1አንቺ የወታደር ከተማ ሰራዊትሽን አሰልፊ ከበባ ተደርጐብናልና የእስራኤልን ገዥ ጉንጩን በበትር ይመቱታል፡፡
2አንቺ ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፣ ከይሁዳ ነገዶች መካከል ትንሿ ብትሆኚም፣ ጅማሬው ከጥንት ከዘላለም ዘመናት የሆነ የእስራኤል ገዥ ከአንቺ ይወጣልኛል፡፡
3ስለዚህ ያማጠችው ልጅ እስክትወልድ ድረስ እግዚአብሔር ሕዝቡን ይተዋቸዋል የተቀሩት ወንድሞቹም ወደ እስራኤል ሕዝብ ይመለሳሉ፡፡
4በያህዌ ብርታት፣ በአምላኩ በያህዌ ስም ክብር ጸንቶ ይቆማል፤ መንጋውንም ይጠብቃል፡፡ በዚያ ጊዜ ታላቅነቱ እስከ ምድር ዳርቻ ስለሚደርስ ተደላድለው ይኖራሉ፡፡
5እርሱ ሰላማችን ይሆናል፡፡ አሦራውያን ወደ ምድራችን ሲመጡ ወደ ምሽጐቻችንም ሲገሠግሡ ሰባት እረኞችን፣ እንዲሁም ስምንት መሪዎችን እናስነሣባቸዋልን፡፡
6እነዚህ ሰዎች የአሦርን ምድር በሰይፍ፣ የናምሩዱንም ምድር እጃቸው ላይ ባለው ሰይፍ ይገዛሉ፡፡ ወደ ምድራችን ሲመጡ ወደ ድንበራችንም ሲገሠግሡ እርሱ ከአሦራውያን ይድነናል፡፡
7የያዕቆብ ትሩፍ በብዙ ሕዝብ መካከል ከያህዌ ዘንድ እንደሚወርድ ጠል፣ ሣር ላይ እንደሚጥል ካፊያ ሰውን እንደማይጠብቅ፣ በሰው ልጆችም እንደማይተማመን ሰው ይሆናል፡፡
8የያዕቆብ ትሩፍ በሕዝቦች መካከል፣ በብዙ ሕዝቦች መካከል ይሆናል፤ በዱር አራዊት መካከል እንዳለ አንበሳ፣ በበጐች መካከል እንዳለ አንበሳ ደቦል ይሆናል፡፡ በእግሩ እየረጋገጠ ይቦጫጭቃቸዋል፤ የሚያድናቸውም አይኖርም፡፡
9እጅህ በጠላቶችህ ላይ ከፍ ከፍ በማለት ያጠፋቸዋል፡፡
10በዚያ ቀን ይላል ያህዌ «ፈረሶቻችሁን ከመካከላችሁ አጠፋለሁ ሠረገሎቻችሁንም እደመስሳለሁ፡፡
11የምድራችሁን ከተሞች አጠፋለሁ ምሽጐቻችሁንም ሁሉ አፈርሳለሁ፡፡
12በምድራችሁ ያለውን ጥንቆላ አጠፋለሁ ከእንግዲህ አታሟርቱም፡፡
13የተቀረጹ ምስሎቻችሁንና የድንጋይ ዐምዶቻችሁን ከመካከላችሁ አጠፋለሁ፡፡ ከእንግዲህ የእጆቻችሁን ሥራ አታመልኩም፡፡
14የአሼራ ምሰሶዋችሁን ከምድራችሁ እነቅላለሁ ከተሞቻችሁንም አጠፋለሁ፡፡
15ያልታዘዙኝን ሕዝቦች በቀጣዬና በመዓቴ እበቀላሁ፡፡»