መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ዘኁልቁ 12

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1“ከዚያ ማርያም እና አሮን ሙሴ ባገባት ኩሻዊ ሴት ምክንያት በሙሴ ላይ በተቃውሞ ተናገሩ፡፡
2እንዲህም አሉ፣ “ያህዌ የተናገረው ከሙሴ ጋር ብቻ ነውን? ከእኛስ ጋር አልተናገረምን?” ያህዌ እነርሱ የተናገሩትን ሰማ፡፡
3ሙሴ ፣ በምድር ላይ ከሚገኝ ከማንኛውም ሰው ይልቅ በጣም ትሁት ሰው ነበር፡፡
4ወዲያውኑ ያህዌ ከሙሴ፣ ከአሮንና ማርያም ጋር ተናገረ “እናንተ ሶስታችሁ ወደ መገናኛው ድንኳን ውጡና ኑ፡፡” ስለዚህም ሶስቱም ወጥተው መጡ፡፡
5ከዚያም ያህዌ በደመና አምድ ወረደ፡፡ በድንኳኑ መግቢያ ቆሞ አሮንንና ማርያምን ጠራቸው፡፡ ሁለቱም ወደ ፊት ቀረቡ፡፡
6ያህዌ እንዲህ አለ፣ “አሁን ቃሎቼን ስሙ፡፡ አንድ የእኔ ነብይ በመካከላችሁ ሲሆን፣ ራሴን፣ በራዕይ እገልጥለታለሁ፣ በህልምም እናገረዋለሁ፡፡
7አገልጋዬ ሙሴ ግን እንደዚያ አይደለም፡፡ እርሱ በቤቴ ላይ ሁሉ የታመነ ነው፡፡
8እኔ ከመሴ ጋር በቀጥታ እናገራሁ፣ በራዕይ ወይም በዘይቤ አይደለም፡፡ እርሱ የእኔን መልክ ያያል፡፡ ስለዚህ በአገልጋዬ በሙሴ ላይ ስትናገሩ ለምን አልፈራችሁም?”
9የያህዌ ቁጣ በእነርሱ ላይ ነደደ፣ ከዚያም ትቷቸው ሄደ፡፡
10ደመናው ከድንኳኑ ላይ ተነሳ፣ እናም ማርያም በድንገት በለምጽ ተመታች እንደ በረዶ ነጭ ሆነች፡፡ አሮን ወደ ማርያም ዞር ብሎ ሲመለከታት በልምጽ መመታቷን አየ፡፡
11አሮን ሙሴን እንዲህ አለው፣ “ጌታዬ ሆይ፣ እባክህን በአንተ ላይ የፈጸምነውን ይህን በደል አትቁጠርብን፡፡ በስንፍና ተናግረናል፣ ደግሞም በድለናል፡፡
12እባክህን ከእናቱ ማህጸን ሲወጣ ጭንጋፍ ሆኖ እንደ ተወለደ ከፊል አካሉ እንደተበላ ሆና አትተዋት፡፡”
13ስለዚህም ሙሴ ወደ ያህዌ ጮኸ፡፡ እንዲህም አለ፣ “እግዚአብሔር ሆይ፣ እባክህ፣ እባክህ ፈውሳት፡፡”
14ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ “አባቷ በፊቷ ላይ ቢተፋባት፣ ለሰባት ቀናት በሀፍረት ትቆያለች፡፡ ከሰፈር ውጭ ለሰባት ቀናት ዝጋባት፡፡ ከዚያ በኋላ መልሰህ አምጣት፡፡”
15ስለዚህም ማርያም ከሰፈር ውጭ ለሰባት ቀናት ተዘጋባት፡፡ እርሷ ወደ ሰፈር እስክትመለስ ድረስ ህዝቡ ጉዞ አላደረገም፡፡
16ከዚያ በኋላ፣ ህዝቡ ከሐዴሮት ተነስቶ ተጓዘና በፋራን ምድረበዳ ሰፈረ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።