መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘኁልቁ 15

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከዚያ ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣
2“ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‘ያህዌ ለእናንተ ወደሚሰጣችሁ ወደ ምትኖሩባት ምድር ስትገቡ
3ለእርሱ በእሳት መስዋዕት ስታቀርቡ፣ የሚቃጠል መስዋዕት ወይም ስዕለት ስታመጡ ወይም የበጎ ፈቃድ ስጦታ፣ ወይም በባዕላቶቻችሁ ለያህዌ ስጦታዎችን ከከብቶች ወይም ከመንጋችሁ ስታቀርቡ
4ለያህዌ መስዋዕቱን የሚያቀርበው ሰው፣ በአንድ አራተኛ ኢን ዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ አስረኛ መልካም ዱቄት የእህል መስዋዕት ያቅርብ፡፡
5እንዲሁም የኢን አንድ አራተኛ ወይን ለመጠጥ መስዋዕት አቅርቡ፡፡ ይህን ከሚቃጠል መስዋዕት ጋር ወይም እያንዳንዱ ጠቦት ሲቀርብ አድርጉት
6አውራ በግ የምታቀርቡ ከሆነ፣ የኢፍ ሁለት አስረኛ መልካም ዱቄት በአንድ ሶስተኛ ኢን ዘይት የተለወሰ የእህል ቁርባን አቅርቡ፡፡
7ለመጠጥ መስዕት፣ የኢን አንድ ሶስተኛ ወይን አቅርቡ፡፡ ይህ ለያዌ ጣፋጭ መዓዛ ይሆናል፡፡
8ለሚቃተል መስዋዕት በሬ፣ ወይም ስዕለት ለማድረስ መስዋዕት ወይም ለያህዌ የህብረት መስዋዕት ስታዘጋጁ
9ከበሬው ጋር በግማሽ ኢን ዘይት የተለወሰ የኢፍ ሶስት አስረኛ መልካም ዱቄት የእህል ቁርባን አቅርቡ፡፡
10ለያዌ ጣፋጭ መዓዛ እንዲሆን ለመጠጥ ቁርባን የኢን ግማሽ ወይን፣ በእሳት የሚረብ መስዋዕት አቅርቡ፡፡
11እያንዳንዱ በሬ፣ እያንዳንዱ አውራ በግ፣ እና እያንዳንዱ ወንድ ጠቦት በግ ወይም ጠቦት ፍየል ሲቀርበ በዚህ አይት ይሁን፡፡
12እያንዳንዱ የምታዘጋጁት መስዋዕት እና ስጦታ እዚህ እንደተገለፀው ይቅረብ፡፡
13ማንም ሰው ለያህዌ ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ለማቅረብ በእሳት የተዘጋጀ መስዋዕት ሲያመጣ፣ የአገር ተወላጅ የሆነ እስራኤላዊ ሁሉ እነዚህን ነገሮች በዚህ መንገድ ያድርግ፡፡
14መጻተኛው ከእናንተ ጋር ቢኖር፣ ወይም በእናንተ ትውልድ መሀል የሚኖር ማናቸውም ሰው፣ ለያህዌ መልካም መዓዛ ለማቅረብ በእሳት የተዘጋጀ መስወዕት ያድርግ፡፡ እርሱ እናንተ እንደምታደርጉት ያድርግ፡፡
15ለማህበረሰቡ እና ከእናንተ ጋር ለሚኖር መጻተኛ ተመሳሳይ ህግ ይሁን፣ ይህ በትውልዳች ሁሉ የፀና ህግ ይሁን፡፡ እናንተ እንደ ታያችሁት፣ ከእናንተ ጋር የሚኖሩ እንግዶች በአንድ አይነት ይታያሉ፡፡
16ለእናንተም ሆነ ከእናንተ ጋር ለሚኖሩ መጻተኞች ተመሳሳይ ህግና ደንቦች ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡”
17ያህዌ ዳግም ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣
18”ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‘ወደ ማስገባችሁ ምድር በመጣች ጊዜ፣
19በምድሪቱ የተመረተውን ምግብ በበላችሁ ጊዜ፣ መስዋዕት መሰዋትና ለእኔ ማቅረብ አለባችሁ፡፡
20ከመጀመሪያው ቡኬታችሁ ከአውድማው የማንሳት መስዋዕት ህብስት አቅርቡ፡፡ በዚህ መንገድ መስዋዕታችሁን አቅርቡ፡፡
21በትውልዶች ሁሉ ከመጀመሪያው ቡኬታችሁ የማንሳት መስዋዕት ለእኔ ትሰጣላችሁ፡፡
