መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ማርቆስ 5

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ባሕሩ ሌላ ዳርቻ፣ ወደ ጌርጌሴኖን አገር መጡ፡፡
2ከጀልባዋ ውስጥ ሲወጣም ወዲያውኑ ርኩስ መንፈስ ያለበት አንድ ሰው ከመቃብር ሥፍራ ወጥቶ ተገናኘው፤
3በመቃብር ስፍራ አድርጎ ነበር፤ እርሱን በሰንሰለት ሊያስረው የሚችል ሰው አልነበረም፤
4ጊዜ በእግር ብረትና በሰንሰለት ይታሰር ስለ ነበር፣ ሰንሰለቶቹን ይበጣጥሳቸው፣ እግር ብረቶቹንም ይሰባብራቸው ነበር፤ እርሱን ለመያዝ የሚያስችል ጥንካሬ ያለው ሰውም አልነበረም፡፡
5ቀንና ሌሊት በመቃብሮቹና በተራራዎቹ ዘንድ ሰውነቱን በድንጋይ እየቈረጠ ይጮኽ ነበር፡፡
6ከሩቅ ሲያየው፣ ሮጠና ሰገደለት፤
7በመጮኽም፣ የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፣ አታሠቃየኝ አለ፡፡
8ርኩስ መንፈስ ከሰውየው ውጣ ብሎት ነበርና፡፡
9ማን ነው ብሎም ጠየቀው፤ ብዙ ነንና ስሜ ሌጌዎን ነው አለው፡፡
10እንዳያባርራቸውም አጥብቆ ለመነው፡፡
11በተራራው ጥግ ትልቅ የእሪያ መንጋ ይሰማራ ነበር፡፡
12በእነርሱ ውስጥ እንድንገባ ወደ እሪያዎቹ ስደደን በማለትም ለመኑት፡፡
13እዲሄዱ ፈቀደላቸው፡፡ ርኩሳን መናፍስቱም ወጡ፣ በእሪያዎቹም ውስጥ ገቡ፤ ሁለት ሺ ያህል እሪያ ያለበት መንጋም በቁልቁለቱ ላይ ወደ ባሕሩ እየተንጋጋ ሄደ፤ በባሕሩም ውስጥ ሰመጠ፡፡
14የሚጠብቁትም ሸሹ፤ በከተማውና በአገሩ ውስጥም አወሩት፡፡ የሆነውንም እንዴት እንደ ነበረ ለማየትም ሰዎች መጡ፡፡
15ኢየሱስም መጥተው አጋንንት ያደሩበትን፣ ሌጌዎንም እንኳ የነበረበትን ሰው ተቀምጦ፣ ልብስ ለብሶና ልቡም ተመልሶለት አይተው ፈሩ፡፡
16ሰዎችም አጋንንት ባደሩበት ሰውየ ላይ የታየው እንዴት እንደ ሆነና በእሪያዎቹ የሆነውም እንዴት እንደ ነበረ ነገሯቸው፡፡
17ኢየሱስንም ከአገራቸው እንዲወጣ ይለምኑት ጀመር፡፡
18ጀልባዋ ውስጥ እየገባ ሳለ፣ በአጋንንት ተይዞ የነበረው ሰው ከአንተ ጋር ልኑር ብሎ ለመነው፡፡
19አልፈቀደለትም፤ ይልቁንም ወደ ቤትህ፣ ወደ ዘመዶችህ ሂድ፣ ጌታ ለአንተ እንዴት ታላላቅ ነገሮችን እንዳደረገልህ፣ እንዴትም ምሕረቱን ባንተ ላይ እንዳሳየ ንገራቸው አለው፡፡
20ሄደና ኢየሱስ እንዴት ታላላቅ ነገሮችን እንዳደረገለት ዐሥር ከተማ በሚባለው ውስጥ ማሠራጨት ጀመረ፤ ሰዎችም ሁሉ ተደነቁ፡፡
21በጀልባዋ ወደ ሌላ አቅጣጫ ይሄድ በነበረ ጊዜም ደግሞ፣ እጅግ ብዙ ሕዝብ ወደ እርሱ ተሰበሰበ፤ እርሱም በባሕሩ አቅራቢያ ነበረ፡፡
22ከምኵራብ ኀላፊዎች አንዱ፣ ኢያኢሮስ የሚባል መጣ፣ እርሱንም አይቶ በእግሩ ሥር ወደቀ፤
