መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ነህምያ 7

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ቅጥሩ ተሰርቶ ከተጠናቀቀና በሮቹም በስፍራቸው ከቆሙ በኋላ፣ የቤተ መቅደሱ ጠባቂዎችና የዝማሬ አባላቱ እንዲሁም የተቀሩት የሌዊ ትውልዶች በየስራ መደባቸው ተመደቡ፡፡
2ወንድሜን አናኒን የኢየሩሳሌም ገዥ አድርጌ ሾምኩት፡፡ እርሱ ከብዙ ሌሎች ሰዎች ይልቅ ታማኝና እግዚአብሔርን የሚፈራና የሚያከብር ሰው ነበር፡፡ በተጨማሪም ሐናንያ በኢየሩሳሌም ለሚገኘው የከተማይ ግንብ አዛዥ ሆኖ ተሾሙ፡፡
3እነርሱን እንዲህ አልኳቸው፣ “ፀሀይ ሞቅ እስክትል የኢየሩሳሌምን መግቢያ በሮች አትክፈቱ፡፡ በሮችን የምትቆልፉትና የበሮችን መቀርቀሪያዎች የምትዘጉት በር ጠባቂዎች መግቢያዎችን እየጠበቁ ሳለ ነው፡፡” አንዳንድ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሰዎችን ዘቦችና በከተማዋ ዙሪያ ያሉ ማረፊያዎችን ጠባቂዎች እንዲያደረጓቸው፤ እንዲሁም አንዳንዶችን ከራሳቸው ቤቶች አቅራቢያ ጠባቂ እንዲያደረጓቸው ነገርኳቸው፡፡
4የኢየሩሳሌም ከተማ ሰፊ ናት፣ ነገር ግን በዚያን ጊዜ በከተማዋ ብዙ ህዝብ አይኖርም ነበር፣ እንዲሁም ከቤቶቹ አንዱንም እንደገና አልገነቡም ነበር፡፡
5እግዚአብሔር መሪዎችንና ሹማምንቱን እንዲሁም ሌሎች ሰዎችን እንድሰበስብ እና በየቤተሰባቸው መዛግብት እንድጽፍ አሳብ በልቤ አኖረ፡፡ እንደዚሁም ወደ ኢየሩሳሌም የተመለሱትን የመጀመሪያዎቹን ተመላሾች ዝርዝር አገኘሁ፡፡ በእዚያ መዛግብት ተጽፎ ያገኘሁት ይህንን ነው፡፡
6”ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ሌሎች ስፍራዎች የተመለሱ ሰዎች ዝርዝር ይህ ነው፡፡ እነርሱ ባቢሎን ውስጥ ይኖሩ ነበር፡፡ ናቡከደነጾር ወደዚያ ወስዷቸው ነበር፡፡ እነርሱ ወደ ኢየሩሳሌምና ይሁዳ ተመለሱ፡፡ እያንዳንዱ ተመላሽ አባት ከልደት በፊት ይኖርበት ወደነበረበት ወደ ራሱ ከተማ ተመልሶ ሄደ፡፡
7እነርሱ ከዘሩባቤል፣ ከኢያሱ፣ ከነህምያ፣ ከአዛርያስ፣ ከረዓምያ፣ ከነሐማኒ፣ ከመርዶክዮስ፣ ከላሶን፣ ከሚስጴሬት፣ ከጉዋይ፣ ከነሑም፣ እና ከዓና ጋር ተመልሰው መጡ፡፡ ከህዝቡ የተመለሱት የወንዶች ቁጥር ዝርዝር እንደሚከተለው ነበር፡
8ከፋሮስ ትውልዶች 2172
9ከሰፋጥያስ ትውልዶች 372
10ከኤራ ትውልዶች፣ 652
