1ኢየሱስም ከዚያ ተነስቶ ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ ወደ ይሁዳ አውራጃዎች መጣ፡፡ ብዙ ህዝብም በአንድ ላይ ሆነው እንደገና ወደ እርሱ መጡ፡፡ እንደልማዱም ያስተምራቸው ጀመር፡፡
2ፊሪሳውያንም ወደ ኢየሱስ መጥተው ሊፈትኑት አንድ ሰው ሚስቱን መፍታት ተፈቅዶለታል ሲሉ ጠየቁት፡፡
3እርሱም መልሶ ሙሴ ምን ብሎ አዘዛችሁ አላቸው፡፡
4እነርሱም የፍቺውን ጽፈት ሰጥቶ ይፍታት ብሎ ደንግጓል አሉት፡፡
5ኢየሱስ ግን ሙሴ ስለልባችሁ ድንዛዜ ይህን ትዕዛዝ ሰጣችሁ እንጂ
6ከፍጥረት መጀመሪያ ግን እግዚአብሔር ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፡፡
7በዚህም ምክንያት ሰው እናቱንና አባቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይጣበቃል
8ሁለቱም አንድ ስጋ ይሆናሉ ስለዚህም አንድ ሥጋ እንጂ ከእንግዲህ ሁለት አይደሉም
9እንግዲህ እግዚአብሔር ያጣመረውን ሰው አይለየው አላቸው፡፡
10በቤትም ሳሉ ደቀመዛሙርቱ ስለጉዳዩ እንደገና ጠየቁት፡፡
11ኢየሱስም ማንም ሚስቱን ፈቶ ሌላይቱን ቢያገባ በሚስቱ ላይ ያመነዝራል፡፡
12እንዲሁም እርሷም ራሷ ባሉዋን ትታ ሌላ ሰው ካገባች ታመነዝራለች አላቸው ፡፡
13ህዝቡም እንዲዳስሳቸው ህጻናትን ወደ ኢየሱስ ያመጡ ነበር፡፡ ደቀመዛሙርትም ገሰጹዋቸው፡፡
14ኢየሱስ ግን ባየ ጊዜ በቁጣ ተሞልቶ ህጻናትን ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተው አትከልክሏቸው፡፡ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደነዚህ ላሉት ናትና አላቸው፡፡
15እውነት እላችኋለሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ህጻን ሆኖ የማይቀበላት ሊገባባት አይችልም፡፡
16ህጻናቱንም አቅፎ እጁን ጭኖ ባረካቸው፡፡
17በመንገድም ሳሉ አንድ ሰው ወደእርሱ ሮጠና በፊቱ ተንበርክኮ ቸር መመህር ሆይ የዘላለምን ህይወት እንድወርስ ምን ማድረግ ይገባኛል? ብሎ ጠየቀው ፡፡
18ኢየሱስም ለምን ቸር ትለኛለህ ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር የለም አለው፡፡
19ትዕዘዛትን ታወቃለህ አትግደል አትስረቅ አታመንዘር በሀሰት አትመስክር አታታልል አባትህንና እናትህን አክብር አለው፡፡
20እርሱም መምህር ሆይ እነኚህን ሁሉ ከልጅነቴ ጀምሮ ጠብቄአለሁ አለው፡፡
21ኢየሱስም አይቶ ወደደውና አንዲት ነገር ቀርታሀለች ሂድ ያለህን ሁሉ ሽጥና ለድሆች ስጥ መዝገብም በሰማይ ይቆይሀል መጥተህም ተከተለኝ አለው፡፡
22እርሱም ብዙ ሀብት ነበረውና በሰማው ነገር ፊቱ ተቁሮ እያዘነ ሄደ፡፡
23ኢየሱስም ዙሪያውን ተመለከተና ደቀመዛሙርቱን ለሀብታሞች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት ጭንቅ ነው አላቸው፡፡
24ደቀመዛሙርቱም በንግግሩ እጅግ ተገረሙ፡፡ ኢየሱስ እርሱ ግን መልሶ ልጆች ሆይ በሀብታቸው ለሚታመኑ ወደ እግዚአብሔር መንግስት መግባት እንዴት ከባድ ነው አላቸው፡፡
25ሀብታም ሰው ወደ መንግስተ ሰማያት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢሾልክ ይቀላል አላቸው፡፡
26ደቀመዛሙርቱም እጅግ ተገርመው እንግዲያውስ ማን ሊድን ይችላል አሉት፡፡
