1በዚያን ጊዜ፣ የአራተኛው ክፍል ገዢ የነበረው ሄሮድስ ስለ ኢየሱስ ሰማ።
2አገልጋዮቹንም፣ "ይህ መጥምቁ ዮሐንስ ነው። ስለዚህ ይህ ሁሉ ኅይል በእርሱ የሚሠራው ከሞት ስለ ተነሣ ነው" አላቸው።
3ሄሮድስ፣ በወንድሙ በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት፣ ይዞ አሳስሮት ነበርና፡፡
4ምክንያቱም ዮሐንስ፣ "እርሷን ማግባትህ ተገቢ አይደለም" ይለው ነበር።
5ሄሮድስ ሊያስገድለው ፈልጎ፣ ሕዝቡን ፈራ፣ ምክንያቱም ሕዝቡ ዮሐንስን እንደ ነቢይ ያዩት ነበር።
6ነገር ግን በሄሮድስ የልደት ቀን፣ የሄሮድያዳ ልጅ በመካከል ስትጨፍር፣ ሄሮድስን ደስ አሰኘችው።
7በዚህም ምክንያት፣ የምትጠይቀውን ሁሉ እንደሚሰጣት በመሓላ ቃል ገባላት።
8በእናቷም ተመክራ፣ “የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ እዚሁ፣ በሳሕን አድርገህ ስጠኝ” አለችው።
9ንጉሡ በጥያቄዋ በጣም ዐዘነ፣ ነገር ግን በመሓላውና ከእርሱ ጋር እራት ላይ በነበሩት ምክንያት፣ የተናገረው እንዲፈጸም አዘዘ።
10ሰው ልኮ፣ በወህኒ ቤት የዮሐንስን ራስ አስቈረጠ።
11ከዚያም ራሱ በሳሕን ተደርጎ ለልጅቱ ተሰጣት፣ እርሷም ለእናቷ ወስዳ ሰጠች።
12ከዚያም የእርሱ ደቀ መዛሙርት መጥተው፣ በድኑን ወስደው ቀበሩት። ከዚህ በኋላ ሄደው ለኢየሱስ ነገሩት።
13ኢየሱስም ይህን በሰማ ጊዜ፣ በጀልባ ገለል ወዳለ ቦታ ሄደ። ሕዝቡም ይህን በሰሙ ጊዜ ፣ ከየከተሞቹ በእግር ተከተሉት።
14ከዚያም ኢየሱስ ቀድሞአቸው መጥቶ ብዙ ሕዝብ አየና ራራላቸው፣ ሕመምተኞቻቸውንም ፈወሰ።
15በመሸም ጊዜ፣ ደቀ መዛሙርቱ መጡና፣ “ቀኑ መሽቷል ይህም ስፍራ ምድረ በዳ ነው ። ሕዝቡን ወደ መንደሮች እንዲሄዱና፣ ለራሳቸው ምግብ እንዲገዙ አሰናብት" አሉት።
16ኢየሱስ ግን፣ "መሄድ አያስፈልጋቸውም፤ እናንተው የሚበሉትን ስጧቸው" አላቸው።
17እነርሱም፣ “ እኛ ያለን አምስት እንጀራና ሁለት ዐሣ ብቻ ነው" አሉት።
18ኢየሱስም፣ "እነርሱኑ ወደ እኔ አምጡአቸው" አለ።
19ከዚያም ኢየሱስ ሣሩ ላይ እንዲቀምጡ ሕዝቡን አዘዘ። ዐምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዐሣ ወሰደ፣ ወደ ሰማይ አሻቅቦ እያየ፣ አመሰገነ፤ እንጀራውንም ቈርሶ፣ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፤ ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ ሰጡ።
20ሁሉም በልተው ጠገቡ፡፡ ከዚያም የተረፈውን ዐሥራ ሁለት መሶብ ሙሉ ቊርስራሽ ሰበሰቡ።
21የበሉትም፣ ከሴቶችና ከልጆች ሌላ፣ ዐምስት ሺ ያህል ወንዶች ነበሩ።
22እርሱም ሕዝቡን እያሰናበተ እያለ፣ ደቀ መዛሙርቱን ወዲያው ወደ ጀልባ ገብተው፣ ከእርሱ በፊት ወደ ማዶ እንዲሄዱ አዘዛቸው።
23ሕዝቡን ካሰናበተ በኋላ፣ ብቻውን ለመጸለይ ወደ ተራራ ወጣ። በመሸ ጊዜ፣ በዚያ እርሱ ብቻውን ነበር።
24ጀልባዋ በባሕሩ መካከል እያለች፤ ከተቃራኒ አቅጣጫ ይነፍስ ስለ ነበር፣ በማዕበሉ ክፉኛ ትንገላታ ነበር።
25ከምሽቱ በአራተኛው ክፍል፣ ኢየሱስ በባሕሩ ላይ እየተራመደ ወደ እነርሱ እየመጣ ነበር።
26ደቀ መዛሙርቱም በባሕር ላይ እየተራመደ ሲያዩት፣ እጅግ ደንግጠው፣ “መንፈስ ነው”ብለው በፍርሀት ጮኹ።
27ኢየሱስ ግን ወዲያውኑ፣ “አይዟችሁ! እኔ ነኝ! አትፍሩ” ብሎ ተናገራቸው።
28ጴጥሮስም መልሶ፣ “ጌታ ሆይ፣ አንተስ ከሆንህ፣ በውሃው ላይ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ" አለው።
29ኢየሱስም፣ “ና" አለው። ስለዚህ ጴጥሮስ ከጀልባው ወጥቶ ወደ ኢየሱስ ለመሄድ፣ በውሃው ላይ ተራመደ።
30ነገር ግን ጴጥሮስ ነፋሱን አይቶ በመፍራት፣ መስጠም በጀመረ ጊዜ ፣ “ጌታ ሆይ፣ አድነኝ” ብሎ ጮኸ።
31ኢየሱስም ያኔውኑ እጁን ዘርግቶ ጴጥሮስን ያዘውና፣ “አንተ እምነት የጎደለህ፣ ለምን ትጠራጠራለህ?” አለው።
32ከዚያም ኢየሱስና ጴጥሮስ ወደ ጀልባው በገቡ ጊዜ፣ ነፋሱ መንፈሱን አቆመ።
33በጀልባው ውስጥ የነበሩት ደቀ መዛሙርትም ኢየሱስን፣ “አንተ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነህ” ብለው ሰገዱለት።
34ከተሻገሩም በኋላ፣ ጌንሳሬጥ ወደ ተባለ አገር መጡ።
35በዚያም ስፍራ የነበሩ ሰዎች ኢየሱስ መሆኑን ባወቁ ጊዜ፣ በአካባቢው ወዳለ ስፍራ ሁሉ መልእክት ላኩና፣ የታመመውን ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ።
36የልብሱን ጫፍ ብቻ ለመንካት ለመኑት፣ የነኩትም ሁሉ ተፈወሱ።