መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

የማቴዎስ 3

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1በእነዚያ ቀኖች መጥምቁ ዮሐንስ በይሁዳ ምድረ በዳ ፤
2"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ" እያለ እየሰበከ መጣ።
3በነቢዩ ኢሳይያስ፦ "ምድረ በዳ ውስጥ የሚጮኽ ሰው ድምፅ፣ የጌታን መንገድ አዘጋጁ፣ ጎዳናዎቹንም አስተካክሉ" ተብሎ የተነገረለት ይህ ነውና።
4ዮሐንስ ይለብስ የነበረው የግመል ጠጕር፣ በወገቡ የሚታጠቀውም የቆዳ ጠፍር ነው፤ ምግቡም አንበጣና የዱር ማር ነበረ።
5በዚያ ጊዜ ኢየሩሳሌም፣ መላው ይሁዳና በዮርዳኖስ ወንዝ ዙሪያ ያለ አገር ሁሉ ወደ እርሱ ይመጡ ነበር።
6ሕዝቡ ኀጢአታቸውን እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ በእርሱ እጅ ተጠመቁ።
7ነገር ግን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ለመጠመቅ ወደ እርሱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፣ "እናንተ የመርዛማ እባቦች ልጆች ከሚመጣው ቊጣ ለማምለጥ ማን አስጠነቀቃችሁ?
8ለንስሐ የሚጠቅም ፍሬ ይኑራችሁ።
9ለራሳችሁም አብርሃም አባታችን አለን" ብላችሁ አታስቡ። እግዚአብሔር ከእነዚህ ድንጋዮች እንኳ ለአብርሃም ልጆችን ማስነሣት እንደሚችል እነግራችኋለሁና።
10አሁን መጥረቢያው በዛፎቹ ሥር ተቀምጦአል። ስለዚህ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል በእሳት ውስጥም ይጣላል።
11እኔ ለንስሐ የማጠምቃችሁ በውሃ ነው፤ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቃል፤ ጫማውን መሸከምም እንኳ አይገባኝም። እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል።
12ዐውድማውን ፈጽሞ ለማጥራትና ስንዴውን በጎተራ ውስጥ ለመክተት መንሹ በእጁ ነው። ገለባውን ግን ፈጽሞ በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።
13ከዚያም ኢየሱስ በዮሐንስ እጅ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ መጣ።
14ነገር ግን "እኔ አንተ እንድታጠምቀኝ ሲገባ፣ አንተ እንዴት ወደ እኔ ትመጣለህ?" በማለት ሊያስቆመው ሞከረ።
15ኢየሱስም መልሶ፣ "አሁን ይህን ፍቀድ፤ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ለእኛ ተገቢ ነውና" አለው። ከዚያም በኋላ ዮሐንስ ፈቀደለት።
16ኢየሱስ ከተጠመቀ በኋላ፣ ወዲያውኑ ከውሃ ውስጥ ወጣ፤ እነሆም ሰማያት ተከፈቱ። የእግዚአብሔር መንፈስ በርግብ መልክ ሲወርድና በእርሱ ላይ ሲቀመጥ አየ።
17እነሆ፣ የምወደው ልጄ ይህ ነው። "በእርሱ እጅግ ደስ ይለኛል" የሚል ድምፅ ከሰማያት መጣ።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።