መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ትንቢተ ናሆም 2

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1እስክትደቅቂ ድረስ የሚረግጥሽ እርሱ እየመጣ ነው፡፡ ስለዚህ ምሽጐችሽን አጠናክሪ መንገድሽን ጠብቂ፤ ወገብሽን ታጠቂ፤ ኃይልሽን ሁሉ አሰባስቢ፡፡
2አጥፊዎች ባድማ ቢያደርጓቸውም፣ የወይን ተክል ቦታቸውን ቢያጠፉባቸውም እንደ እስራኤል ክብር ሁሉ ያህዌ የያዕቆብንም ክብር ይመልሳል፡፡
3የወታደሮቹ ጋሻ ቀይ ነው፣ ተዋጊዎቹም ሐምራዊ ልብስ ለብሰዋል ዝግጁ በሆኑበት ቀን የሰረገሎቹ ብረት ያብረቀርቃል የጦሩ ዘንግ ይወዛወዛል፡፡
4ሰረገሎቹ በየመንገዱ ይከንፋሉ፤ ሰፋፊ በሆኑት መንገዶች በፍጥነት ወዲያ ወዲህ ይላሉ፡፡ የሚንቦገቦግ ችቦ ይመስላሉ፤ እንደ መብረቅም ይወረወራሉ፡፡
5እስክትደቂ ድረስ የሚረግጥሽ እርሱ የጦር ሹማምንቱን ይጠራል እነርሱም እየተደነቃቀፉ ወደ ፊት ይመጣሉ፣ ለማጥቃት ወደ ከተማ ቅጥር ይወጣሉ፤ የሚወረወርባቸውን ፍላጻ በትልቁ ጋሻቸው ይከላከላሉ፡፡
6በወንዙ በኩል ያሉ በሮች ወለል ብለው ይከፈታሉ ቤተ መንግሥቱም ተደመሰሰ፡፡
7ንግሥቲቱ ተማርካ ዕርቃኗን ተወሰደች ሴት አገልጋዮቿ ደረታቸውን እየደቁ እንደ ርግብ ያላዝናሉ፡፡
8ነነዌ ውሃ መያዝ እንደማይችል ኩሬ ናት፤ ሕዝቧም እንደ ፈጣን ወራጅ ውሃ ፈጥኖ ይሸሻል፡፡ ሌሎች «ቁሙ ቁሙ» ብለው ይጮኻሉ ዞር ብሎ የሚያይ ግን የለም፡፡
9የነነዌ ሀብት ስፍር ቁጥር የለውም የከበሩ ድንጋዮቿ የተትረፈረፉ ናቸው ስለዚህ ብሩን ዝረፉ፣ ወርቁንም ንጠቁ፡፡
10ነነዌ ባዶ ሆነች፣ ተራቆተች፡፡ የሰዎች ልብ ቀለጠ፤ የሰው ሁሉ ጉልበት ተብረከረከ ሁሉም ተጨንቀዋል፤ ፊታቸው ገርጥቷል፡፡
11የአንበሶች ዋሻ፣ የአንበሳ ደቦሎች የሚመገቡበት፣ ወንድ አንበሳና እንስት አንበሳ ምንም ሳይፈሩ ወዲያ ወዲህ ይሉበት የነበረ ቦታ የታል?
12አንበሳ ለግልገሎቹ የሚበቃውን ያህል ገደለ፤ ለእንስቶቹ የሚበቃውንም ያህል አድኖ ያዘ የገደለውን በዋሻው፣ የነጠቀውንም በመኖሪያ ቦታው ሞልቶአል፡፡
13የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ ሰረገሎችን አቃጥላለሁ፤ ደቦል አንበሶችህን ሰይፍ ይበላቸዋል፡፡ የዘረፍኸውን ከምድርህ አጠፋለሁ፤ ከእንግዲህ የመልእክተኞችህ ድምፅ አይሰማም፡፡»
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።