1ከዚያ ወጥቶ ወደ ገዛ ምድሩ መጣ፤ ደቀመዛሙርቱም ተከተሉት፡፡
2ሰንበት በሆነ ጊዜም በምኩራብ ውስጥ ሊያስተምር ጀመረ፡፡ የሰሙትም ሁሉ ይህ ሰው እነኚህን ነገሮች ከወዴት አገኛቸው? ለዚህ ሰው የተሰጠችውስ ጥበብ እንደምን ያለች ናት፤ በእጆቹ የሚደረጉት እነዚህ ታላላቅ ነገሮችስ ምን ትርጉም ይኖራቸው ይሆን?
3ይህ አናጺው የማርያም ልጅ፤ የያዕቆብና የዮሳ፣ የይሁዳና የስምዖን ወንድም አይደለምን? እህቶቹስ ቢሆኑ እዚህ ከእኛ ጋር አይደሉምን? በማለት ተደነቁ፤ ተሰናከሉበትም፡፡
4ኢየሱስም ነብይ በሀገሩ፣ በወገኑና በገዛ ቤተሰቡ ካልሆነ በስተቀር ሳይከበር አይቀርም አላቸው፡፡
5ላይ እጆቹን ጭኖ ከመፈወስ በስተቀር በዚያ ታላቅ ተአምራት አላደረገም፡፡
6ምክንያት ተደነቀ፡፡ በየመንደሮቹም እያስተማረ ዞረ፡፡
7አሥራ ሁለቱን ወደ ራሱ ጠራና ሁለት ሁለት አድርጎ ይልካቸው ጀመር፤ በእርኩሳን መናፍስት ላይም ሥልጣንን ሰጣቸው፡፡
8ለጉዞአቸውም ከበትራቸው በቀር ምግብ፣ የመንገድ ሻንጣም ሆነ በገንዘብ ቦርሳቸው ውስጥ ገንዘብ እንዳይዙ አዘዛቸው፡፡
9በስተቀር ቅያሪ ልብስ አትያዙ አላቸው፡፡
10ከዚያ እስክትወጡ ድረስ በምትገቡበት ቤት በዚያ ቆዩ አላቸው፡፡
11ቦታ ሁሉ ከማይቀበሏችሁና ከማይሰሟችሁ ሰዎች ምሥክር ይሆንባቸው ዘንድ በጫማችሁ ሥር ያለውን አቧራ አራግፉ፡፡
12ደቀ መዛሙርቱም ወጥተው ሰዎች ንሰሐ እንዲገቡ ሰበኩላቸው፡፡
13ብዙ አጋንንትን አስወጡ፤ ታመው የነበሩ ብዙዎችንም ዘይት ቀብተው ፈወሱአቸው፡፡
14ዝናው ወጥቶ ነበርና ንጉሡ ሔሮድስ በሰማ ጊዜ አጥማቂው ዮሐንስ ከሙታን ተነሥቶአል፤ ስለዚህ እነዚህ ታላላቅ ነገሮች የሚደረጉትም በእርሱ ነው አለ፡፡
15ግን ሌሎች ኤልያስ ነው አሉ፡፡ ሌሎቹም ነብይ ወይም ከነብያት አንዱ ነው አሉ፡፡
16ነገር ግን ሔሮድስ ይህንን ሁሉ በሰማ ጊዜ እኔ አንገቱን ያስቆረጥኩት ዮሐንስ ተነሥቶአል አለ፡፡
17ባገባት በወንድሙ በፊሊጶስ ሚስት በሄሮድያስ ምክንያት ራሱ ልኮ ዮሐንስን በመያዝ በወህኒ አኑሮት ነበርና፡፡
18ዮሐንስም ሔሮድስን የወንድምህ ሚስት ለአንተ ልትሆን አይገባም ይለው ነበር፡፡
19ሔሮድያዳ ዮሐንስን ትቃወምና ልትገድለው ትፈልግ ነበር፣አልቻለችምም፡፡
