1በመጨረሻው ዘመን የያህዌ ቤት ተራራ ሌሎች ተራቶች ላይ ይመሠረታል ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ይላል ሕዝቦችም ወደ እርሱ ይጐርፋሉ፡፡ ብዙ ሕዝቦች መጥተው እንዲህ ይላሉ
2«ኑ ወደ ያህዌ ተራራ፣ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንሂድ እርሱ መንገዱን ያስተምረናል እኛም በመንገዱ እንሄዳለን፡፡ ሕግ ከጽዮን፣ የያህዌም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣል፡፡
3እርሱ በብዙ ሕዝብ መካከል ይፈርዳል በሩቅ ባሉ ሕዝቦችም ላይ ይበይናል፡፡ ሰይፋቸውን ቀጥቅጠው ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ ያደርጉታል፡፡ መንግሥት በመንግሥት ላይ ሰይፍ አያነሣም፤ ከእንግዲህ የጦር ትምህርት አይማሩም፡፡
4ይልቁን፣ እያንዳንዱ ሰው ከገዛ ወይኑ ሥር ከገዛ በለሱም ሥር ይቀመጣል፡፡ የሰራዊት አምላክ ያህዌ ተናግሮአልና የሚያስፈራቸው አይኖርም፡፡
5ሕዝቦች ሁሉ በአምላኮቻቸው ስም ይሄዳሉ፡፡ እኛ ግን በአምላካችን በያህዌ ስም ለዘላለም እንሄዳለን
6በዚያ ቀን ይላል ያህዌ፣ አንካሳውን እሰበስባለሁ ስደተኞችና ሐዘንተኞች ያደረግኃቸውን እሰበስባለሁ፡፡
7አንካሳውን ወደ ተረፉት ወገኖች የተገፉትንም ወደ ብርቱ ሕዝብ እመልሳለሁ፤ እኔ ያህዌ በጽዮን ተራራ ከዘላለም እስከ ዘላለም እነግሣለሁ፡፡
8አንተ የመጠበቂያው ማማ፣ የጽዮን ሴት ልጅ አምባ የቀድሞው ግዛትህ፣ የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ መንግሥት ይመለስልሃል፡፡
9አሁንስ እንደዚህ የምትጮኺው ለምንድነው? በመካከልሽ ንጉሥ የለምን? ምጥ እንደ ያዛት ሴት የምትጨነቂው መካሪሽ ስለጠፋ ነውን?
10የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ ምጥ እንደያዛት ሴት ተጨነቂ፤ አሁን ከከተማ ወጥተሸ ሜዳ ላይ ስፈሪ ወደ ባቢሎንም ትሄጃለሽ፡፡ በዚያም ከጠላት እጅ ትድኛለሽ በዚያም እግዚአብሔር ከጠላቶችሽ ይታደግሻል፡፡
11አሁን ግን፣ ብዙ ሕዝቦች አንቺ ላይ ተሰብስበዋል እነርሱም፣ «የረከሰች ትሁን፤ እኛም መፈራረስዋን እንይ» ብለዋል፡፡
12ነቢዩ እንዲህ ይላል፤ «የያህዌን ሐሳብ አያወቁም የእርሱንም ዕቅድ አያስተውሉም፤ እርሱ ዐውድማ ላይ እንደ ነዶ ይሰበስባቸዋል፡፡»
13ያህዌ እንዲህ ይላል፤ «ቀንድሽን እንደ ብረት፣ ሰኮናሽን እንደ ናስ አደርጋለሁ ብዙ ሕዝቦችን ታደቂያለሽ የጽዮን ልጅ ሆይ፣ ተነሥተሸ አበራዪ፡፡ በግፍ የሰበሰቡትን ሀብት ለራሴ ሀብታቸውንም ለምድር ሁሉ ጌታ አቀርባለሁ፡፡»