11ሞዓብ ትውልዶች፣ የኢያሱና ኢዮብአብ ትውልዶች 2818
12ከኤላም ትውልዶች 1254፣
13ከዛቱዕ ትውልዶች፣ 845፣
14ከዘካይ ትውልዶች፣ 845፣
15ትውልዶች፣ 648፣
16ከቤባይ ትውልዶች፣ 628፣
17ከዓዝጋድ ትውልዶች፣ 2322፣
18ከአዶኒቃም ትውልዶች፣ 667፣
19ከበጉዋይ ትውልዶች፣ 2067፣
20ከዓዲን ትውልዶች፣ 655፣
21ከአጤር ትውልዶች ሌላ ስማቸው ሕዝቅያስ ከሚባለው፣ 98፣
22ከሐሱም ትውልዶች፣ 328
23ከቤሳይ ትውልዶች፣ 324፣
24ከሐሪፍ ትውልዶች፣ ሌላ ስማቸው ጆራህ ከሚባለው፣ 112
25ከገባዖን ትውልዶች 95
26አባቶቻቸው በእነዚህ ከተሞች የኖሩ ወንዶችም ደግሞ ተመለሱ ከቤተልሔምና ከነጦፉ የመጡ ወንዶች፣ 188፡፡
27ከዓናቶት የመጡ ወንዶች፣ 128 ነበሩ
28ከቤት አዛምት የመጡ ወንዶች 42፣
29ከቂርያት ይዓሪም ከከፈሪና ከብኤሮት 743 ወንዶች
30ኮራማና ከጌባ 621 ወንዶች
31122 ወንዶች ነበሩ
32ከቤቴልና ከጋይ፣ 123 ወንዶች
33ከናባው፣ 52 ወንዶች
34ከኤላም፣ 1254 ወንዶች
35ከካሪም 320 ወንዶች ነበሩ
36ከኢያሪኮ፣ 345 ወንዶች
37ከሎድ፣ ሐዲድና አኖ 721 ወንዶች ነበሩ እነዚህ ካህናትም ደግሞ ተመልሰዋል
38ከሴናዓ ትውልድ 3930 ነበሩ
39የኢያሱ ቤተሰብ የሆኑ፣ የዮዳኤ ትውልዶች፣ 973
40ከኢሜር ትውልዶች 1052፣
41ከፋስኮር ትውልዶች፣ 1247፣
42ከካሪም ትውልዶች፣ 1017
43ከሌዋውያን ትውልዶች የተመለሱት እነዚህ ነበሩ፣ የኢያሱ፣ ቀደምኤል፣ ቤትኢ እና የሆዳይዋ ትውልዶች 74 ናቸው
44ከመዘምራኑ ትውልዶች የተመለሱት እነዚህ ነበሩ ከኤሳፍ ትውልድ 148
45እንዲሁም ከሰሎም፣ አጤር፣ ጤልሞን፣ ዓቁብ፣ ሐጢጣ፣ እና ሶባይ ትውልዶች የተመለሱ 138 የቤተ መቅደሱ በር ጠባቂዎች ናቸው፡፡
46የተመለሱት የቤተ መቅደሱ ሰራተኞች የእነዚህ ሰዎች ትውልዶች ነበሩ የሲሐ፣ ሐሡፋ፣ ጠብዖት
47የኬረስ፣ ሲዓዓ ሩዶን
48የልባና አገባ፣ ሰሞላይ
49የሐናን ጌዱል፣ ጋሐር፣
50ራያ፣ ራአሰን፣ ኔቆዳ
51ጋሴም፣ አዛ፣ ፋሴሐ
52ቤሳይ፣ ምዑኒም፣ ንፉሰሊም፣ እነዚህ ንፉሰሲም ተብለውም ይጠራሉ
53በቅቡቅ፣ ሐቀፋ፣ ሐርሑር፣
54በሰሎት፣ እነዚህ በሰሉት ተብለውም ይጠራሉ ምሒዳ፣ ሐርሻ
55ቦርቆስ፣ ሲሣራ፣ ቴማ
56ንስያ፣ ሐጢፋ
57ከንጉስ ዳዊት አገልጋዮች ትውልዶች የተመለሱት እነዚህ ነበሩ፣ ሶጣይ፣ ሶፌሬት፣ ፍሩዳ
58የዕላ፣ ደርቆን፣ ጊዴል
59ሰፋጥያስ፣ ሐጢል፣ ፈከራት፣ ሐፂቦይምና አሞን