20ሔሮድስ ዮሐንስን ይፈራው ነበር፡፡ ቅዱስና ጻድቅ እንደሆነ በማወቁም ይጠነቀቅለት ነበር፡፡ በሚሰማው ጊዜ ግራ እየተጋባም ቢሆን በደስታ ይሰማው ነበር፡፡
21ምቹ ቀን በመጣ ጊዜም ልደቱን አስመልክቶ ሔሮድስ ለመኳንንቱ፣ ለሹማምንቱና ለገሊላ ታላላቅ ሰዎች የእራት ግብዣ አዘጋጀላቸው፡፡
22የሄሮድያዳ ልጅ ራሷ ገብታ በዘፈነች ጊዜም ሔሮድስንና ከእርሱ ጋር በማዕድ የተቀመጡትን አስደሰተቻቸው፡፡ ንጉሱም ልጃገረዲቱን የምትፈልጊውን ሁሉ ጠይቂኝ እሰጥሻለሁ አላት፡፡
23ማናቸውንም የምትፈልጊውን ጠይቂኝ፣ የመንግሥቴን ግማሽም ቢሆን እሰጥሻለሁ ብሎ ማለላት፡፡
24እርስዋም ወጥታ ወደ እናቷ በመሄድ ምን ልጠይቀው? ብትላት የአጥማቂው የዮሐንስን ራስ አለቻት፡፡
25እርስዋም ወደ ንጉሱ ፈጥና በመምጣት የአጥማቂውን የዮሐንስን ራስ በሳህን እንድትሰጠኝ እፈልጋለሁ አለችው፡፡
26ንጉሡም እጅግ አዘነ፡፡ ነገር ግን በመሐላዎቹና በማዕድ በተቀመጡት ምክንያት አልተቃወማትም፡፡
27ንጉሡም ወዲያውኑ ከጠባቂዎቹ አንደኛውን ወታደር ልኮ ራሱን እንዲያመጣ አዘዘው፡፡ እርሱም ሔደና በወህኒ የዮሐንስን ራስ ቆረጠው፤
28በሳህን አምጥቶም ለልጃገረዲቱ ሰጣት፣ ልጃገረዲቱም ለእናቷ ሰጠቻት፡፡
29ደቀመዛሙርቱም ይህንን በሰሙ ጊዜ መጡና አስከሬኑን ወስደው በመቃብር አኖሩት፡፡
30ሐዋርያቱም ወደ ኢየሱስ ተመልሰው ያደረጉትንና ያስተማሩትን ነገር ሁሉ ነገሩት፡፡
31እርሱም እናንተ ራሳችሁ ወደ ምድረበዳ ኑና ጥቂት ጊዜ ዕረፉ አላቸው፡፡ ወደ እነርሱ የሚመጡና የሚሔዱ ብዙዎች ነበሩና ለመብላት እንኳን ጊዜ አጥተው ነበር፡፡
32በጀልባ ገብተው ወደ ምድረበዳው ፈቀቅ ብለው ሔዱ፡፡
33ሲሔዱም ሕዝቡ አዩአቸውና ብዙዎቹ አወቁአቸው፤ እነርሱም ከየከተሞቹ ሁሉ በአንድነት በሩጫ ቀደሟቸው፡፡
34ወደዚያ በመጣም ጊዜ ብዙ ሕዝብ አይቶ እረኛ እንደሌላቸው በጎች ይመስሉ ነበርና አዘነላቸው፡፡ ብዙ ነገሮችንም ያስተምራቸው ጀመር፡፡
35ቀኑ በመሸ ጊዜም ደቀመዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀርበው ሥፍራው ምድረበዳ ነው፣ ቀኑም መሽቶአል፤
36በአቅራቢያው ወደሚገኙ ከተሞችና መንደሮች ሔደው ለራሳቸው አንዳች የሚበሉትን እንዲገዙ ሕዝቡን አሰናብታቸው አሉት፡፡
37እርሱ ግን መልሶ እናንተ የሚበሉትን ስጧቸው አላቸው፡፡ እነርሱም እንሂድና ይበሉ ዘንድ የአንድን ሰው የስድስት ወር ገቢ በሚያህል ገንዘብ እንጀራ ገዝተን እንስጣቸውን? አሉት፡፡
