1ዚያም ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
2”ለእስራኤላውያን የሰጠኋቸውን የከነዐንን ምድር እንዲያዩ ጥቂት ሰዎችን ላክ፡፡ ከአባቶቻቸው ከእያንዳንዱ ነገድ አንድ ሰው ላክ፡፡ ከመሀላቸው የሚላከው እያንዳንዱ ሰው መሪ መሆን አለበት፡፡”
3ሙሴ የያህዌን ትእዛዝ እንዲያደርጉ ከፋራን ምድረ በዳ ላካቸው፡፡ ሁሉም ከእስራኤል ሰዎች መሃል የተመረጡ መሪዎች ነበሩ፡፡
4ስሞቻቸው እነዚህ ነበሩ፡ ከሮቤል ነገድ፣ የዘኩር ልጅ ሳሙኤል፡፡
5ከስምዖን ነገድ፣ የሱሬ ልጅ ሰፈጥ፡፡
6ከይሁዳ ነገድ፣ የዩፎኒ ልጅ ካልብ፡፡
7ከይሳኮር ነገድድ የዮሴፍ ልጅ ይግአል፡፡
8ከኤፍሬም ነገድ፣ የነዌ ልጅ አውሴ፡፡
9ከብንያም ነገድ፣ የራፋ ልጅ ፈልጢ፡፡
10ከዛብን ነገድ፣ የሰዲ ልጅ ጉዲኤል፡፡
11ከዮፍ ትውልዶች፣ ይህም፣ ከምናሴ ነገድ ነው፣ የሱሲን ልጅ ጋዲ፡፡
12ከዳን ነገድ፣ የገማሊ ልጅ ዓሚኤል፡፡
13ከአሴር ነገድ፣ የሚካኤል ልጅ ሰቱር፡፡
14ከንፍታሌም ነገድ፣ የያቢ ልጅ ናቢ፡፡
15ከጋድ ነገድ፣ የማኪ ልጅ ጉዲኤል ነበሩ፡፡
16ምድሪቱን እንዲያዩ ሙሴ የላቸው ሰዎች ስሞች እነዚህ ነበሩ፡፡ ሙሴ የነዌ ልጅ አውሴን፣ ኢያሱ ብሎ ጠራው፡፡
17ሙሴ እነርሱ የከነዓንን ምድር እንዲያዩ ላካቸው፡፡ እንዲህ አላቸው፣ “ከነጌብ ጀምራችሁ እስከ ተራራማው አገር ድረስ ሂዱ፡፡
18ምድሪቱ ምን እንደምትመስል ተመልከቱ፡፡ በዚያ የሚኖሩ ሰዎችን እዩ፣ ጠንካሮች ወይም ደካሞች መሆናቸውን፣ እና ጥቂት ወይም ብዙ መሆናቸውን ተመልከቱ፡፡
19የሚኖሩባት ምድር ምን እንደምትመስል እዩ፡፡ መልካም ናት ወይስ መጥፎ? በዚያ ምን አይነት ከተሞች አሉ? ሰፈር አይነት ናቸው? የተቀጠሩ ከተሞችስ ናቸውን?
