1ቀናት በኋላ ኢየሱስ ወደ ቅፍርናሆም ተመልሶ በመጣ ጊዜ፣ በቤት እንዳለ ወሬው ተሰማ፡፡
2ሰዎችም ተሰበሰቡ፤ከዚህ የተነሣ በበሩ መግቢያም እንኳ በቂ ቦታ አልነበራቸውም፡፡ ኢየሱስም የእግዚአብሔርን ቃል ነገራቸው፡፡
3ሰዎችም አንድ ሽባ ሰው ወደ እርሱ አመጡ፡፡
4ብዛት ምክንያት ወደ እርሱ መቅረብ ስላልቻሉ፣ኢየሱስ ባለበት አቅጣጫ ጣሪያውን ነደሉት፡፡ በቀዳዳውም ሽባው ያለበትን ዐልጋ ወደ ታች አወረዱት፡፡
5እምነታቸውን አይቶ ሽባውን ሰው፣ "አንተ ልጅ ኀጢአትህ ተሰርዮልሃል" አለው፡፡
6ግን አንዳንድ ጸሓፍት በዚያ ተቀምጠው ነበር፡፡ ይህ ሰው እንዲህ ብሎ የሚናገረው ለምንድን ነው? እርሱ እግዚአብሔርን ይሳደባል፤
7ከእግዚአብሔር በቀር ኀጢአትን ይቅር ማለት የሚችል ማን ነው? እያሉ በልባቸው ያጉረመርሙ ነበር፡፡
8ኢየሱስ በውስጣቸው እያጉረመረሙ እንደሆነ በመንፈሱ ዐውቆ፣ "በልባችሁ የምታጉረመርሙት ለምንድን ነው? አላቸው፡፡
9ለሽባው ሰው የትኛውን ማለት ይቀላል? ኀጢኣትህ ተሰርዮልሃል ወይስ ተነሣ ዐልጋህን ተሸክመህ ሂድ ማለት?
10እንጂ የሰው ልጅ በምድር ላይ ኀጢኣትን የማስተሰረይ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ፣
11እልሃለሁ፤ ተነሣ! ዐልጋህን ተሸከምና ወደ ቤትህ ሂድ" አለው፡፡
12እርሱም ተነሣ፤ ወዲያውኑም ዐልጋውን ተሸክሞ በሁሉም ፊት ወጥቶ ሄደ፡፡በዚያ የነበሩትም ሁሉም ተገርመው ስለ ነበር እንዲህ ያለ ነገር ፈጽሞ አይተን አናውቅም በማለት እግዚአብሔርን አከበሩ፡፡
13ወደ ባሕሩ ዳርቻ ሄደ፡፡ሕዝቡም በሙሉ ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ አስተማራቸውም፡፡
14ሲያልፍም የእልፍዮስን ልጅ ሌዊን ቀረጥ በመሰብሰቢያ ቦታው ተቀምጦ አየውና "ተከተለኝ" አለው፡፡ ተነሥቶም ተከተለው፡፡
15በእርሱ(በሌዊ) ቤት ተቀምጦ እየበላ ነበር፡፡ ብዙ ቀራጮችና ኀጢአተኞችም ከኢየሱስና ከደቀመዛሙርቱ ጋር ተቀመጡ፤ ብዙዎቹም ተከትለውት ነበርና፡፡
16ጸሓፍትም ከኀጢአተኞችና ከቀራጮች ጋር ሲበላ ሲያዩት ደቀመዛሙርቱን፣ "እርሱ ከቀራጮችና ከኀጢአተኞች ጋር የሚበላውና የሚጠጣው እንዴት ነው" አሏቸው፡፡
17ይህን ሲሰማ፣ "ሕሙማን እንጅ ጤናሞች ሐኪም አያስፈልጋቸውም" ፤ እኔ ኀጢአተኞችን እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም አላቸው፡፡
18ደቀመዛሙርትና ፈሪሳውያን ይጾሙ ነበር፡፡ ወደ እርሱም መጥተው የዮሐንስ ደቀመዛሙርትና የፈሪሳውያን ደቀመዛሙርት የሚጾሙት ነገር ግን የአንተ ደቀመዛሙርት የማይጾሙት ለምንድን ነው? አሉት፡፡
19እንዲህ አላቸው፡፡ሙሽራው አብሮአቸው ሳለ ሚዜዎቹ ይጾማሉ? ሙሽራው ከእነርሱ ጋር እስካለ ሊጾሙ አይችሉም፡፡
20ግን ሙሽራው የሚወሰድበት ቀን ይመጣል፡፡ በዚያን ጊዜ በዚያ ቀን ይጾማሉ፡፡
21አዲስ እራፊ ጨርቅ በዐሮጌ ልብስ ላይ አየይጥፍም፤ ያለበለዚያ የተጣፈው እራፊ ይቀደዳል፡፡ ቀዳዳውም የባሰ ይሆናል፡፡
22የወይን ጠጅ በዐሮጌ ዐቁማዳ ውስጥ የሚያስቀምጥ ማንም ለም፡፡ አለበለዚያ የወይን ጠጁ ዐቁማዳውን ያፈነዳዋል፤የወይን ጠጁና ዐቁማዳውም ይበላሻሉ፡፡ ነገር ግን አዲስ የወይን ጠጅ በአዲስ ዐቁማዳ ውስጥ ያስቀምጣሉ፡፡
23በሰንበት ቀን በእህል ማሳ መካከል ያልፍ ነበር፡፡ ደቀመዛሙርቱም ሲያልፉ እሸት መቅጠፍ ጀመሩ፡፡
24ፈሪሳውያንም እነሆ በሕግ ያልተፈቀደውን በሰንበት የሚያደርጉት ለምንድን ነው? አሉት፡፡
25እንዲህ አላቸው፡፡ ዳዊት በተራበና በተቸገረ ጊዜ ለራሱና አብረውት ለነበሩት ምን እንዳደረገ፣ አብያታር ሊቀ ካህናት በነበረ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደገባ፤
26ብቻ የተፈቀደውን ገጸ ኅብስት እንደ በላ፣ ከእርሱም ጋር ለነበሩት እንደሰጣቸው ፈጽሞ አላነበባችሁምን? እንዲህም አላቸው፡፡
27የተፈጠረው ለሰው ነው እንጂ ሰው ለሰንበት አልተፈጠረም፡፡
28የሰው ልጅ የሰንበትም እንኳ ጌታ ነው፡፡