1ከዚያ የእስራኤል ሊቀ ካህን የሆነው ኤልያብ፣ ከሌሎች ካህናት ጋር የበጎች በር የተባለውን እንደገና ሰሩ፡፡ ይህንንም ለያህዌ ክብር ለዩት፣ እናም የመግቢያውን በሮች በስፍራው አቆሙ ቀጥሎ ቅጥሩን የመቶ ማማ እስከሚባለው ድረስ መልሰው ገነቡ፣ እናም ያህዌን ለማክበር ለዩት፡፡ እንዲሁም የሐንኤልን ማማ መልሰው ገነቡ፡፡
2ከእነርሱ ቀጥሎ፣ የኢያሪኮ ሰዎች መልሰው ይገነቡ ነበር፡፡ ከእነርሱ ቀጥሎ፣ የአምሪ ልጅ ዘኩር መልሶ ይገነባ ነበር፡፡
3የአሳ በር የሚባለውን የሃስና ልጆች ገነቡት፡፡ እነርሱ የእንጨት አምዶቹን ከመግቢያዎቹ በላይ አጋደሙ፣ ደግሞም በሮቹን በስፍራቸው አኖሩ፡፡ ከዚያ ጠንካራ ቁልፍ እንዲኖር መቀርቀሪያ እና መወርወሪያዎችን አበጁ፡፡
4ከእነርሱ ቀጥሎ፣ የአቆስ የልጅ ልጅ፣ የአርዮ ልጅ የሆነው ሜርሞት ቅጥሮቹን ለማጠናከር ጠገናቸው፡፡ ከእርሱ ቀጥሎ፣ የሜሴዜቤል የልጅ ልጅ፣ የበራክየ ልጅ የሆነው ሜሱላም የቅጥሩን ከፊል ጠገነ፡፡ ከእርሱ ቀጥሎ፣ የበዓና ልጅ ሳዶቅ የቅጥሩን ከፊል ጠገነ፡፡
5ከእርሱ ቀጥሎ፣ የተቁሖ ሰዎች ቅጥሩን በከፊል ጠገኑ፣ ነገር ግን የቴቁ መሪዎች አሰሪዎቻቸው እንዲሰሩ የሰጣቸውን ለመስራት አልፈለጉም፡፡
6የፋሴሐ ልጅ ዮዳሄ እና የበሶድያ ልጅ ሜሱላም አሮጌውን መግቢያ ጠገኑ፡፡ ከመግቢያው በላይ ያሉትን አምዶችም በስፍራቸው አደረጉ፣ እንዲሁም መቀርቀሪያዎችንና መወርወሪያዎችን መግቢያውን ለመቆለፍ አስገቡ፡፡
7ከእነርሱ ቀጥሎ፣ የገባኦንና ከምጽጳ ሰዎች የሆኑት ገባኦናዊው መልጥያ እና ሜሮኖታዊው ያዶን፣ ከባህሩ ማዶ የሚገኘው አውራጃ ገዢ የሚኖርበትን ክፍል ጠገኑ፡፡
8ከእርሱ ቀጥሎ፣ የሖርሃያ ልጅ ዑዝኤል፣ እና ሐናንያ ነበሩ፣ ነገር ግን እነርሱ እስከ ሰፊው ቅጥር ድረስ ያለውን ክፍል ሰሩ፡፡ ሐርሃያ ወርቅ አንጥረኛ፣ ሐናንያ ደግሞ ሽቶ ቀማሚ ነበሩ፡፡
9ከእርሱ ቀጥሎ፣ የኢየሩሳሌምን ከፊል አውራጃ የሚገዛው የሆር ልጅ ረፋ የቅጥሩን ከፊል መልሶ ሰራ፡፡
10ከእርሱ ቀጥሎ፣ የኤርማፍ ልጅ ይዳያ ከቤቱ አጠገብ የሚገኘውን ቅጥር ከፊሉን መልሶ ሰራ፡፡ ከእርሱ ቀጥሎ የአሰቦንያ ልጅ ሐጡስ የቅጥሩን ከፊል መልሶ ሰራ፡፡
11የሃሪም ልጅ መልክያ፣ እና የፈሐት ሞዓብ ልጅ አሱብ የቅጥሩን ከፊል ጠገነ፣ እንዲሁም የእቶን ማማ የተባለውን መልሶ ሰራ፡፡
12ከእርሱ ቀጥሎ፣ ሌላውን የኢየሩሳሌም ከፊል አውራጃ የሚገዛው የአጦሎኤስ ልጅ ሰሎም የቅጥሩን ከፊል መልሶ ሰራ፡፡ ሴት ልጆቹ በስራው ረዱት፡፡