20ምድሪቱ ምን እንደምትመስል እዩ፣ ለእርሻ የተመቸች ናት ወይስ አይደለችም፣ በዚያ ዛፎች አሉ ወይስ የሉም፡፡ ብርቱ ሁኑና ከምድሪቱ ምርት ከየአይነቱ ይዛችሁ ኑ፡፡” ወቅቱ የወይን ፍሬ ማፍራት የጀመረበት ነበር፡፡
21ስለዚህ ሰዎቹ ወጥተው በሌለቦ ሐማት አጠገብ፣ ከጺን ምድረበዳ እስከ ሌቦ ድረስ ምድሪቱን ተመለከቱ፡፡
22ከኔጌብ ወጥተው እስከ ኬብሮን ደረሱ፡፡ ከዔናቅ ነገድ ዝርያ የሆኑ የአኪመን፣ የሴሲና፣ እና የተላሚ ነገዶች በዚያ ነበሩ፡፡ ኬብሮን ግብጽ ውስጥ የተመሰተረችው ከከጣኔዎስ ሰባት አመት ቀደም ብላ ነበር፡፡
23ኤሽኮል ሸለቆ ሲደርሱ፣ የወይን ዘለላ የያዘ ቅርንጫፍ ቆረጡ፡፡ ከቡድናቸው በሁለቱ መሃል በበትር አድርገው የወይኑን ዘለላ ተሸከሙት፡፡ እንደዚሁም ሮማንና በለስም አመጡ፡፡
24የእስራኤል ሰዎች በዚየ ከቆረጡት የወይን ዘለላ የተነሳ፣ ያቺ ስፍራ የኤሽኮል ሸለቆ ተብላ ተጠራች፡፡
25ምድሪቱን መርምረው ከአርባ ቀናት በኋላ ተመለሱ፡፡
26የተላኩት ሰዎች፣ ሙሴና አሮን እንዲሁም መላው የእስራኤል ማህበረሰብ ወዳሉበት በፋራን ምድረበዳ ወደምትገኘው ወደ ቃዴስ መጡ፡፡ ወደ እነርሱና ወደ መላው ማህበረሰብ ተመልሰው መጥተው፣ የምድሪቱን ፍሬ አሳይዋቸው፡፡
27ሙሴን እንዲህ አሉት፣ “ወደ ላከን ምድር ደረስን፡፡ በእርግጥም ወተትና ማር ታፈሳለች፡፡ ከምድሪቱ ምርት እነሆ፡፡
28ሆኖም፣ በዚያ የሚኖሩ ሰዎች ብርቱዎች ናቸው፤¨ከተሞቹም የተመሸጉና ትላልቅ ናቸው፡፡ ደግሞም በዚያ የዔናቅን ዝርያዎችም አይተናል፡፡
29አማሌቃውያን በነጌብ ይኖራሉ፡፡ ኬጢያውያን፣ ኢያቡሳዊያን፣ እና አሞራዊያን በተራራማው አገር ይኖራሉ፡፡ ከነዓናዊያን በባህሩ አቅራቢያ በዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ ይኖራሉ፡፡”
30ከዚያ ካሌብ በሙሴ ዙሪያ የተሰበሰቡበትን ሰዎች ሊያበረታታቸው ተነሳ፣ እንዲህም አለ፣ “በአንድ ጊዜ ተነስተን እንውጣና ምድራቸውን እንውረስ፣ ምክንያቱም በሚገባ ልናሸንፍ እንችላለን፡፡”
31ግን ከእርሱ ጋር የሄዱት ሌሎች ሰዎች እንዲህ አሉ፣ “እኛ ሰዎቹን ማጥቃት አንችልም ምክንያቱም እነርሱ ከእኛ ይልቅ ጠንካሮች ናቸው፡፡”
32ስለዚህም ስለተመለከቷት ምድር በእስራኤለ ሰዎች መሀል ተስፋ አስቆራጭ ወሬ አሰራጩ፡፡ እንዲህም አሉ፣ “የተመለከትናት ምድር በላይዋ የሚኖሩትን የምትበላ ናት፡፡ በዚያ ያየናቸው ሰዎ ሁሉ ቁመተ ረጃጅም ሰዎች ናቸው፡፡
33በዚያ የኤናቅ ዝርያዎችን አይተናል፣ ከግዙፋኑ ሰዎች የመጡትን ግዙፎቹን ሰዎች አይተናል፡፡ ከእነርሱ ጋር ስንተያይ፣ በእኛ በራሳችን ዐይን እንደ አንበጣ ነበርን፣ ደግሞም በእነርሱም ዐይን እንደዚሁ ነበርን፡፡”