መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ትንቢተ ሚክያስ 1

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በይሁዳ ንጉሦች በአዮአታም፣ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን ወደ ሞሬታዊው ወደ ሚክያስ የመጣው የያህዌ ቃል፣ ስለ ሰማርያና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ራእይ ይህ ነው፡፡
2እናንት ሕዝቦች ስሙ ምድርና በውስጧ የምትኖሩ ሁሉ አድምጡ፡፡ ጌታ ከቅዱስ መቅደሱ፣ ጌታ ያህዌም ይመሰክርባችኃል፡፡
3ተመልከቱ፤ ያህዌ ከመኖሪያው ስፍራ ይመጣል፤ ‹ወርዶም፣ በምድር ከፍታዎች ላይ ይራመዳል፡፡
4ተራሮች ከሥሩ ይቀልጣሉ ሸለቆዎች ይሰነጠቃሉ እሳት ፊት እንዳለም ሰም በገደል ላይ እንደሚወርድ ውሆች ይሆናሉ፡፡
5ይህ ሁሉ የሚሆነው ከያዕቆብ ዐመፅ ከእስራኤልም ቤት ኃጢአት የተነሣ ነው፡፡ የያዕቆብ ዐመፅ ምክንያት ምን ነበር? ሰማርያ አይደለችምን? የይሁዳስ ኮረብታ መስገጃ ምንድው? ኢየሩሳሌም አይደለችምን?
6ስለዚህ ሰማርያን ሜዳ ላይ እንዳለ ፍርስራሽ ክምር፣ ወይን እንደሚተከልባትም ቦታ አደርጋታለሁ፡፡ የከተማዋን ፍርስራሽ ድንጋይ ወደ ሸለቆው አወርዳለሁ፤ መሠረቶችዋንም እገልጣለሁ፡፡
7ምስሎቿ ሁሉ ይሰባበራሉ፤ ለእርሷ የተሰጡ ስጦታዎችም ይቃጠላሉ፡፡ ጣዎቶችዋም ሁሉ ለጥፋት ይሆናሉ፡፡ እነዚህን የሰበሰበችው ለዝሙት ሥራዋ ካገኘችው ገጸ በረከት እንደ ነበር ሁሉ አሁንም ገጸ በረከትዋ የዝሙት አዳሪነት ዋጋ መቀበያ ይሆናል፡፡
8በዚህ ምክንያት ዋይ ዋይ እያልሁ አለቅሳለሁ፤ ባዶ እግሬንና ዕርቃኔን እሄዳለሁ፤ እንደ ቀበሮ አላዝናለሁ እንደ ጉጉትም አለቅሳለሁ፡፡
9ቁስሏ የማይፈወስ ነውና ለይሁም ተርፏል፡፡ ወደ ሕዝቤ ደጅ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ደርሷል
10በጌት አታውሩ፣ ከቶም አታልቅሱ በቤትዓፍራ ትቢያ ላይ እንከባለላለሁ
11እናንት በሻፊር የምትሮሩ ዕርቃናችሁን ሆናችሁ እለፉ፡፡ በጸዓናን የሚኖሩ ከዚያ አይወጡም፡፡ ቤትዔጼል ሐዘን ላይ ስለሆነች መጠጊያ ልትሆን አትችልም፡፡
12የማሮት ነዋሪዎች መልካም ዜና ለመስማት እጅግ ጓጉተዋል፤ ምክንያቱም ከያህዌ ዘንድ ጥፋት እስከ ኢየሩሌም ደጆች መጥቷል፡፡
13እናንት በለኪሶ የምትኖሩ የሰረገሎችን ፈረሶች ለጉሙ፣ ለጽዮን ሴት ልጅ ኃጢአት መጀመሪያ እናንተ ነበራችሁ፡፡ የእስራኤልም በደል አንተ ዘንድ ተገኝቷል፡፡
14ስለዚህ እናንተ ለሞሬሴት ጌት የመሰነባበቻ ስጦታ ትሰጣላችሁ፤ የአክዚብም ከተሞች የእስራኤልን ንጉሦች ያታልላሉ፡፡
15እናንት በመሪሳ የምትኖሩ ወራሪ አመጣባችኃለሁ፡፡ የተከበሩ የእስራኤል መሪዎች በዓዶላም ዋሻ ይሸሸጋሉ፡፡
16ደስ ትሰኙባቸው ለነበሩ ልጆቻችሁ በማዘን ራሳችሁን ተላጩ ጡራችሁን ተቆረጡ ራሳችሁን እንደ ንስር ራስ ተመለጡት ምክንያቱም ልጆቻችሁ በምርኮ ከእናንተ ይወሰዳሉና፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።