መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ማርቆስ 14

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ከሁለት ቀን በኋላ የፋሲካና የቂጣ በዓል ነበር፡፡ የካህናት አለቆችና ጸሓፍት እንዴት አድርገው በተንኮል ይዘው ሊገድሉት እንደሚችሉ ያስቡ ነበር፡፡
2ነገር ግን የህዝብ ሁከት እንዳይሆን በበዓል ቀን አይሁን ተባብለው ነበር፡፡
3እርሱም በቢታኒያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት በማዕድ ተቀምጦ ሳለ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የከበረ ሽቱ የያዘ የአልባስጥሮስ ጠርሙስ ይዛ መጣች፡፡ ጠርሙሱንም ሰብራ ሽቱውን በኢየሱስ በራሱ ላይ አፈሰሰች ፡፡
4ነገር ግን ከመካከላቸው አንዳንዶቹ እንዲህ ያለው የሽቱ ማባከን ያስፈለገው ለምንድነው በማለት የተበሳጩ አንዳንድ ሰዎች ነበሩ
5ይህ ቅባት ከሦስተ መቶ ሽልንግ በላይ ተሸጦ ለድሆች ሊሰጥ ይቻል ነበር እያሉ በእርሷ ላይ አጉረመረሙ፡፡
6ኢየሱስ ግን ተዋት ለምን ታስቸግሯታላችሁ እርሷ መልካምን ነገር አድርጋልኛለች፡፡
7ድሆች ሁሉጊዜ ከእናንተ ጋር ናቸው በፈለጋችሁም ጊዜ መልካም ልታድጉላቸው ትችላላችሁ እኔን ግን ሁልጊዜ አታገኙኝም፡፡
8እርሷ ከመቃብር በፊት ሰውነቴን ሽቱ በመቀባት የምትችለውን አድርጋለች፡፡
9ደግሞም እውነት እላችኋለሁ ይህ ወንጌል በዓለም ዙሪያ በሚሰበክበት ጊዜ ሁሉ ይህች ሴት ያደረገችው ነገር ለመታሰቢያዋ ይነገራል አላቸው፡፡
10ከአስራ ሁለቱ አንዱ የሆነው የአስቆሮቱ ይሁዳ እንዴት አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ ወደ ካህናት አለቆች ሄደ
11እነርሱም በሰሙ ጊዜ ደስ አላቸው ገንዘብም ሊሰጡት ቃል ገቡለት፡፡እርሱም አሳልፎ ሊሰጠው አመቺ ጊዜ ይጠብቅ ነበር፡፡
12የፋሲካን መስዋዕት በሚያቀርቡበት በቂጣ በዓል የመጀመሪው ቀን ደቀመዛሙርቱ ፋሲካን ትበላ ዘንድ የት እናዛገጅልህ ብለው ጠየቁት፡፡
13እርሱም ከደቀመዛሙርቱ ሁለቱን ልኮ ወደ ከተማ ሂዱ ወዲያውም አንድ ሰው ውሃ ተሸክሞ ታገኛላችሁ ተከትላችሁትም ሂዱና
14ወደሚገባበት ቤት ገብታችሁ የቤቱን ባለቤት መምህሩ ከደቀመዛሙርቴ ጋር ፋሲካን እበላ ዘንድ የእንግዳ ክፍሌ የትኛው ነው ብሎሀል ብላችሁ ጠይቁት
15እርሱ ራሱ በሰገነት ላይ ያለ በቤት ዕቃ የተደራጀና የተዘጋጀ ሰፊ አዳራሽ ያሳያችኋል በዚያም አዘጋጁልን ፡፡
16ደቀመዛሙርቱም ወጥተው ወደ ከተማ መጡ ልክ እንዳላቸውም አገኙ ፋሲካንም አዘጋጁ፡፡
17በመሸም ጊዜ ከአስራ ሁለቱ ጋር መጣ፡፡
18ተቀምጠውም በመመገብ ላይ ኢየሱስ አውነት እላችኋለሁ በማዕድ ከኔ ጋር ያለ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል አላቸው፡፡
19እነርሱም እጅግ አዝነው በየተራ እኔ እሆንን ይሉት ጀምር፡፡
20ኢየሱስም ከእኔ ጋር ወደ ወጥ ሳህኑ የሚነክረውና ከአስራሁለቱ አንዱ ነው አላቸው፡፡
21የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደተጻፈው ይሄዳል የሰው ልጅ አሳልፎ ለሚሰጠው ለዚያ ሰው ግን ወዮለት ባይወለድ ይሻለው ነበር አላቸው፡፡