60በአጠቃላይ፣ 392 የቤተ መቅደስ ሰራተኞችና የሰለሞን ትውልዶች አገልጋዮች ተመላሾች ነበሩ፡፡
61ከዳላያ፣ ጦብያ እና ኔቆዳ ጎሣዎች
62ሰዎች ያሉት ሌላ ቡድን ከቴልሜላ ቴላሬሳ፣ ከክሩብ፣ አዳን፣ በባቢሎን አዳን እና ኢሜር ተብሎም ይታወቃል፤ ከእነዚህ ከተሞች ይመለሳሉ፡፡ ነገር ግን እነርሱ እስራኤላዊያን መሆናቸውን ማረጋገጥ አልቻሉም፡፡
63የኤብያ፣ አቆስ፣ እና ቤርዜሊ ትውልድ የሆኑ ካህናትም ደግሞ ተመለሱ፡፡ ቤርዜሊ ከገለዓድ አካባቢ የቤርዜሊ ትውልድ የሆነችን አንዲት ሴት አገባ፤ እርሱም የሚስቱን ቤተሰቦች ስም መጠሪያው አድርጎ ወሰደ፡፡
64እነዚህ የአባቶችን ስሞች በያዙ መዛግብቶች ውስጥ የትውልድ ሀረጋቸውን ፍለጋ አደረጉ፣ ነገር ግን የቤተሰቦቻቸውን ስሞች ማግኘት አልቻሉም፤ ስለዚህ ካህናት ያሏቸውን መብቶችና ግዴታዎች ማግኘት አልተፈቀደላቸውም፡፡ በመሆኑም ንጹህ እንዳልሆኑ ስተቆጠረ ካህናት ለመሆን አልበቁም ምክንያቱም የትውልድ ሀረጋቸውን ማመላከት አልቻሉም፡፡
65ስለዚህ አገረ ገዥው በኡሪምና ቱሚም የሚያገለግል ከህን እስኪነሳ ድረስ ከመስዋዕቱ ከተወሰደው እጅግ ከተቀደሰው ከካህናቱ ድርሻ ምግብ እንዳይበሉ አዘዛቸው፡፡
66በአጠቃላይ፣ ከይሁዳ የተመለሱት ሰዎች 42360 ነበሩ፡፡
67እንደዚሁም 7337 አገልጋዮቻቸውና 245ዘማሪዎች ከወንዶችም ከሴቶችም በአንድነት ተቆጠሩ፡፡
68እስራኤላዊያኑ ከባቢሎን 736 ፈረሶችና 245 በቅሎዎች፣
69አራት መቶ ሰላሳ አምስት ግመሎችና 6720 አህዮችንም ጭምር ይዘው ተመለሱ፡፡
70አንዳንዶቹ የጎሣው መሪዎች ለመቅደሱ ግንባታ ሠራተኞች ስጦታዎችን ሰጡ፡፡ አገረ ገዥው 8. 5 ኪሎግራም ወርቅ ለመቅደስ አገልግሎት ሀምሳ ጎድጓዳ ሳህኖች፣ እና 530 የክህነት ልብሶችን ለካህናቱ ሰጠ፡፡
71ሌሎቹ መሪዎች ለግምጃ ቤት ሀላፊው 170 ኪሎግራም ወርቅ ሰጡ፣ የጎሣው መሪዎች በአጠቃላይ 1. 2 ሜትሪክ ቶን ብር ሰጡ፡፡
72ሌላው ህዝብ 170 ኪሎግራም ወርቅ፣ እና 1. 1 ሜትሪክ ቶን ብር እንዲሁም 67 የክህነት ልብስ ለካህናቱ ሰጡ፡፡
73ስለዚህም ካህናቱ፣ ካህናቱን የሚረዱ ሌዋውያን፣ የቤተመቅደሱ ጠባቂዎች፣ ዘማሪዎቹ፣ የቤተ መቅደሱ ሰራተኞች፣ እና በርካታው ተራ ህዝብ እንዲሁም እስራኤላዊ የሆኑ ሁሉ አባቶቻቸው ይኖሩባቸው በነበሩ በይሁዳ ከተሞች መኖር ጀመሩ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።