1“በዚያን ምሽት ማህበረሰቡ በሙሉ ድምጹን ከፍ አድርጎ አለቀሰ፡፡
2እስራኤል ሰዎች ሁሉ ሙሴንና አሮንን ነቀፉ፡፡ መላው ማህበረሰብ እንዲህ አሏቸው፣ “በግብጽ ምድር ብንሞት ይሻለን ነበር፡፡ ውይም ምነው በዚህ በረሃ በሞትን ኖሮ!
3ያህዌ ለምን በዚህ ምድረበዳ በሰይፍ እንድንሞት ወደዚህ ምድር አመጣን? ሚስቶቻችንና ትናንሽ ልጆቻችን የተጠቁ ይሆናሉ፡፡ ወደ ግብጽ መመለስ አይሻለንምን?”
4እርስ በእርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፣ “ሌላ መሪ እንምረጥ፣ እናም ወደ ግብጽ እንመለስ፡፡”
5ከዚያ ሙሴና አሮን በእስራኤል ህዝብ በማህበረሰቡ ጉባኤ ፊት በግምባራቸው ተደፉ፡፡
6ምድሪቱን ለማየት ከወጡት ውስጥ ከነበሩት የነዌ ልጅ ኢያሱና የዩፎኒ ልጅ ካሌብ ልብሳቸውን ቀደዱ፡፡
7እስራኤል ሰዎች መላው ማህበረሰብ እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፣ “በውስጧ ያለፍነውና የተመለከትናት ምድር በጣም መልካም መድር ናት፡፡
8ያህዌ በእኛ ደስ ከተሰኘ፣ ወደዚህች ምድር ያስገባናል ደግሞም እርሷን ለእኛ ይሰጠናል፡፡ ምድሪቱ ወተትና ማር የምታፈስ ናት፡፡
9ነገር ግን በያህዌ ላይ አታምጹ፣ ደግሞም በምድሪቱ የሚኖሩትን ህዝቦች አትፍሩ፡፡ በቀላሉ እንደ ምግብ እንበላቸዋለን፡፡ ጥላቸው ከእነርሱ ተገፏል፣ ምንያቱም ያህዌ ከእኛ ጋር ነው፡፡ እነርሱን አትፍሯቸው”፡፡
10ነገር ግን መላው ማህበረሰብ እስከ ሞት ሊወግሯቸው ተነሰቡቸው፡፡ ከዚያ የያህዌ ክብር በመገናኛው ድንኳን ለመላው የእስራኤል ሰዎች ታየ፡፡
11ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “ይህ ህዝብ እስከ መቼ እኔን ይንቀኛል በመካከላቸው በሃይሌ ያደረኳቸውን ምልክቶች እያዩ እንኳን እስከ መቼ በእኔ አያምኑም
12በበሽታ እመታቸዋለሁ፣ ወደ ርስታቸው አላስገባቸውም፣ ሆኖም ከአንተ ከራስህ ነገድ ከእነርሱ ይልቅ ታላቅና ሃያል ህዝብ አበጃለሁ፡፡”
13ሙሴ ያህዌን እንዲህ አለው፣ “ይህን ብታደርግ፣ ግብጻዊያን ስለዚህ ነገር ይሰማሉ፣ ምክንያቱም አንተ ይህን ህዝብ በኃይልህ ከእነርሱ አድነሃቸዋል፡፡
14ለዚህች ምድር ነዋሪዎች ይህንን ይናገራሉ፡፡ አንተ ያህዌ፣ ከዚህ ህዝብ ጋር እንደሆንክ እነርሱ ሰምተዋል፣ ምክንያቱም አንተ ፊት ለፊት ታይተሃል፡፡ የአንተ ደመና በእኛ ህዝብ ላይ ሆኗል፡፡ አንተ በእነርሱ ፊት በቀን በደመና አምድ በምሽት በእሳት አምድ ሄደሃል፡፡
15አሁን ይህንን ህዝብ እንደ አንድ ሰው ብትገድል፣ ዝናህን የሰሙ ህዝቦች እንዲህ ይላሉ፣
16‘ያህዌ ይህንን ህዝብ ሊሰጣቸው ወደ ማለላቸው ምድር ሊያስገባቸው ባለመቻሉ ምክንያት፣ በምድረበዳ ገደላቸው፡፡