13ሐኖንና የዛኖ ከተማ ሰዎች የሸለቆ መግቢያ ተብሎ የሚጠራውን መልሰው ሰሩ፡፡ እነርሱም መግቢያዎቹን መልሰው በስፍራቸው አቆሙ፣ ደግሞም መወርወሪያዎቹንና መቀርቀሪያዎቹን በሮቹን ለመቆለፊያ አበጁ፡፡ ቅጥሩን የቆሻሻ መጣያ በር እስከሚባለው ድረስ 460 ሜትር መልሰው ሰሩ፡፡
14የበት ሐካሪም አውራጃ ገዢ የሆነው የረካብ ልጅ መልክያ የቆሻሻ መጣያ በር ተብሎ የሚጠራውን መልሶ ሰራ፡፡ መግቢያውን ለመቆለፊያ መወርወሪያዎቹንና ፍርግርጎቹን መልሶ ሰራ፡፡
15የምጽጳ አውራጃን የሚገዛው የኮልሐዜ ልጅ ሰሎም የፏፏቴ በር ተብሎ የሚጠራውን መግቢያ መልሶ ሰራ፡፡ ከመግቢያው በላይ ጣራ አበጀ፣ በሩን ለመቆለፍ መግቢያዎቹንና መቀርቀሪያዎቹን እንዲሁም ፍርግርጎቹን አበጀ፡፡ ከዳዊት ከተማ ተነስቶ ቁልቁል እስከ ሼላን ገንዳ አጠገብ ከንጉሱ መናፈሻ ቀጥሎ ቅጥሩን ገነባ፡፡
16ከእርሱ ቀጥሎ፣ የቤት ዱር አውራጃን በከፊል የሚገዛው የዓዝቡቅ ልጅ ነህምያ፣ በዳዊት ከተማ ውስጥ እስከ መቃብር ስፍራ ያለውን ቅጽር፣ ሰው ሰራሽ እስከ ሆነው መዋኛ እና እስከ ፈረስ ቤቶች ድረስ መልሶ ሰራ፡፡
17ከእርሱ ቀጥሎ፣ ካህናቱን የረዱት ብዙ የሌዊ ትውልዶች የቅጥሩን ክፍሎች መልሰው ሰሩ፡፡ የባኒ ልጅ ሬሁ አንዱን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡ የቅኢላን ግማሽ አውራጃ የሚገዛው ሐሽብያ የአውራጃውን ህዝብ ወክሎ ቀጣዩን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡
18የቅዒሊን ቀሪውን ግማሽ አውራጃ የሚገዛው የኤንሐዳድ ልጅ በዋይና ከሌሎች የሌዊ ትውልዶች ጋር ቀጣዩን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡
19ከእርሱ ቀጥሎ፣ የምጽጳ ከተማን የሚገዛው የኢያሱ ልጅ ኤጽር እስከ ጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት ደጃፍ፣ መአዘን ላይ እስከ ሚገኘው የቅጥሩ ቅስት ድረስ ያለውን ሌላውን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡
20ከእርሱ ቀጥሎ፣ የዘባይ ልጅ ባሮክ የቀረውን የቅጥሩን ክፍል በታላቅ ትጋት መልሶ ሰራው፡፡ ከሊቀ ካህኑ ከኤልያሴብ ቤት በር እስከ ራሱ እስከ ባሮክ ቤት መጨረሻ ድረስ ያለውን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡
21ከእርሱ ቀጥሎ፣ የአቆስ የልጅ ልጅ፣ የኦርዮ ልጅ የሆነው ሜሪሞት ከኤልያሴብ ቤት በር እስከ ራሱ እስከ ሜሪምት ቤት መጨረሻ ያለውን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡
22ከእርሱ ቀጥሎ፣ ብዙ ካህናት የቅጽሩን ክፍሎች መልሰው ሰሩ፡፡ በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ያሉ ካህናት አንድ ክፍል መልሰው ሰሩ፡፡
23ከእነርሱ ቀጥሎ፣ ብንያምና አሱብ ከቤታቸው ፊት ለፊት ያለውን አንድ ክፍል መልሰው ሰሩ፡፡ የሖናንያ የልጅ ልጅ፣ የመፅሤያ ልጅ የሆነው ዓዛርያስ ቀጣዩን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡
24ከእርሱ ቀጥሎ፣ ከዓዛርያስ ቤት ቅጽሩ በጥቂቱ ዞር እስከሚልበት ድረስ ያለውን አንዱን ክፍል የኤንሐዳድ ልጅ ቢንዊ መልሶ ሰራ፡፡
25ከእርሱ ቀጥሎ፣ ቅጥሩ ከሚዞርበትና የመጠበቂያ ማማው ከላይኛው ቤተ መንግስት ከፍ ብሎ እስከሚታይበት ድረስ ያለውን አንድ ክፍል የኡዛይ ልጅ ፉላል መልሶ ሰራ፡፡ መጠበቂያ ማማው ጠባቂዎቹ ከሚኖሩበት አደባባይ አጠገብ ይገኛል፡፡ ከፉላል ቀጥሎ፣ የፋሮስ ልጅ ፈዳ ቅጥሩን መልሶ ሰራ፡፡
26ከእርሱ ቀጥሎ የቤተ መቅደስ አገልጋዮች በትልቁ ማማ ምስራቅ አቅጣጫ ፊቱን ወደ ውሃ በር ያደረገውን አንድ ክፍል መልሰው ጠገኑ፡፡
27ከእርሱ ቀጥሎ፣ የተቁሐ ሰዎች ከትልቁ ማማ ፊት ለፊት እስከ ኦፌል ቅጥር ድረስ ያለውን ሁለተኛውን ክፍል መልሰው ሰሩ፡፡
28ከፈረስ መግቢያ ሰሜን አንስቶ ያለውን ቅጽር አንድ የካህናት ቡድን መልሶ ሰራው፡፡ እያንዳንዱ ካህን ከቤቱ ፊት ለፊት ያለውን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡
29ከእነርሱ ቀጥሎ፣ የኢሜር ልጅ ሳዶቅ ከቤቱ ፊት ለፊት ያለውን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡ ከእርሱ ቀጥሎ፣ በስተምስራቅ የሚገኘው በር ጠባቂ የነበረው የሴኬንያ ልጅ ሸማያ ቀጣዩን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡
30ከእርሱ ቀጥሎ፣ የሰሌምያ ልጅ ሐናንያ፣ እና የሴሌፍ ስድስተኛ ልጅ አንድ ክፍል መልሰው ሰሩ፡፡ ያም እነርሱ መልሰው የጠገኑት ሁለተኛው ክፍል ነበር፡፡ ከእርሱ በኋላ የበራክያ ልጅ ሜሱላም እርሱ ይኖርበት በነበረው ቤት ፊት ለፊት የሚገኙትን ቅጥሮች ክፍል መልሶ ሰራ፡፡
31ከእነርሱ ቀጥሎ፣ ወርቅ አንጣሪው መልክያ ከቀጠሮ በር ማዕዘን ላይ እስከሚገኘው የላይኛው መኖሪያዎች የሚገኙትን የቤተ መቅደስ አገልጋዮችና ነጋዴዎች እስከ ሚገለገሉባቸው ህንጻዎች ድረስ ያለውን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡
32ሌሎች ወርቅ አንጥረኞች፣ ከነጋዴዎች ጋር ሆነው የቅጥሩን የመጨረሻ ክፍያ እስከ በጎች በር ድረስ መልሰው ሰሩ፡፡