23ልጄ ልትሞት ነው፤ እንድትድንና በሕይወት እንድትኖር መጥተህ እጅህን ትጭንባት ዘንድ እለምንሃለሁ በማለትም አጥብቆ ለመነው፡፡
24ዐብሮት ሄደ፤ እጅግ ብዙ ሰዎችም ተከተሉት፤ ይጋፉትም ነበር፡፡
25ሁለት ዓመት ደም ይፈስባት የነበረ፣
26ብዙ ችግር የደረሰባት ብትሆንና ያላትን ሁሉ ብትከፍልም፣ ምንም ያልተሻላት፣ ይልቁንም የባሰባት
27ሴት ስለ ኢየሱስ ሰምታ ከሕዝቡ በስተኋላ መጣች፣ የኢየሱስንም ልብስ ነካች፡፡
28ላት፣ ይልቁንም የባሰባት 27አንድ ሴት ስለ ኢየሱስ ሰምታ ከሕዝቡ በስተኋላ መጣች፣ የኢየሱስንም ልብስ ነካች፡፡ 28ልብሱን ብቻ ከነካሁ እድናለሁ ብላለችና፡፡
29የሚፈስሰው ደሟ ቆመ፤ ከሕማሟ እንደ ተፈወሰችም በሰውነቷ ታወቃት፡፡
30ኢየሱስ ኀይል ከእርሱ መውጣቱን በራሱ በመረዳት፣ ዙሪያውን ወደ ሕዝቡ ተመለከተ፤ ልብሴን የነካው ማን ነው? ብሎም ተናገረ፡፡
31መዛሙርቱም ሕዝቡ ሲጋፉህ ታያለህ፣ የነካኝ ማን ነውም? ትላለህ፡፡
32ይህን ያደረገችውንም ለማየት ዙሪያውን ተመለከተ፡፡
33ሴትዮዋ ግን በመፍራትና በመንቀጥቀጥ፣ ለእርሷ የተደረገውንም በማወቅ መጣችና በፊቱ ወደቀች፤ እውነቱንም ሁሉ ነገረችው፡፡
34እርሱም፡- ልጄ ሆይ! እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ፣ ከሕማምሽም ተፈወሺ አላት፡፡
35ኢየሱስ ገና እየተናገረ ሳለ ከምኵራቡ ኀላፊ ቤት ሰዎች መጡ፤ ልጅህ ሞታለች፤ መምህሩን ለምን ታስቸግረዋለህ ብለውም ተናገሩ፡፡
36ኢየሱስ የተናገሩትን ሰምቶ የምኵራቡን ኀላፊ “አትፍራ፤ እመን ብቻ” አለው፡፡
37ኢየሱስ ከጴጥሮስ፣ ከያዕቆብና ከያዕቆብ ወንድም ከዮሐንስ በቀር ማንም እንዲከተለው አልፈቀደም፡፡
38ወደ ምኵራቡ ኀላፊ ቤት መጡ፤ ኢየሱስ ያዘኑ፣ የሚያለቅሱና የዋይታ ጩኸት የሚያሰሙ ሰዎችን ተመለከተ፡፡
39ወደ ውስጥ ገባና “ለምን ታዝናላችሁ? ለምንስ ታለቅሳላችሁ? ልጅቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም” አላቸው፡፡
40ሰዎቹ በኢየሱስ ሣቁበት፤ እርሱ ግን ሁሉንም ወደ ውጭ አስወጣቸው፡፡ የልጅቱን አባትና እናት፣ ከእርሱም ጋር የነበሩትን ይዞ ልጅቱ ወደ ነበረችበት ክፍል ገባ፡፡
41ከዚያም ልጅቱን በእጁ ይዞ “ታሊታ ኩም!” ትርጉሙ “ትንሿ ልጅ ተነሺ እልሻለሁ” ማለት ነው፡፡
42ወዲያው ልጅቱ ተነሣች፤ መራመድም ጀመረች፡፡ (ዐሥራ ሁለት ዓመቷ ነበርና) በዚህ ሰዎቹ በጣም ተገረሙ፡፡
43ከዚያም ኢየሱስ ስለዚህ ጕዳይ ማንም ማወቅ እንደሌለበት ለሰዎቹ ጥብቅ ትእዛዛትን ሰጣቸው፤ የምትበላውንም ስጧት አለ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።