38እርሱም ምን ያህል እንጀራ እንዳላችሁ ሂዱና እዩ አላቸው፡፡ ባወቁ ጊዜም ያለው አምስት እንጀራና ሁለት ዓሳ ነው አሉት፡፡
39እርሱም ሁሉን በአረንጓዴው ሣር ላይ በቡድን በቡድን እንዲያስቀምጡ አዘዛቸው፡፡
40እነርሱም በመቶዎችና በሃምሳዎች እየሆኑ በረድፍ ተቀመጡ፡፡
41እርሱም አምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዓሳ ተቀብሎ ወደ ሰማይ በመመልከት ባረከውና ቆርሶ ለሕዝቡ እንዲያቀርቡት ለደቀመዛሙርቱ ሰጣቸው፡፡ ሁለቱን ዓሳም ለሁሉም አካፈላቸው፡፡
42ሁሉም በልተው ጠገቡ፡፡
43አሥራ ሁለት ትላልቅ መሶብ ሙሉ ቁርስራሽ፣ እንዲሁም ከዓሳው ሰበሰቡ፡፡
44እንጀራውን የበሉት እነዚያ 5000 ወንዶች ነበሩ፡፡
45ወዲያውኑ እርሱ ራሱ ሕዝቡን ሲያሰናብት ሳለ ደቀመዛሙርቱ በጀልባ ገብተው ወደ ማዶ ወደ ቤተሳይዳ ቀድመውት እንዲሻገሩ ግድ አላቸው፡፡
46ከተለያቸው በኋላም ሊጸልይ ወደ ተራራ ፈቀቅ አለ፡፡
47በመሸም ጊዜ ጀልባዋ በባህር ላይ ነበረች፤ እርሱም ብቻውን በምድር ላይ ነበር፡፡
48ነፋሱ ከፊት ለፊታቸው እየተቃወማቸው ሳለ ለመቅዘፍ ሲጨነቁ አያቸውና ከሌሊቱ በአራተኛው ክፍል በባህሩ ላይ እየተራመደ ወደ እነርሱ መጣ፤ ሊያልፋቸውም ይፈልግ ነበር፡፡
49ነገር ግን በባህሩ ላይ ሲራመድ ባዩት ጊዜ ምትሃት ነው ብለው ስላሰቡ ጮኹ፡፡
50ሁሉም አይተውት ስለነበረ ታወኩ፡፡ እርሱ ግን ወዲያው ተናገራቸውና አይዞአችሁ! እኔ ነኝ አትፍሩ! አላቸው፡፡
51ወደ እነርሱ ወጥቶም ወደ ጀልባይቱ ገባ፤ ነፋሱም ተወ፡፡
52እነርሱም በራሳቸው ያለመጠን ተገረሙ፤ ልባቸው ደንዝዞ ነበርና ስለ እንጀራው አላስተዋሉም፡፡
53በተሻገሩ ጊዜም ወደ ጌንሳሬጥ አገር ወደ ባህሩ ዳርቻ መጡ፡፡
54ከጀልባዋ በወጡ ጊዜም ሕዝቡ ወዲያው አወቁትና
55በዙሪያው ወዳሉ መንደሮች በሞላ በመሮጥ ህሙማንን በአልጋ ተሸክመው እርሱ እንዳለ ወደሰሙበት ወደዚያ አመጧቸው፡፡
56በየትኛውም እርሱ በገባባቸው መንደሮች ወይም ከተማዎች ወይም ሀገሮች ህሙማንን በገበያ ሥፍራዎች ያስቀምጧቸው፣ ቢቻላቸው ሊዳስሱት ካልሆነም የልብሱን ጫፍ ለመንካት ይለምኑት ነበር፤ የዳሰሱትም ሁሉ ይድኑ ነበር፡፡