1ክፉ ነገር ለማድረግ ለሚያቅዱ መኝታቸው ላይ ሆነው ተንኰል ለሚያውጠነጥኑ ወዮላቸው፡፡ ያን ለማድረግ ሥልጣን ስላላቸው ሌሊቱ ሲነጋ ዕቅዳቸውን ሥራ ላይ ያውሉታል፡፡
2የዕርሻ ቦታ ሲፈልጉ፣ ቀምተው ይወስዳሉ ቤት ሲፈልጉ ነጥቀው ይወስዳሉ፡፡ የሰው መብት ረግጠው ሀብቱን ይዘርፋሉ
3ስለዚህ ያህዌ እንዲህ ይላል በዚያ ሕዝብ ላይ ጥፋት አመጣለሁ ከዚህም ልታመልጡ አትችሉም፡፡ ያ የመከራ ጊዜ ስለሚሆን ከእንግዲህ በእብሪት አትኖሩም፡፡
4በዚያ ቀን ጠላቶቻችሁ ይሳለቁባችኃል በሐዘን እንጉርጉሮ እንዲህ እያሉ ያፌዙባችኃል እኛ እስራኤላውያን ፈጽሞ ጠፍተናል ያህዌ የሕዝቤን ንብረት ወስዶ ርስታችንንም ለከሐሂዲዎች አከፋፈለ
5ስለዚህ እናንተ ባለጸጐች በያህዊ ጉባኤ ውስጥ ርስት በዕጣ የሚከፋፈሉ ልጆች አይኖሯችሁም፡፡
6«ትንቢት አትናገር» ምንም ውርደት አይደርስብንም፤ ስለ እነዚህ ነገሮች ትንቢት አትናገር ይላሉ፡፡
7የያዕቆብ ቤት ሆይ፣ እንደህ መባል ነበረበትን? የያህዌ ትዕግሥት አልቋልን? እነዚህስ የእርሱ ድርጊቶች ናቸውን? አካሄዳቸው ቀና ለሆነ ሰዎች ቃሎቼ መልካም አያደርጉምን?
8በመጨረሻ በሕዝቤ ላይ በጠላትነት ተነሥታችኃል ከጦርነት በኃላ ሰላም ነው ብለው ወደሚያስቡት እንደሚመለሱ ወታደሮች ምንም ሳይጠራጠሩ የሚያልፉ ሰዎችን ልብስ ገፋችኃል፡፡
9የወገኔን ሴቶች ከሚወዱት ቤታቸው አባረራችሁ በረከቴን ለዘላለም ከልጆቻቸው ወሰዳችሁ፡፡
10በርኩሰት ምክንያት ከባድ ጥፋት ስለሚመጣ እዚህ ቦታ መቆየት አትችሉም፤ ስለዚህ ተነሥታችሁ ሂዱ፡፡
11አንድ ሰው በሐሰት መንፈስ ተነሣሥቶ «ስለ ወይን ጠጅና ጠንካራ መጠጥ ትንቢት እናገራለሁ» ቢል፤ በእነዚህ ሰዎች ዘንድ እንደ ነቢይ ይቆጠራል፡፡
12ያዕቆብ ሆ በእርግጥ ሁላችሁንም እሰበስባለሁ፤ የእስራኤልን ትሩፍ ጉረኖ ውስጥ እንዳለ በጐች በመሰማሪያ ላይ እንዳለ መንጋ አመጣቸዋለሁ፡፡ ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ታላቅ ጩኸት ይሆናል፡፡
13መንገዳቸውን የሚከፍትላቸው መሪ ከእነርሱ ፊት ፊት ይሄዳል እነርሱም ተግተልትለው በበሩ ይወጣሉ ንጉሣቸው ፊት ፊታቸው ይሄዳል፤ ያህዌ መሪያቸው ይሆናል፡፡