22አንዳንድ ጊዜ ለማድረግ ሳታስቡ ለሙሴ የነገርኩትን እነዚህን ህጎች ሁሉ በተመላለፍና
23ትዕዛዛትን ለእናንተ መስጠት ከጀመርኩበት ቀን አንስቶ በትውልዳችሁ ቀጣይ ዘመናት በሙሴ በኩል ያዘዝኳችሁን ነገሮች በሙሉ ባታደርጉ ኃጢአት ትሰራላችሁ፡፡
24ማህበረሰቡ ሳያውቅ በደል ፈጽሞ ሲገኝ፣ መላው ህብረተሰብ ለያህዌ መልካም መዓዛ እንዲሆን አንድ ወይፈን ለሚቃጠል መስዋዕት ያቀርባል፡፡ ከዚሁ ጋር የእህል ቁርባን እና የመጠጥ ቁርባን እንዲሁም ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል በደንቡ መሠረት ያቅርብ፡፡
25ካህኑ ለመላው የእስራኤል ማህበረሰብ ማስተስረያ ያቀርባል፡፡ ኃጢአቱ የተፈፀመው፣ ባለማወቅ ስለሆነ ይቅር ይባላሉ፡፡ ለእኔ በእሳት የተዘጋጀውን መስዋዕታቸውን አቅርበዋልና ይቅር ይባለሉ፡፡ በእኔ ፊት ሳያውቁ ለፈጸሙት ስህተት የኃጢአት መስዋዕታቸውን አቅርበዋልና፡፡
26ከዚያ መላው የእስራኤል ማህበረሰብና ከእነርሱ ጋር የሚኖሩ መጻተኞች ይቅር ይባላሉ፣ ምክንያቱም ሁሉም ኃጢአቱን የፈፀሙት ሆን ብለው አይደለም፡፡
27አንድ ሰው ሳያውቅ ኃጢአት ቢሰራ ለኃጢአት መስዋዕት የአንድ አመት ሴት ፍየል ያቅርብ፡፡
28ካህኑ ሳያውቅ ኃጢአት ለሰራው ሰው በያህዌ ፊት ያስተሰርይለታል፡፡ ያ ሰው ማስተሰርያ ሲደረግ ይቅር ይባላል፡፡
29ማናቸውንም ነገር ሁን ብሎ ላላደረገ ተመሳሳይ ህግ ይኑራችሁ፣ በእስራኤል ሰዎች መሀል ለሚኖረው ተወላጅም ሆነ መጻተኛ ተመሳሳይ ህግ ይኑራቸው፡፡
30ነገር ግን ራሱን ለመከላከል አንዳች ነገር ያደረገ ሰው፣ የአገር ተወላጅም ይሁን መጻተኛ እኔን ያቃልላል፡፡ ስለዚህ ያ ሰው ከወገኖቹ ተለይቶ ይጥፋ፡፡
31ምክንቱም እርሱ ቃሌን ንቋል ደግሞም ትዕዛዛቴን ተላልፏል፣ ያ ሰው ሙሉ ለሙሉ ከህዝቡ ተለይቶ ይጥፋ፡፡ ኃጢአቱ በራሱ ላይ ይሆናል፡፡”
32የእስራኤል ህዝቦች በምድረ በዳ በነበሩበት ጊዜ፣ አንድ ሰው በሰንበት ቀን እንጨት ሲለቅም አገኙት፡፡
33ያገኙት ሰዎች ወደ ሙሴ፣ ወደ አሮንና ወደ መላው ማህበረሰብ አቀረቡት፡፡
34በእርሱ ላይ ምን መደረግ እንዳለበት የታወቀ ህግ ስላልበረ በጥበቃ ሥር አቆዩት፡፡
35ከዚያ ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “በእርግጥ ሰውየው መገደል አለበት፡፡ መላው ማህበረሰብ ከሰፈር ውጭ በድንጋይ ይውገረው፡፡”
36ስለዚህም መላው ማህበረሰብ ሰውየውን ከሰፈር ውጭ አውጥተው ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው እስኪሞት ድረስ ወገሩት፡፡
37ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
38“ለእስራኤል ትውልዶች በየለብሳቸው ጠርዝ ዘርፍ እንዲያስሩ ንገራቸው፣ ዘርፎቹን በእያንዳንዱ ጠርዝ በሰማያዊ ገመድ እንዲያንጠለጥሉ እዘዛቸው፡፡ በሚቀጥሉት ትውልዶቻቸው ሁሉ ይህን ያድርጉ፡፡
39ይህንን ስትመለከቱ፣ በትዕዛዛት ሁሉ፣ እንድትሄዱ፣ የራሳችሁን ልቦናና እይታ ሳትከተሉ ቀድሞ ታደርጉት ከነበረው መንፈሳዊ አመንዝራነት ለመመለስ ይህ ለእናንተ ልዩ ማስታወሻ ይሆናችኋል፡፡
40ትዕዛዛቶቼን ሁሉ እንድትጠብቁና አስተዋዮች እንድትሆኑ ይህን አድርጉ፣ ደግሞም ቅዱሳንና ለእኔ ለአምላካችሁ የተለያችሁ ትሆናላች፡፡
41አምላካችሁ እሆን ዘንድ፣ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡”
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።