17አሁን፣ እኔ እለምንሃለሁ፣ ታላቁን ሀይልህን ተጠቀም፡፡ አንተ እንዲህ ብለሃልና፣
18‘ያህዌ ለቁጣ የዘገየ ነው፣ በቃል ኪዳን ታማኝነቱ የተትረፈረፈ ነው፡፡ እርሱ በደልና መተላለፍን ይቅር ይላል፡፡ የአባቶችን ኃጢአት ቅጣት እስከ ሁለትና ሶስት ትውልድ በልጆቻቸው ላይ ሲያመጣ በደላቸውን በምንም አይነት ሳይቀጣ አይቀርም፡፡’
19የቃል ኪዳን ታማኝነነትህን ታላቅነት ስላልተረዳ ይህ ህዝብ ይበድላል፣ በግብጽ ከነበሩበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ሁልጊዜም ይቅር እንዳልካቸው ይቅር እንድትል እለምንሃለሁ፡፡”
20ያህዌ እንዲህ አለው፣ “ልመናህን ሰምቼ ይቅር ብያቸዋለሁ፣
21ነገር ግን፣ እኔ ሕያው ስለሆንኩና መላው ምድርም በእኔ ክብር የተሞላች ስለሆነች፣
22ክብሬን፣ በግብጽና በምድረበዳው ጉዟቸው ያደረኳቸውን የሀይሌን ምልክቶች አይተው እነዚያ ህዝቦች ሁሉ - እስከ አሁን ድረስ በእነዚህ አስር ጊዜ ተፈታተኑኝ እንጂ ድምጼን አልሰሙም፡፡
23ስለዚህ ለአባቶቻቸው የማልኩላቸውን ምድር በፍጹም አያዩም፡፡ እኔን ከናቁት ውስጥ አንዳቸውም ምድሪቱን አያዩም፣
24ከባሪያዬ ከካሌብ በስተቀር፣ ምክንያቱም እርሱ የተለየ መንፈስ አለው፡፡ እርሱ እኔን በሙሉ ልቡ ተከትሎኛል፣ ሊያያት ወደሄደበት ምድር እኔ እመጣዋለሁ፡፡ የእርሱ ትውልዶች ይወርሷታል፡፡
25(አሁን አማሌቃዊያንና ከነዓናውያን በሸለለቆው ይኖራሉ፡፡) ነገ ተመልሳችሁ በሸምበቆው ባህር በኩል ወደ ምድረ በዳው ሂዱ፡፡”
26ህዌ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፣
27”እኔን የሚነቅፈውን ይህን ክፉ ማህበረሰብ እስከ መቼ እታገሳለሁ የእስራኤል ሰዎች በእኔ ላይ ሲያጉረመርሙ ሰምቻለሁ፡፡
28እንዲህ በላቸው ‘እኔ ሕያው ነኝ’ ይላል ያህዌ፣ ‘እኔ እየሰማሁ፣ የተናገራችሁትን፣ ያንኑ አደርግባችኋለሁ፡፡
29በድናችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃል፣ እናንተ በእኔ ላይ ያጉረመርማችሁ ሁላችሁም፣ በህዝብ ቆጠራው የተቆጠራችሁ ሃያ አመትና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያላችሁ ሰዎች ሁሉ ትሞታላችሁ፡፡
30መኖሪያችሁ ትሆን ዘንድ እንደምሰጣችሁ ቃል ወደገባሁላችሁ ምድር ከዮፍኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በስተቀር ከእናንተ አንዳችሁም አትገቡም፡፡
31ነገር ግን ተጠቂ ይሆናሉ ያላችኋቸው ትንንሽ ልጆቻችሁን፣ እኔ ወደ ምድሪቱ አስገባቸዋለሁ፡፡ እናንተ የናቃችኋትን ምድር እነርሱ ይገቡባታል!
