1ምኩራብም ደግሞ ገባ፤ በዚያም እጁ የሰለለችበት ሰው ነበረ፡፡
2ሰውየውን በሰንበት ቀን ይፈውሰው እንደሆነ ተመለከቱት፡፡
3የሰለለችበትን ሰውየም ተነሥ አለው፡፡
4ሕዝቡንም በሰንበት ቀን የተፈቀደው መልካም ማድረግ ነው ወይስ ክፉ ማድረግ? ሕይወትን ማዳን ወይስ ማጥፋት? አላቸው፡፡ ነገር ግን ሕዝቡ ዝም አሉ፡፡
5በቁጣ ሲመለከት፣ በልባቸው ድንዳኔ ዐዝኖ፣ ሰውየውን እጅህን ዘርጋ አለው፤ ዘረጋውም፤ ዳነም፡፡
6ወጡ፤ ወዲውም እንዴት ሊያጠፉት እንደሚችሉ ከሄሮድስ ወገኖች ጋር በእርሱ ላይ ተማከሩ፡፡
7ከደቀ ዛሙርቱ ጋር ወደ ባሕሩ ሄደ፤ ከገሊላም እጅግ ብዙ ሕዝብ ተከትለው፤ ከይሁዳና
8ከኤዶምያስና ከዮርዳኖስ ማዶ፣ ከጢሮስና ከሲዶና ምን ታላላቅ ነገሮችን እንዳደረገ በመስማት እጅግ ብዙ ሕዝብ ወደ እርሱ መጣ፡፡
9የተነሣ እንዳያጨናንቁት ትንሽ ጀልባ እንዲያቆዩለት ለደቀ መዛሙርቱ ተናገረ፤
10ፈውሶ ነበርና፡፡ በብዙ ደዌ የሚሠቃዩ ሁሉ ሊዳስሱት ይጋፉት ነበር፡፡
11መናፍስትም ባዩት ጊዜ በፊቱ ወደቁ፤ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ እያሉም ጮኹ፡፡
12ግን ማንነቱን እንዳይገልጡት አጥብቆ አዘዛቸው፡፡
13ወደ ተራራውም ወጣ፤ የሚፈልጋቸውንም ወደ እርሱ ጠራ፤ እነርሱም ወደ እርሱ ሄዱ፡፡
14ጋር እንዲሆኑ፣ ለመስበክ እንዲልካቸውና
15ለማስወጣት ሥልጣን እንዲኖራቸው
16ሁለት ሾመ፤ ጴጥሮስ ብሎ የሰየመው ስምዖን፣
17ልጅ ያዕቆብና የያዕቆብ ወንድም ዮሐንስ፤ እነርሱንም ቦአኔርጌስ ብሎ ጠራቸው፤ የነጎድጓድ ልጆች ማለት ነው፤
18እንድርያስና ፊልጶስ፣ በርተሎሜዎስና ማቴያስ፣ ቶማስና የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፣ ታዴዎስ፣ ቀናተኛው ስምኦንና
19የሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ፡፡
20ኢየሱስ ወደ አንድ ቤት ውስጥ ገባ፡፡ መብላት እንኳ እስከማይችሉ ድረስ እንደ ገና ብዙ ሕዝብ መጥቶ ተሰበሰበ፡፡
21ዘመዶቹም በሰሙ ጊዜ ይዘውት ሊሄዱ ወደ እርሱ መጡ፤ ዐብዶአል ብለው ነበርና፡፡
22የወረዱ ጻፎችም ብዔልዜቡል አለበት፤ አጋንንንትን የሚያስወጣውም በአጋንንት አለቃ ነው አሉ፡፡
23እርሱ ጠርቶአቸውም በምሳሌ ነገራቸው፤ ሰይጣን እንዴት ሰይጣንንን ማስወጣት ይችላል?
24መንግሥትም እርስ በርሱ ቢከፋፈል፣ ያ መንግሥት መቆም አይችልም፤
25ቤትም እርስ በርሱ ቢለያይ፣ ያ ቤት ጸንቶ ሊቆም አይችልም፡፡
26ሰይጣንም እርስ በርሱ ቢቀዋወምና ቢለያይ፣ ፍጻሜው ይሆናል እንጂ መቆም አይችልም፡፡ በመጀመሪያ ኀይለኛውን ሰው ካላሰረና ከዚያም ንብረቱን ካልዘረፈ በቀር፣
27ወደ ኀይለኛው ቤት መግባትና ንብረቱን መዝረፍ የሚችል የለም፡፡
28እላችኋለሁ፤ ለሰው ልጆች ኀጢአታቸው ሁሉ፣ የሚሳደቡትም ስድብ ሁሉ ይቅር ይባላል፤
29ቅዱስን የሚሳደብ ግን ፈጽሞ ይቅርታ አያገኝም፤ ይልቁንም የየዘለዓለም ኀጢአት ዕዳ አለበት፤
30ርኩስ መንፈስ አለበት ብለዋል፡፡
31ወንድሞቹም መጡ፤ ውጭ ቆመውም እንዲጠሩት ወደ እርሱ ላኩ፡፡
32ብዙ ሰው ተቀምጦ ነበር፤ ሰዎችም እነሆ፣ እናትህና ወንድሞችህ ውጭ ይፈልጉሃል አሉት፡፡
33መለሰላቸው፤ አላቸውም፣ እናቴና ወንድሞቼ ማን ናቸው?
34ዙሪያ የተቀመጡትን ተመልክቶም፣ እነሆ እናቴና ወንድሞቼ! ምክንያቱም
35ፈቃድ የሚፈጽም ሁሉ ወንድሜ፣ እኅቴና እናቴ ነው፡፡