22እየተመገቡም ሳለ እንጀራን አንስቶ ከባረከ በኋላ ቆርሶ ሰጣቸውና ውሰዱና ብሉ ይህ ስጋዬ ነው አላቸው፡፡
23እንዲሁም ጽዋውን አንስቶ አመስግኖ ለደቀመዛሙርቱ ሰጣቸው ሁሉም ጠጡ፡፡
24እርሱም ይህ ለብዙዎች የሚፈስ የቃል ኪዳን ደሜ ነው ፡፡
25እውነት እላችኋለሁ በእግዚአብሔር መንግስት እንደገና እንደ አዲስ እስከምጠጣበት ቀን ድረስ ከዚህ ወይን ከዚህ በኋላ አልጠጣም፡፡
26መዝሙርም ከዘመሩም በኋላ ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ሄዱ፡፡
27ኢየሱስም እረኛውን እመታለው በጎቹም ይበታተናሉ ተብሎ እንደተጻፈ ሁላችሁ ትሰናከላላችሁ
28ከተነሳሁ በኋላ ግን ወደ ገሊላ እቀድማችኋለሁ አላቸው፡፡
29ጴጥሮስም ሁሉ ቢሰናከሉ እኔ ግን አልሰናከልም አለው፡፡
30ኢየሱስም አውነት እልሃለሁ ዛሬ ሌሊት ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮህ ሶስት ጊዜ ትክደኛለህ አለው፡፡
31እርሱ ግን እጅግ እየጮኸ እስከሞት እንኳ ቢሆን አልክድህም አለው፡፡ ሌሎቹም እንደዚያው አሉ፡፡
32ጌቴ ሴማኒ ወደሚባል ሥፍራም መጡ፡፡ ደቀመዛሙርቱንም እስክ ጸልይ ድረስ በዚህ ተቀመጡ አላቸው፡፡
33ኢየሱስም ጴጥሮስን ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ ሄደ እጅግ ሊያዝንና ሊተክዝ ጀመረ፡፡
34ነፍሴ እስከሞት ድረስ እጅግ አዝናለች በዚህ ሆናችሁ ትጉ ንቁም አላቸው፡፡
35ጥቂትም ፈቀቅ ብሎ ሄደ፤ በግንባሩም ተደፍቶ የሚቻል ከሆነ ይህች ሰዓት ሰዓቲቱ እንድታልፍ መጸለይ ጀመረ፡፡
36አባት ሆይ ለአንተ ሁሉ ይቻላል ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ ነገር ግን የእኔ ሳይሆን የአንተ ፈቃድ ይሁን አለ፡፡
37ወደ እነርሱም መጣ ተኝተውም አገኛቸው ጴጥሮስንም ስምዖን ተኝተሀልን ለአንድ ሰዓት እንኳ ልትተጋ አልቻልክምን፡፡
38ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፡፡ መንፈስ ዝግጁ ነው ሥጋ ግን ደካማ ነው አለው፡፡
39ተመልሶም ሄደና ያንኑ ቃል ደግሞ ጸለየ፡፡
40እንደገና ወደ ደቀመዛሙርቱ በመጣ ጊዜ አሁንም ተኝው አገኛቸው አይናቸው በእንቀልፍ ከብዶ ስለነበር የሚመልሱለትንም አያውቁም ነበር፡፡
41ለሦስተኛም ጊዜ ወደ እነርሱ መጣና እንግዲህስ ይበቃል ተኙ እረፉም የሰው ልጅ ለኃጢአተኞች አልፎ ይሰጥ ዘንድ ሰዓቲቱ ደርሳለች ፡፡
42ተነሱ እንሂድ እነሆ አሳልፎ የሚሰጠኝ በደጅ ነው አላቸው፡፡
43ወዲያውም ገና በመናገር ላይ ሳለ ከአስራ ሁለቱ አንዱ የነበረው የአስቆሮቱ ይሁዳ መጣ ፡፡ ከእርሱም ጋር ከካህናት አለቆች፣ ከጸሓፍትና ከሽማግሌዎች ዘንድ የተላኩ ብዙ ህዝብ ሠይፍና ቆመጥ ይዘው መጡ፡፡
44አሳልፎ የሚሰጠውም የምስመው እርሱ ነውና ያዙት በጥንቃቄ ውሰዱት ብሎ ምልክት ሰጥቷቸው ነበር፡፡
45በመጣም ጊዜ በቀጥታ ወደ ኢየሱስ ቀርቦ መምህር ሆይ ብሎ ሳመው፡፡
46እነርሱም ይዘው ወሰዱት፡፡
47ነገር ግን በዚያ ከቆሙት መካከል አንዱ ሰይፉን መዘዘ፤ የሊቀ ካህናቱን አገልጋይ ጆሮም ቆረጠው፡፡
