መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ማርቆስ 4

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በባህር አጠገብ ማስተማር ጀመረ፡፡ ከህዝቡ መብዛት የተነሳ በባህር ላይ ባለ ጀልባ ገብቶ ተቀመጠ፡፡ ህዝቡም ሁሉ በባህሩ ዳርቻ ላይ ተሰብስበው ነበር፡፡
2ነገርም በምሳሌ አስተማራቸው፡፡ በትምህርቱም እንዲህ አላቸው፡፡
3ስሙ ዘሪ ሊዘራ ወጣ፡፤
4በሚዘራበትም ጊዜ አንዳንዱ በመንገድ ዳር ወደቀ ወፎችም መጥተው ለቀሙት፡፡
5ደግሞ ብዙ አፈር በሌለው በድንጋያማ መሬት ላይ ወደቀ፡፡ መሬቱ ጥልቀት ስላልነበረው ወዲያው በቀለ፤
6በወጣ ጊዜም ጠወለገ ሥርም ስላልነበረው ደረቀ፡፡
7ደግሞም አንዳንዱ በእሾህ መካከል ወደቀ እሾሁም አድጎ አነቀው ፍሬም አላፈራም፡፡
8አንዳንዱ በመልካም መሬት ላይ ወደቀ አደገ እየበዛ ሄደ ፍሬም አፈራ ሶስት እጥፍ ስልሳ እጥፍ እና መቶ እጥፍ ፍሬ ሰጠ፡፡
9እንዲህም አለ ጆሮ ያለው ይስማ፡፡
10በሆነ ጊዜ ከደቀመዛሙርቱ ጋር አብረው የነበሩት ስለ ምሳሌዎቹ ጠየቁት፡፡
11አላቸው ለእናንተ የእግዚአብሔር መንግሥት ምስጢር ተሰጥቷችኋል፡፡ በውጭ ላሉት ግን እንዲህ አይደለም
12እንዳያዩ ሰምተውም እንዳያስተውሉ እንደገና ተመልሰው ይቅር እንዳይባሉ ሁሉም ነገር በምሳሌ ይሆንባቸዋል፡፡
13አላቸው እናንተ ይህ ምሳሌ አልገባችሁምን? ሌሎቹን ምሳሌዎች ሁሉ እንዴት ትረዳላችሁ?
14ዘሪው ቃሉን ዘራ፡፡
15በመንገድ ዳር የወደቁት እነዚህ ናቸው ቃሉ በሚዘራበት ጊዜና ቃሉን እንደሰሙ ወዲያውኑ ሰይጣን መጥቶ በውስጣቸው የተዘራውን ቃል ይወስዳል፡፡
16በድንጋያማ መሬት ላይ የወደቁት አነዚህ ቃሉን በሰሙ ጊዜ ወዲያውኑ በደስታ ይቀበሉታል
17ሥር የላቸውምና ለጊዜው ይቀበሉታል ከዚያም በቃሉ ምክንያት መከራ ወይም ስደት በሚነሳበት ጊዜ ወዲያወኑ በቃሉ ይሰናከሉበታል፡፤
18ቦታ የወደቁት እነዚህ ቃሉን የሰሙ ናቸው
19አለም ሀሳብና የባለጠግነት ማታለል የሌሎች ነገሮች ምኞት ይገቡና ዘሩን ያንቁታል ፍሬ የማያፈራም ይሆናል፡፡
20መሬት የወደቁት እነዚህ ቃሉን ሰምተው የሚቀበሉት ናቸው ሰላሳ እጥፍ ስልሳ እጥፍ እና መቶ እጥፍ የሚያፈሩ ናቸው፡፡
21አላቸው፡- መብራትን ከፍ ባለ ማስመጫ ላይ እንጂ ከእንቅብ በታች ወይም አልጋ ሥር ያስቀምጡታልን?
22ሳይገለጥ የሚቀር ነገር የለም በሚስጢር የተደረገ ወደ ብርሃንም የማይወጣ የለም፡፡
23ያለው ይስማ እንዲህም አላቸው
24-25አስተውሉ መስፈሪያ ይሰፈርላችኋል ለእናንተም የበለጠ ይሰጣችኋል፡፡ ላለው የበለጠ ይጨመርለታል ከሌለው ግን ያ ያለው እንኳ ይወሰድበታል፡፡
26አለ የእግዚአብሔር መንግሥት በመሬት ላይ ዘርን የዘራን ሰው ትመስላለች፡፡
27ሲመሽ ይተኛል ሲነጋም ይነቃል፡፡ እንዴት እንደሆነ ባላወቀው መልኩ ዘሩ አቆትቁጦ በቀለ፡፤
28ምድር የራሷን ሰብል ፍሬ አፈራች መጀመሪያ ቅጠሉ ቀጥሎም ዛላው በመጨረሻም በዛላው ውስጥ ሙሉ ፍሬ አፈራች፡፡
29ግን ፍሬው በደረሰ ጊዜ መከር ነውና ወዲያውኑ ማጭድ አዘጋጀ፡፡
30እንዲህ አለ የእግዚአብሔርን መንግሥት በምን እንመስላታለን? ወይም በምን ምሳሌ እንገልጻታለን?
31ቅንጣት ትመስላለች፡፡ በምድር ላይ በተዘራ ጊዜ ሲዘራ ምንም እንኳ በምድር ካሉ ዘሮች ሁሉ ያነሰ ቢሆንም
32ጊዜ ያድጋል ቅርንጫፍም ያወጣል የሰማይ ወፎች ከጥላው ሥር እስኪጠለልቡበት ድረስ ከተክሎች ሁሉ ይልቅ ታላቅ ይሆናል፡፡
33ሊሰሙ በሚችሉት መጠን ቃሉን በብዙ ምሳሌዎች ተናገራቸው
34ምሳሌ ምንም አልተናገራቸውም፡፡ ለደቀመዛሙርቱ ግን ለብቻቸው ሁሉንም ነገር ገለጸላቸው፡፡
35ቀን በመሸ ጊዜ ወደ ማዶ እንሻገር አላቸው፡፡
36ህዝቡንም ትተው በጀልባ ወሰዱት፡፡ ሌሎችም ጀልባዎች ከእርሱ ጋር ነበሩ፡፡
37የነፋስ ማዕበልም ተነሳ ጀልባው እስኪጥለቀለቅ ድረስ ማዕበል ጀልባውን መታው፡፡
38ከጀልባው በስተኋለኛው ክፍል ትራስ ተንተርሶ ተኝቶ ነበር፡፡ ቀስቅሰውም መምህር ሆይ ስንጠፋ አይገድህምን አሉት፡፡
39እርሱም ተነሳ ነፋሱንም ገሰጸው ባህሩንም ዝም በል ጸጥ በል አለው፡፡ ነፋሱም ተወ ታላቅ ጸጥታም ሆነ፡፡
40ስለምን ፈራችሁ? እምነት የላችሁምን እምነታችሁስ ወዴት አለ አላቸው፡፡
41ፈርተው እርስ በእርሳቸው ነፋሱና ባህሩ እንኳ የሚታዘዙለት እንግዲህ ይህ ማነው? ተባባሉ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።