ ከእያንዱ መሪ አንድ በአጠቃላይ ከየነገድ የተመረጡ አስራ ሁለት በትሮችን ውሰድ፡፡ የእያንዳንዱን ሰው ስም በበትሩ ላይ ጻፍ፡፡
3የአሮንን ስም በሌዊ በትር ላይ ጻፍ፡፡ ለእያንዳንዱ መሪ ከየአባቶቹ ነገድ አንድ በትር ሊኖር ያስፈልጋል፡፡
4በትሮቹን ከአንተ ጋር በምገናኝበት በመገናኛው ድንኳን ከምስክሩ ኪዳን ፊት አስቀምጣቸው፡፡
5እንዲህ ይሆናል፣ እኔ የምመርጠው ሰው በትር ታቆጠቁጣለች፡፡ የእስራኤለ ሰዎች በአንተ ላይ የሚያደርጉትን ማጉረምረማቸውን እንዲያቆሙ አደርጋለሁ፡፡”
6ሙሴ ለእስራኤል ሰዎች ተናገረ፡፡ ሁሉም የነገዱ መሪዎች በትሮቻቸውን ሰጡት፣ ከእያንዳንዱ መሪ አንድ በትር፣ ከየነገዱ አባቶች ተመረጠ፣ በአጠቃላይ አስራ ሁለት በትሮች ተመረጡ፡፡ የአሮን በትር ከእነዚህ መሀል ነበር፡፡
7ከዚያ ሙሴ እነዚህን በትሮች ወስዶ በያህዌ ፊት በምስክሩ ድንኳን ውስጥ አስቀመጣቸው፡፡
8በማግስቱ ሙሴ ወደ ምስክሩ ድንኳን ሄደ፣ እናም የሌዊ ነገድ የሆነችው የአሮን በትር አቆጥቁጣ አየ፡፡ እምቡጥ አብቅላ፣ አበባና ለውዝም አፍርታ ነበር!
9ሙሴ በትሮቹን ሁሉ ከያህዌ ፊት ወደ እስራኤል ሰዎች ሁሉ አመጣቸው፡፡ እያንዳንዱ ሰው የራሱን በትር አግኝቶ ወሰደ፡፡
10ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “የአሮንን በትር በምስክሩ ፊት አስቀምጣት፡፡ ባመፁት ሰዎች ላይ ለበደላቸው ምልክት ይሆን ዘንድ አስቀምጣት፣ ስለዚህም በእኔ ላይ የሚያሰሙትን ማጉረምረም ፍጻሜ ታደርግለታለህ፤ ይህ ካልሆነ ይሞታሉ፡፡”
11ሙሴ ልክ ያህዌ እንዳዘዘው አደረገ፡፡
12የእስራኤል ሰዎች ሙሴን፣ “እኛ ሁላችንም እዚህ መሞታችን ነው፣ ሁላችንም መጥፋታችን ነው!
13ወደ ያህዌ ማደሪያ ድንኳን የቀረቡ፣ እያንዳንዳቸው ወደዚህ የመጡ ይሞታሉ፡፡ ሁላችንም መጥፋት ይኖርብናልን?” አሉት፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።