1ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ፡፡
2በነብዩ በኢሳይያስ እንደተጻፈው እነሆ! መንገድን የሚያዘጋጅላችሁን መልዕክተኛዬን በፊታችሁ እልካለሁ፤
3መንገድን አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ ብሎ በምድረበዳ የሚጮህ ሰው ድምፅ፡፡
4በምድረበዳ እያጠመቀና ለኃጢአት ይቅርታ የንሰሐን ጥምቀት እየሰበከ መጣ፡፡
5ሁሉና በኢየሩሳሌም ያሉ ሁሉ ወደ እርሱ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ እየመጡ ኃጢአታቸውን በመናዘዝ ይጠመቁ ነበር፡፡
6የግመል ጠጉር ይለብስና ወገቡን በቆዳ መታጠቂያ ይታጠቅ፣ አንበጣና የበረሃ ማርም ይበላ ነበር፡፡
7የጫማውን ማሰሪያ ለመፍታት የማልበቃ ከእኔ ይልቅ ታላቅ የሆነ እርሱ ከበስተኋላዬ ይመጣል፡፡
8በውሃ አጥምቄአችኋለሁ፤ እርሱ ግን በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃችኋል እያለ ይሰብክ ነበር፡፡
9ቀናት ኢየሱስ ከገሊላ ናዝሬት በመምጣት በዮርዳኖስ ውስጥ በዮሐንስ ተጠመቀ፡፡
10እንደወጣም ሰማይ ሲከፈት፣ መንፈስ ቅዱስም እንደ እርግብ በእርሱ ላይ ሲወርድ አየ፤
11ልጄ አንተ ነህ፤ በአንተ ደስ ይለኛል የሚል ድምጽም ከሰማያት መጣ፡፡
12መንፈስ ቅዱስ ወደ ምድረበዳ መራው፡፡
13በሰይጣን እየተፈተነም በምድረበዳ ለአርባ ቀን ቆየ፡፡ ከዱር አራዊትም ጋር ነበረ፤ መላዕክትም አገለገሉት፡፡
14ታልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን የምሥራች ቃል እየሰበከ ወደ ገሊላ መጣ፡፡
15ተፈጸመ፤የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለችና ንሰሐ ግቡ፤ በወንጌልም እመኑ ይል ነበር፡፡
16ባህር ዳር ሲያልፍ ሳለ ስምዖን ጴጥሮስንና ወንድሙን እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባህር ሲጥሉ አያቸው፤ አሳ አጥማጆች ነበሩና፡፡
17በኋላዬ ኑና ሰዎችን የምታጠምዱ አደርጋችኋለሁ አላቸው፡፡
18መረቦቻቸውን ትተው ተከተሉት፡፡
19እልፍ እንዳለም የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብንና ወንድሙን ዮሐንስን እነርሱም በጀልባቸው ውስጥ መረቦቻቸውን ሲጠግኑ አያቸው፡፡
20ጠራቸው፤ እነርሱም ዘብዴዎስ አባታቸውን ከተቀጣሪ ሰራተኞቻቸው ጋር በጀልባው ውስጥ ትተው ተከተሉት፡፡
21ቅፍርናሆም ሔዱ፡፡ ወዲያው በሰንበት ቀን ወደ ምኩራብ ገብቶ አስተማራቸው፡፡
22ጸሐፍት ሳይሆን ትምህርቱ እንደ ባለሥልጣን ስለነበረ በትምህርቱ ተገረሙ፡፡
23ርኩስ መንፈስ ያለበት አንድ ሰው በምኩራባቸው ነበረ፡፡
24የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ! ከአንተ ጋር ምን አለን? ልታጠፋን መጣህን? ማን እንደሆንክ አውቄሃለሁ፤ አንተ የእግዚአብሔር ቅዱስ ብሎ ጮኸ፡፡
25ዝም በል! ከእርሱም ውጣ ብሎ ገሰጸው፡፡
26መንፈስ መሬት ላይ ጥሎ ካንፈራገጠው በኋላ በታላቅ ድምጽ ጮኾ ወጣ፡፡
27ሁሉ በጣም ተገረሙና ይህ አዲስ ትምህርት ምንድነው? ርኩሳን መናፍስትን እንኳን በሥልጣን ያዛቸዋልና እነርሱም ይታዘዙለታል በማለት እርስ በርሳቸው ተጠያየቁ፡፡
28እርሱም በገሊላ አውራጃና በዙሪያው ባሉ ሀገራት ሁሉ ዝናው ወጣ፡፡
29እንደወጡ ወዲያው ከዮሐንስና ከያዕቆብ ጋር ወደ ስምዖንና እንድርያስ ቤት መጡ፡፡
30ጊዜ የስምዖን አማት አተኵሷት ተኝታ ነበርና ወዲያው ስለ እርስዋ ነገሩት፡፡
31እጇን ይዞ አስነሳት፤ ወዲያውኑ ትኵሳቱ ለቀቃትና አገለገለቻቸው፡፡
32ጠልቃ በመሸ ጊዜም ብዙ በሽተኞችንና በአጋንንት የተያዙትን ወደ እርሱ አመጧቸው፡፡
33ሰው ሁሉ በአንድነት በቤቱ ደጃፍ ተከማችቶ ነበር፡፡
34በተለያየ በሽታ የታመሙትን ፈወሳቸው፤ ብዙ አጋንንንትንም አወጣ፡፡ አጋንንቱ ማን መሆኑን አውቀውት ነበርና እንዳይገልጡት አዘዛቸው፡፡
35እጅግ በማለዳ ተነስቶ ለብቻው ወደ ምድረበዳ ሔደና ጸለየ፡፡
36ከእርሱ ጋር የነበሩትም ተከተሉት፡፡
37ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ይፈልጉሃል አሉት፡፡
38የምሥራቹን ቃል እንድሰብክ ወደ ሌሎቹ ከተሞች ደግሞ እንሂድ፣ ስለዚህ ጉዳይ መጥቻለሁና አላቸው፡፡
39ወዳሉ ምኩራቦቻቸው ሁሉ እየገባ ሰበከላቸው፣ አጋንንትንም አወጣ፡፡
40ለምጻም ወደ እርሱ መጥቶ ሰገደለትና ብትፈቅድስ ልታነጻኝ ትችላለህ ብሎ ለመነው፡፡
41አዘነለት፤ እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና እፈቅዳለሁ፣ ንጻ! አለው፡፡
42ለምጹ ለቀቀውና ንጹህ ሆነ፡፡
43ለማንም እንዳይናገር አጥብቆ አዘዘውና ወዲያው ሲያሰናብተው ሳለ
44ግን ራስህን ለካህን አሳይ፤ ስለመንጻትህ ምሥክር እንዲሆንባቸው ሙሴ ያዘዘውን መስዋዕት አቅርብ አለው፡፡
45ግን ሄደና ኢየሱስ በግልጽ ወደ ከተማ ለመግባት እስኪሳነው ድረስ ስለዚህ ነገር አብዝቶ ሊያወራና ሊያሰራጭ ጀመረ፡፡ በመሆኑም በምድረበዳ አካባቢዎች እንዲቆይ ሆነ፤ ሰዎችም ከየአቅጣጫው ወደ እርሱ ይመጡ ነበር፡፡