27ኢየሱስም ወደ እነርሱ ተመከተና ለሰዎች ይህ አይቻልም ነገር ግን ለእግዚአብሔር ይቻላል ለእግዚአብሔር ሁሉ ይቻላልና አላቸው፡፡
28ጴጥሮስም ጌታ ሆይ እኛ ሀሉን ትተን ተከልንህ ይለው ጀመር፡፡
29ኢየሱስም እውነት እላችኋለሁ ስለኔና ስለ ወንጌል ቤቱን ወንዱሞቹን ወይም እህቶቹንወይም እናቱን ወይም አባቱን ወይም ልጆቹን ወይም መሬቱን የሚተው
30በዚህ ዓለም መቶ እጥፍ ቤቶችን ወንድሞችን እህቶችን እናቶችን ልጆችንና መሬት ከስደት ጋር በሚመጣውም አለም የዘላለምን ህይወት የማይቀበል የለም
31ነገር ግን ብዙዎች ፊተኞች ኋለኞች ኋለኞችም ፊተኞች ይሆናሉ አላቸው፡፡
32ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄዱ ሳለ ኢየሱስ ከፊት ከፊታቸው ይሄድ ነበር፡፡ እጅግም ተገርመው ነበር የሚከተሉትም በጣም ፈርተው ነበር፡፡ አስራሁለቱን እንደገና ወስዶ ሊደርስበት ያለውን ነገር ይነግራቸው ጀመር፡፡
33እነሆ ወደ ኢየሩሳሌም እንሄዳለን የሰው ልጅም ለካህናት አለቆችና ለጻፎች አልፎ ይሰጣል እነርሱም ሞትን ይፈርዱበታል ለአህዛብም አሳልፈው ይሰጡታል፡፡
34አህዛብም/ፈሪሳዊያን ይቀልዱበታል ይተፉበታል ይገርፉታል ይገድሉታልም ከሶስት ቀን በኋላም ይነሳል እያለ ይነግራቸው ጀመር፡፡
35የዘብድዮስ ልጆች ያዕቆብና ዮሀንስ ወደ ኢየሱስ ቀርበው መምህር ሆይ የምንጠይቅህን ሁሉ እንድታደርግልን እንለምንሀለን አሉት፡፡
36እርሱም ምን እንዳደርግላችሁ ትፈልጋለችሁ አላቸው፡፡
37እነርሱም በክብርህ በምትሆንበት ጊዜ አንዳችን በቀኝህ አንዳችን በግራህ እንድንቀመጥ ፍቀድ አሉት፡፡
38ኢየሱስ ግን የምትለምኑትን አታውቁም እኔ የምጠጣውን ጽዋ ልትጠጡ እኔ የምጠመቀውን ጥምቀት ልትጠመቁ ትችላላችሁን አላቸው፡፤
39እነርሱም እንችላለን አሉት፡፡ ኢየሱስም እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችሁ እኔ የምጠመቀውን ጥምቀት ትጠመቃላችሁ
40ነገር ግን በግራዬና በቀኜ መሆን ለተዘጋጀላቸው ነው እንጂ እኔ የምሰጠው አይደለም አላቸው፡፡
41አሥሩ ደቀማዘሙርትም ይህን በሰሙ ጊዜ በያዕቆብና በዮሀንስ ላይ ተቆጡ፡፡
42ኢየሱስም ወደ እርሱ ጠርቶ የአህዛብ አለቆች በሚመሩዋቸው ላይ እንደሚሠለጥኑባቸው ታላላቆቻቸውም እንደሚገዙዋቸው ታውቃላችሁ፡፡
43በእናንተ ዘንድ ግን እንዲህ አይደለም ነገር ግን ከእናንተ ማንም የበላይ(ታላቅ) ለመሆን የሚፈልግ የሁሉ አገልጋይ ይሁን
44ፊተኛ ለመሆን የሚፈልግም የሁሉ ባሪያ ይሁን
45የሰው ልጅም ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊያደርግ እንጂ እንዲያገልግሉት አልመጣም አላቸው፡፡
46ኢየሱስና ደቀመዛሙርቱም ወደ ኢያሪኮ መጡ፡፡ ከደቀመዛሙርቱና ከብዙ ህዝብ ጋር ከኢያሪኮ በመውጣት ላይ ሳለ የጤሚዮስ ልጅ ዓይነ ስወሩ ለማኝ በርጠሚዮስ በመንገድ ዳር ተቀምጦ ይለምን ነበር፡፡
47የናዝሬቱ ኢየሱስ እያለፈ መሆኑን ሲሰማ የዳዊተ ልጅ ኢየሱስ ሆይ እራራልኝ እያለ ጮኸ፡፡
48ብዙዎችም ዝም እንዲል ገሰፁት፡፡ እርሱ ግን አብዝቶ የዳዊት ልጅ ሆይ እራራልኝ ብሎ ጮኸ፡፡
49ኢየሱስም ቆመና ጥሩት አለ፡፡ እነርሱም አይዞህ መምህሩ ይጠራሀልና ተነሳ አሉት፡፡
50በርጠሚዮስም ልብሱን ጥሎ እየዘለለ ወደ ኢየሱስ መጣ፡፡
51ኢየሱስም ምን እንዳደርገልህ ትወዳለህ አለው፡፡ ዓይነ ስውሩም ሰው መምህር ሆይ ማየት እንድችል አለው፡፡
52ኢየሱስም መንገድህን ሂድ እምነትህ አድኖሀል አለው፡፡ ወዲያውም አየ ኢየሱስንም ተከትሎ ሄደ፡፡