32እናንተ ግን፣ በድናችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃል፡፡
33ልጆቻችሁ ለአርባ አመታት በምድረዳ ይንከራተታሉ፡፡ በረሃው ሁላችሁንም እስኪገድላችሁ ድረስ፣ እነርሱ እናንተን የአመጽ ድርጊቶች ዋጋ ይከፍላሉ፡፡
34ምድሪቱን በተመለከታችሁባቸው አርባ ቀናት ልክ፣ ለአርባ አመታት ስኃጢአታችሁ መከራ ትቀበላላችሁ - ለእያንዳንዱ ቀን አንድ አመት፣ እናም የእኔ ጠላት መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ ታውቃላችሁ፡፡
35እኔ ያህዌ፣ ይህንን ተናግሬያለሁ፡፡ በእኔ ላይ በተነሱ በዚህ ክፉ ማህበረሰብ ላይ በእርግጥ ይህን አደርጋሁ፡፡ በዚህ ምድረ በዳ ይጠፋሉ፡፡ በዚህ ስፍራ ይሞታሉ፡፡”
36-37ስለዚህ ሙሴ ምድሪቱን እንዲያዩ የላካቸው ሰዎች ሁሉ በያህዌ ፊት በወረርሽኝ አለቁ፡፡ እነዚህ ሰዎች ስለምድሪቱ መጥፎ ወሬ ይዘው የተመለሱ ነበሩ፡፡ ይህም መላው ማህበረሰብ በሙሴ ላይ እንዲያጉረመርም አደረገ፡፡
38ምድሪቱን ለማየት ከሄዱት ሰዎች መሀል፣ የነዌ ልጅ ኢያሱና የዩፎኒ ልጅ ካሌብ ብቻ በህይወት ቀሩ፡፡
39ሙሴ እነዚህን ቃላት ሁሉ ለእስራኤል ሰዎች ሲናገር፣ በጥልቅ አዘኑ፡፡
40ማልደው ተነስተው ወደ ተራራው ጫፍ ወጥተው እንዲህ አሉ፣ “እነሆ፣ አሁን በዚህ አለን፣ ደግሞም ያህዌ ቃል ወደገባልን ስፍራ እንሄለን፣ እኛ በድለናል፡፡”
41ነገር ግን ሙሴ እንዲህ አለ፣ “ለምን አሁን የያህዌን ትእዛዝ ትሽራላችሁ ድል አይቀናችሁም፡፡
42አትውጡ፣ ምክንያቱም በጠላቶቻችሁ እንዳትሸነፉ ሊጠብቃችሁ ያህዌ ከእናንተ ጋር አይደለም፡፡
43በዚያ አማሌቃዊያንና ከነዓናዊያን አሉ፣ እናንተም በሰይፍ ታልቃላችሁ ምክንቱም ያህዌን ከመከተል ፊታችሁን መልሳችኋል፡፡ ስለዚህ እርሱ ከእናንተ ጋር አይሆንም፡፡”
44እነርሱ ግን ወደ ተራራማው አገር ለመሄድ በድፍረት ተነሱ፣ ሆኖም፣ ሙሴም ሆነ የያህዌ የቃል ኪዳኑ ታቦት ከሰፈር አብሯቸው አልወጣም፡፡
45ከዚያ አማሌቃዊያን ወርደው መጡ፣ እንደዚሁም በተራሮቹ የሚኖሩ ከነዓናዊያን መጡባቸው፡፡ እነርሱም እስራኤላውያንን አጠቋቸው እስከ ሔርማ መንገድ ድረስ አሳደዷቸው፡፡