መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ትንቢተ ናሆም 1

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ስለ ነነዌ የተነገረ ቃል፤ የአልቆሻዊው የናሆም ራእይ መጽሐፍ ይህ ነው፡፡
2ያህዌ ቀናተኛና ተበቃይ ነው፤ ያህዌ የሚበቀል በመዓትም የተሞላ አምላክ ነው፡፡ ያህዌ ባላጋራዎቹን ይበቀላል፤ በጠላቶቹም ላይ ቁጣውን ይወርዳል፡፡
3ያህዌ ለቁጣ የዘገየ፣ በኃይሉም ታላቅ ነው፤ በምንም ዐይነት ጠላቶቹን ንጹሕ ናችሁ አይልም፡፡ ያህዌ በወጀብና በዐውሎ ነፋስ ውስጥ መንገድ አለው፤ ደመናም የእግሩ ትቢያ ነው፡፡
4ባሕርን ይገሥጻል፤ ያደርቀዋልም፤ እርሱ ወንዞችን ሁሉ ያደርቃል፡፡ ባሳንና ቀርሜሎስ ጠውልገዋል፤ የሊባኖስ አበቦችም ረግፈዋል፡፡
5ተራሮች በእርሱ ፊት ተናወጡ፤ ኮረብቶችም ቀለጡ፤ ምድር በፊቱ፣ ዓለምና በውስጧ የሚኖሩ ሰዎችም ሁሉ ተናወጡ፡፡
6በቁጣው ፊት ማን መቆም ይችላል? ጽኑ ቁጣውንስ ማን መቋቋም ይችላል? መዓቱ እንደ እሳት ፈስሶአል፤ ዐለቶችም በፊቱ ተሰነጣጠቁ፡፡
7ያህዌ መልካም ነው፤ በመከራ ጊዜም መሸሸጊያ ነው፤ በእርሱ ለሚታመኑበት ታማኝ ነው፡፡
8ጠላቶቹን ግን በኃይለኛ ጐርፍ ያጥለቀልቃቸዋል፤ ወደ ጨለማም ያሳድዳቸዋል፡፡
9እናንተ ሰዎች ያህዌ ላይ የምታሤሩት ምንድነው? እርሱ ፈጽሞ ያጠፋዋል፤ መከራም ዳግመኛ አይነሣም፡፡
10እንደ እሾኽ ይጠላለፋሉ፤ በወይን ጠጃቸውም ይሰክራሉ፤ እሳት እንደ ገለባ ይበላቸዋል፡፡
11ነነዌ ሆይ፣ ያህዌ ላይ የሚያሤር፣ ክፉ ምክር የሚመክር ከመካከላችሁ ወጥቷል፡፡
12ያህዌ እንዲህ ይላል፤ «ኅይለኞችና ቁጥራቸውም እጅግ የበዛ ቢሆን እንኳ ተቆርጠው ይጠፋሉ፤ ከእንግዲህም ሕዝባቸው አይኖም፡፡ ይሁዳ ሆይ፣ ከዚህ በፊት ባስጨንቅህም፣ ከእንግዲህ አላስጨንቅህም፡፡
13አሁንም ቀንበራቸውን ከአንተ ላይ እሰብራለሁ፤ ስንሰለትህንም በጥሼ እጥላለሁ፡፡
14ነነዌ ሆይ፣ ስለ አንቺ ያህዌ እንዲህ ብሎ አዝዞአል፤ «ስም የሚያስጠራ ትውልድ አይኖራችሁም፡፡ የተቀረጹ ምስሎችና ቀልጠው የተሠሩ ጣዖቶችን ከአማልክቶቻችሁ ቤት አጠፋለሁ፡፡ እጅግ ክፉ ነህና መቀበሪያህን እምስልሃለሁ፡፡
15የምሥራችን የሚያመጣና ሰላምን የሚያውጅ ሰው እግር በተራራው ላይ ናቸው! ይሁዳ ሆይ፣ በዓላትህን አክብር፤ ስእለትህንም ፈጽም፤ ከእንግዲህ ክፉዎች አይወርሩህም፤ እነርሱ ፈጽሞ ይጠፋሉ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።