መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ማርቆስ 8

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በእነዚያ ቀናት እንደገና ብዙ ህዝብ በተሰበሰበና የሚበሉት ባጡ ጊዜ
2ኢየሱስም ደቀመዛሙርቱን ወደእርሱ ጠርቶ ህዝቡ ከኔ ጋር ሶስት ቀናት ቆይተዋል የሚበሉትም የላቸውምና እራራላቸዋለሁ
3ሳይበሉ ብሰዳቸውም በመንገድ ላይ ይደክማሉ አንዳንዶቹም ከሩቅ ሥፍራ ነው የመጡት አላቸው፡፡
4ደቀመዛሙርቱም በዚህ ምድረበዳ እነዚህን ሁሉ የሚያጠግብ እንጀራ እንዴት ይገኛል ብለው መለሱለት፡፡
5ስንት እንጀራ አላችሁ ብሎ ጠየቃቸው፡፡ ሰባት አሉት ፤
6ህዘቡን በምድር ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ ሰባቱንም እንጀራ ተቀብሎ እግዚአብሔርን ካመሰገነ በኋላ ቆርሶ እንዲያቀርቡላቸው ለደቀመዛሙርቱ ሰጣቸው እነርሱም ለህዝቡ አቀረቡላቸው፡፤
7ጥቂትም ትናንሽ አሦች ነበሯቸው ባርኮም ያንንም አንዲያቀርቡላቸው አዘዘ፡፡
8ሕዝቡም በልተውም ጠገቡ፡ ደቀመዛሙርቱም የተረፈውን ቁርስራሽ ሰባት ታላላቅ መሶብ አነሱ፡፡
9የህዝቡም ቁጥር ቁጥራቸውም አራት ሺ ያህል ነበር፡፡ ከዚያም ኢየሱስ ህዝቡን አሰናበታቸው ፡፡
10ወዲያውም ከደቀመዛሙርቱ ጋር ወደ ጀልባ ገብተው ወደ ዳልማኑታ አውራጃ አካባቢ ሄዱ፡፡
11ፈሪሳውያንም ወደ ኢየሱስ እርሱ መጥተው ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ ምልክትን እንዲያሳያቸው በመፈለግ ሊፈትኑት ይጠይቁት ጀምር፡፡
12ኢየሱስም እርሱም በመንፈሱ እጅግ ተበሳጭቶ በዚህ ዘመን ያለ ህዝብ ለምን ምልክት ይፈልጋል እዉነት እላችኋለሁ እናንተ ሰዎች አይሰጣችሁም አላቸው፡፡
13ትቶአቸው እንደገና ወደ ጀልባ ገብቶ ወደ ባህሩ ማዶ ተሻገረ፡፡
14ደቀመዛሙርቱም እንጀራ መያዝን ረሱ፡፡
15በጀልባ ውስጥም ከአንድ እንጀራ በቀር ምንም አልያዙም ነበር።
16ኢየሱስ ከፈሪሳዊያንና ከንጉሥ ሄሮድስ እርሾ ተጠንቀቁ ብሎ አሳሰባቸው፡፡ እንጀራ ስላልያዝን ነው ብለው እርስ በእርሳቸው ተነጋገሩ ፡፡
17ኢየሱስም ይህን አውቆ እንጀራ ስለሌላችሁ ለምን ትነጋገራላችሁ፡፡ እስከአሁን አልገባችሁምን ወይም እስከአሁን አታስተውሉምን ልባችሁ ደንዝዞአልን
18አይን እያላችሁ አታዩምን ጆሮ እያላችሁ አትሰሙምን አታስታውሱምን
19አምስቱን እንጀራ ለአምስት ሺ ባካፈልኩ ጊዜ ስንት መሶብ ቁርስራሽ ሰበሰባችሁ ብሎ ጠየቃቸው እነርሱም አሥራ ሁለት ብለው መለሱለት፡፡
20ሰባቱን ለአራት ሺ ባካፈልኩ ጊዜስ ስንት ቅርጫት ቁርስራሽ አነሳችሁ አላቸው ሰባት አሉት ፡፡
21ገና አታስተውሉምን አላቸው፡፡
22ወደ ቤተ ሳይዳም መጡ፡፡ የአካባቢው ሰዎችም አይነ ስውር የሆነን ሰው ወደ እርሱ አምጥተው እንዲዳስሰው ለመኑት፡፡
23የአይነስውሩንም ሰው እጅ ይዞ ከመንደሩ ውጭ ወሰደው፡፡ በአይኖቹም ላይ እንትፍ ብሎና እጁን ጭኖ አሁን ይታይሀልን ብሎ ጠየቀው፡፡
24ቀና ብሎ ተመለከተና ሰዎች ሲራመዱ እንደዛፍ ሆነው ይታየኛል አለው፡፡
25እንደገናም እጁን በአይኑ ላይ በጫነበት ጊዜ በሚገባ ተመለከተ የአይኑም ብርሀን ተመለሰለት ሁሉንም ነገር አጥርቶ አየ፡፡
26ኢየሱስም ወደ መንደሩ እንኳ እንዳትገባ ብሎ ወደ ቤቱ አሰናበተው፡፡
27ኢየሱስም ከደቀመዛሙርቱ ጋር ወደ ፊሊጶስፕ ቂሳሪያ ዙሪያ ወዳሉ መንደርሮች ሄዱ፡ በመንገድም ላይ ሳሉ ሰዎች እኔን ማነው ይላሉ ብሎ ጠየቃቸው
28እነርሱም መጥምቁ ዮሐንስ ሌሎች ደግሞ ኤልያስ አንዳንች ግን ከነቢያት አንዱ ብለው መለሱለት፡፡
29እንደገናም እናንተስ እኔ ማን እንደሆንኩ ትላለችሁ ብሎ ጠየቃቸው፡፡ ጴጥሮስም አንተ መሲሁ ነህ በማለት መለሰለት፡፡
30ስለእርሱ ለማንም እንዳይናገሩ አስጠነቀቃቸው፡፡
31የሰው ልጅ ብዙ መከራ እንደሚቀበል በሽማግሌዎች፣ በካህናት አለቆችና በጻፎች እንደሚነቀፍና እንደሚገደል በሦስተኛውም ቀን እንደገና እንደሚነሳ እንዳለው ያስተምራቸው ጀመር፡፡
32ይህንንም በግልጽ ተናገረ፡፡ ጴጥሮስም ወስዶ ሊገስጸው ጀመረ፡፡
33ኢየሱስም ዞር ብሎ ደቀመዛሙርቱን አየና ወደ ኋላዬ ሂድ አንተ ሰይጣን የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን ነገር አታስብምና ብሎ ጴጥሮስን ገሰጸው፡፡
34ህዘቡንና ደቀመዛሙርቱንም ወደ እርሱ ጠርቶ ሊከተለኝ የሚወድ ማንም ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ፡፡
35ህይወቱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠጣፋታልና ነፍሱን ግን ስለኔ ወይም ስለወንጌል የሚያጣ ያገኛታልና፡፡
36ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጣ ምን ይጠቅመዋል፡፡
37ወይስ ሰው ስለነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል፡፡
38በዚህ አመንዝራ ኃጢአተኛ ህዝብ ፊት በእኔና በቃሌ የሚያፍርብኝ ማንም ቢኖር የሰው ልጅም ከቅዱሳን መላዕክቱ ጋር በአባቱ ክብር በሚመጣበት ጊዜ ያፍርበታል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።