1ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
2”ሁለት የብር መለከቶች አብጁ፡፡ በብር ቀጥቅጠህ አብጃቸው፡፡ መለከቶቹን ማህበረሰቡን በጋራ ለመጥራትና ከመንደሮቸው እንዲንቀሳቀሱ ጥሪ ለማሰማት ተጠቀምባቸው፡፡
3ካህናቱ ማህበረሰቡን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ በፊትህ ለመሰብሰብ መለኮቶቹን ይንፉ፡፡
4ካህናቱ አንድ መለከት ብቻ ከነፉ፣ የእስራኤል ነገድ መሪዎች ይሰበስቡ፡፡
5ከፍ ባለ ድምጽ ስትነፉ፣ በስተምስራቅ የሰፈሩት ጉዟቸውን ይጀምሩ፡፡
6ለሁለተኛ ጊዜ ከፍ ባለ ድምጽ ስትነፋ በደቡብ በኩል የሰፈሩት ጉዟቸውን ይጀምሩ፡፡ ለጉዟቸው ከፍ ያለ የመለከት ድምጽ ያሰሙ፡፡
7ማህበረሰቡ በአንድነት ሲበሰበሰብ፣ መለከቶች ይነፉ ነገር ግን ድምጹ ከፍ አይበል፡፡
8የካህኑ የአዘሮን ልጆች፣ መለኮቶቹን ይንፉ፡፡ በትውልዶቻችሁ ሁሉ ዘንድ ይህ ለእናንተ ሁልጊዜም ስርዓት ይሆናል፡፡
9በሚወሯችሁ ተቃዋሚዎቻች ላይ በምድራች ለጦርነት ስትወጡ፣ ለማንቂያ የመለከት ድምጽ ታሰማላችሁ፡፡ እኔ፣ አምላካችሁ ያህዌ፣ አስባችኋለሁ ደግሞም ከጠላቶቻችሁ አድናችኋለሁ፡፡
10እንደዚሁም፣ በመደበኛ ባዕላቶቻችሁም ሆነ በወራቶች መጀመሪያ ላይ በክብረ በዓል ወቅት ለሚቃጠል መስዋዕቶቻችሁ ክብርና በህብረት መስዋዕቶቻችሁ መስዋዕቶች ላይ መለኮቶችን መንፋት አለባች፡፡ እነዚህ እናንተ የእኔ የአምላካችሁ ለመሆናችሁ መታሰቢያ ሆነው ያገለግላሉ፡፡ እኔ አምላካችሁ ያህዌ ነኝ፡፡”
11በሁለተኛው አመት፣ በሁለተኛው ወር፣ በወሩ ሀያኛ ቀን ደመናው ከቃል ኪዳኑ ምስክር ማደሪያ ላይ ተነሳ፡፡
12የእስራኤል ሰዎች ከሲና ምድረበዳ ተነስተው ጉዟቸውን ቀጠሉ፡፡ ደመናው በፋራን ምድረ በዳ ውስጥ ቆመ፡፡
13የመጀመሪያ ጉዟቸው፣ በሙሴ በኩል የተሰጣቸውን የያህዌን ትዕዛዝ ተከትለው አደረጉ፡፡
14በይሁዳ ትውልዶች ዓርማ ስር ያለው ሰፋሪዎች በመጀመሪያ ተንቀሳቀሱ፡፡ የይሁዳን ሠራዊት የሚመራው የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበር፡፡
15የይሳኮርን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራው የሶገር ልጅ ናትናኤል ነበር፡፡
16የዛብሎንን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራው የኬሎን ልጅ ኤልያብ ነበር፡፡
17የማደሪያ ድንኳኑን የተሸከሙት የጌድሶን እና የሜራሪ ትውልዶች፣ ማደሪያ ድንኳኑን ነቅለው ጉዟቸውን ጀመሩ፡፡
18ቀጥሎ፣ በሮቤል ሰፈር ሰራዊት ዓርማ ስር የነበሩት ጉዟቸውን ቀጠሉ፡፡ የሮቤልን ሰራዊት የሚመራው የሶዲዮር ልጅ ኤሊሱር ነበር፡፡
19የስምዖንን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራዊ የሱሪስዓይ ልጅ ስለሚኤል ነበር፡፡
