መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

የማቴዎስ 16

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያንም መጥተው ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው በመጠየቅ ኢየሱስን ፈተኑት፡፡
2ነገር ግን ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አላቸው፣ "በመሸ ጊዜ ሰማዩ ቀልቷልና ዝናብ አይኖርም ትላላችሁ
3በነጋ ጊዜም፣ ‹ዛሬ ሰማዩ ስለ ጠቈረ ይዘንባል› ትላላችሁ፤ የዘመኑን ምልክት ግን መለየት አትችሉም፡፡
4ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፤ ነገር ግን ከነቢዩ ከዮናስ ምልክት በቀር ሌላ ምልክት አይሰጠውም፡፡" ከዚያም ኢየሱስ ትቶአቸው ሄደ፡፡
5ደቀ መዛሙርቱ ወደ ማዶ ተሻገሩ፤ እንጀራ መያዝን ግን ረሱ፡፡
6ኢየሱስ፣ "ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠንቀቁ፣ ተጠበቁም" አላቸው፡፡
7ደቀ መዛሙርቱ፣ "እንጀራ ስላልያዝን ነው" ብለው እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ፡፡
8ኢየሱስ ይህን ዐውቆ፣ "እናንተ እምነተ ጎደሎዎች፣ እንጀራ ስላልያዝን ነው ብላችሁ ስለ ምን እርስ በርሳችሁ ትነጋገራላችሁ?"
9ዐምስት እንጀራ ለዐምስቱ ሺህ እንደ በቃና ስንት ቅርጫት እንደ ሰበሰባችሁ አሁንም አታስተውሉም ወይም አታስታውሱም?
10ወይም ደግሞ ሰባቱ እንጀራ ለአራቱ ሺህ እንደ በቃና ስንት ቅርጫት እንዳነሣችሁስ አታስታውሱምን?
11እኔ የነገርኋችሁ ስለ እንጀራ እንዳልነበረ እንዴት ነው የማታስተውሉት? ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያ እርሾ ተጠንቀቁ፣ ተጠበቁም፡፡"
12ከዚያም እርሱ ሲነግራቸው የነበረው ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ትምህርት እንዲጠበቁ እንጂ፣ ስለ እንጀራ እርሾ እንዳልነበረ ተረዱ፡፡
13ኢየሱስም ወደ ቂሣርያ ፊልጶስ ክልል በመጣ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፣ "ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ነው ይላሉ?" በማለት ጠየቃቸው፡፡
14እነርሱ፣ እንዲህ አሉ፤ "አንዳንዶች መጥምቁ ዮሐንስ፣ ሌሎች ኤልያስ፣ የቀሩትም ኤርምያስ፣ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ፡፡"
15"እናንተስ እኔን ማን ትሉኛላችሁ?" አላቸው፡፡
16ስምዖን ጴጥሮስ፣ "አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ" በማለት መልስ ሰጠ፡፡
17ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለው፣ "የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፣ አንተ የተባረክህ ነህ፤ ይህን የገለጠልህ የሰማዩ አባቴ ነው እንጂ፣ ሥጋና ደም አይደለም፡፡
18ደግሞም አንተ ጴጥሮስ ነህም እላለሁ፤ በዚህም አለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ የገሃነም ደጆችም አያሸንፏትም፡፡
19እኔ የመንግሥተ ሰማያትን መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፡፡ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፤ በምድር የምትፈታውም ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል፡፡››
20ከዚያም ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ መሆኑን ለማንም እንዳይናገሩ ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው፡፡
21ከዚያን ጊዜ አንሥቶ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም መሄድ፣ በሽማግሌዎችና በካህናት አለቆች፣ በፈሪሳውያንና በሕግ መምህራንም እጅ ብዙ መከራ መቀበልና መገደል፣ በሦስተኛውም ቀን መነሣት እንዳለበት ለደቀ መዛሙርቱ ይነግራቸው ጀመር፡፡
22ከዚያም ጴጥሮስ ኢየሱስን ለብቻው ገለል አድርጎ፣ "ጌታ ሆይ፣ ይህ ከአንተ ይራቅ፤ ይህም ከቶ አይሁንብህ" በማለት ገሠጸው፡፡
23ኢየሱስ ግን ዞር ብሎ ጴጥሮስን፣ "ከፊቴ ዞር በል፣ ሰይጣን! ስለ ሰው እንጂ ስለ እግዚአብሔር ነገር ደንታ የለህምና አንተ ለእኔ እንቅፋት ነህ" አለው፡፡
24ከዚያም በኋላ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፤ "ሊከተለኝ የሚፈልግ ማንም ቢኖር፣ ራሱን መካድ፣ የራሱን መስቀል መሸከምና እኔን መከተል አለበት፡፡
25ሕይወቱን ለማዳን የሚፈልግ ሁሉ ያጣዋል፤ ስለ እኔ ሕይወቱን የሚያጣ ግን ያገኘዋል፡፡
26ሰው ሙሉውን ዓለም የራሱ ቢያደርግ ሕይወቱን ግን ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ሰው በሕይወቱ ፈንታ ምን መስጠት ይችላል?
27የሰው ልጅ በአባቱ ክብር ከመላእክቱ ጋር ይመጣልና፡፡ ከዚያም ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው ይከፍለዋል፡፡
28እውነት እላችኋለሁ፤ እዚህ ከቆማችሁት መካከል የሰው ልጅ በመንግሥቱ ሲመጣ እስኪያዩ ድረስ ሞትን የማይቀምሱ አንዳንዶች አሉ፡፡"
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።