48ኢየሱስም መልሶ ወንበዴ እንደምትይዙ ሰይፍና ቆመጥ ይዛችሁ ልትይዙኝ መጣችሁን
49በየዕለቱ በቤተ መቅደስ እያስተማርከ ከእናንተ ጋር በነበርኩ ጊዘ አልያዛችሁኝም፡፡ ነገር ግን የተጻፈው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆኗል አላቸው፡፡
50ሁሉም ትተውት ሸሹ፡፡
51እርቃኑን ከበፍታ በተሰራ ጨርቅ የሸፈነ አንድ ወጣት ይከተለው ነበር ሊይዙትም ባሉ ጊዜ
52የበፍታ ጨርቁን ነጠላውን ትቶ ራቁቱን አመለጠ፡፡
53ኢየሱስንም ወደ ሊቀ ካህናቱ ይዘውት መጡ፡፡ የካህናት አለቆች፣ ሽማግሌዎችና ጸሓፍትም አብረውት መጡ፡፡
54ጴጥሮስም እስከ ሊቀካህናቱ ግቢ ድረስ በሩቅ ሆኖ ይከተለው ነበር፡፡ ከዚያም ከጠበቃዊዎች ጋር እሳት እየሞቀ ተቀመጠ፡፡
55ሊቀ ካህናቱና ጉባኤው ሁሉ በኢየሱስ ላይ ሞት የሚያስፈርድበት ምክንያት ይፈልጉ ነበር ነገር ግን ሊያገኙ አልቻሉም፡፡
56ብዙዎች በሀሰት ቢመሰክሩበትም ምስክርነታቸው እርስ በእርሱ የሚጣረስ ነበር፡፡
57ሦስት ሰዎችም ተነስተው በሀሰት መሰከሩበት እንዲህም አሉ
58ይህንን በእጅ የተሰራ ቤተመቅደስ በሶስት ቀን አፍርሼ እንደገና በሶስት ቀን ውስጥ በእጅ ያልተሰራ ሌላ ቤተመቅደስ እሰራለሁ ሲል ሰምተነዋል ፡፡
59የእነርሱም ምስክርነት ቢሆን እርስ በእርሱ የሚጣረስ ነበረ፡፡
60ሊቀ ካህናቱም ተነስቶ በመካከል ቆመና ለሚመሰክሩብህ መልስ አትሰጥምን ብሎ ጠየቀው፡፡
61ኢየሱስ ግን ዝም አለ መልስም አልሰጠም፡፡ ሊቀ ካህናቱም በድጋሚ የቡሩኩ ልጅ መሲሁ አንተ ነህን ብሎ ጠየቀው
62ኢየሱሰም አዎ ነኝ የሰው ልጅ በኃይሉ ቀኝ ተቀምጦ በሰማይ ደመና ሲመጣ ታዩታላችሁ አለው፡፡
63ሊቀካህናቱም ልብሱን ቀደደና ከእንግዲህ ምን ሌላ ምስክር ያስፈልጋል
64እግዚአብሔርን ሲሳደብ ሰምታችኋል ታዲያ ምን ታስባለችሁ ፡፡ ሁሉም ሞት ይገባዋል አሉ፡፡
65አንዳነዶቹም ይተፉበት ፊቱንም ሸፍነው ትንቢት ተናገር እያሉ ያሾፉበት ጀመር፡፡ መኮንኖችም በእጃቸው እየጎሰሙ ወሰዱት፡፡
66ጴጥሮስም በሊቀ ካህናቱ ግቢ እሳት በመሞቅ ላይ ሳለ
67አንዲት የሊቀ ክህናቱ የቤት ውስጥ ሠራተኛ አየችውና አንተ በትክክል ከናዝሬቱ ኢየሱስ ጋር ነበርክ አለችው፡፡
68እርሱ ግን የምትይውን አላውቀውም ምን እንደምታወሪም አልገባኝም ብሎ ካደ፡፡ ወደ ዋናው በር መግቢያ በሄደ ጊዜ ዶሮ ጮኸ
69ሠራተኛይቱም አይታው በዚያ ላሉት ወታደሮች ይህ ከእነርሱ አንዱ ነው አለቻቸው፡፡
70እርሱ ግን እንደገና ካደ፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ በዚያ ከቆሙት መካከል አንዳንዶቹ ጴጥሮስን አንተ የገሊላ ሰው ስለሆንክ በትክክል ከእነርሱ አንዱ ነህ አሉት፡፡
71እርሱም የምትሉትን ሰው አላውቀውም ብሎ መማልና መራገም ጀመረ፡፡
72ወዲያውም ለሁለተኛ ጊዜ ዶሮ ጮኸ ጴጥሮስም ኢየሱስ ዛሬ ሌሊት ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮህ ሶስት ጊዜ ትክደኛለህ ያለውን ቃል አስታወሰ ነገሩንም ባሰበ ጊዜ አለቀሰ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።