20የጋድን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራው የራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ ነበር፡፡
21ቀዓታውያን ተነሱ፡፡ እነርሱ የቅድስተ ቅዱሳኑን ቅዱስ ዕቃዎች ተሸከሙ፡፡ ቀዓታውያን ቀጣዩ ሰፈር ከመድረሳቸው አስቀድሞ ሌሎች ማደሪያ ድንኳን ይተክላሉ፡፡
22የኤፍሬምን ሰራዊት የሚመራው የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ ነበር፡፡
23የምናሴን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራው የፍዳሱር ልጅ ገማልኤል ነበር፡፡
24የብንያምን ትውልዶች ሠራዊት የሚመራው የጋዴዮን ልጅ አቢዳን ነበር፡፡
25በዳን ትውልዶች ዓርማ ስር የሰፈሩት ሠራዊቶች በመጨረሻ ይወጣሉ፡፡ የዳንን ሰራዊት የሚመራው የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር ነበር፡፡
26የአቤርን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራው የኤክራን ልጅ ፋግኤል ነበር፡፡
27የንፍታሌምን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራው የዔናን ልጅ አኪሬ ነበር፡፡
28የእስራኤል ሰዎች ሰራዊቶች ጉዟቸውን ያደረጉት በዚህ መልክ ነው፡፡
29ሙሴ ከምድያማዊው የራጉኤል ልጅ ከአባብ ጋር ተነጋገረ፡፡ ራጉኤል የሙሴ ሚስት አባት ነበር፡፡ ሙሴ ከአባብ ጋር ተነጋገረ እንዲህም አለ፣ “ያህዌ እሰጣችኋለሁ ወዳለን ስፍራ እየተጓዝን ነው፡፡ ያህዌ እንዲህ ብሎን ነበር፣ ‘እኔ ለእናንተ የተናገርኩትን እርሷኑ ስፍራ እሰጣችኋለሁ፡፡’ አንተ ከእኛ ጋር አብረኸን ና እኛም መልካም እናደርግልሃለን፡፡ ያህዌ ለእስራኤል መልካም ለማድረግ ቃል ገብቷል፡፡”
30አባብ ግን ሙሴን እንዲህ አለው፣ “እኔ ከአንተ ጋር አልሄድም፡፡ እኔ ወደ ገዛ ምድሬና ወደ ራሴ ህዝብ እሄዳለሁ፡፡”
31ከዚያም ሙሴ እንዲህ ሲል መለሰ፣ “እባክህን ከእኛ አትለይ፡፡ በበረሃ እንዴት መስፈር እንደሚቻል ታውቃለህ፡፡ ስንሰፍር ልትመለከተን ይገባል፡፡
32ከእኛ ጋር ብትሄድ፣ ያህዌ ለእኛ የሚያደርግልንን በጎነት ያንኑ እኛም ለአንተ እናደርግልሃለን፡፡”
33ከያህዌ ተራራ ተነስተው ለሶስት ቀናት ተጓዙ፡፡ የያህዌ የቃልዳኑ ታቦት የሚያርፍበትን ስፍራ እንዲያገኙ ለመፈለግ ለሶስት ቀናት በፊታቸው ተጓዘ፡፡
34ሲጓዙ የያህዌ ደመና በቀን ብርሃን በላያቸው ነበር፡፡
35ታቦቱ በተነሳበት ጊዜ ሁሉ፣ ሙሴ እንዲህ ይላል፣ “ያህዌ ሆይ፣ ተነስ፡፡ ጠላቶችህን በትን፡፡ የሚጠሉህ ከአንተ እንዲሸሹ አድርግ፡፡”
36ታቦቱ በቆመ ጊዜ ሁሉ፣ ሙሴ “ያህዌ ሆይ፣ ብዙ አስር ሺህ ወደሚሆኑት እስራኤላውያን ተመለስ” ይል ነበር፡፡