1“እነሆ፣ መልእክተኝዬን እልካለሁ፤ እርሱም መንገዴን በፊቴ ያዘጋጃል። እናንተ የምትፈልጉትም ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ የመጣል። ደስ የምትሰኙበትን የቃል ኪዳኑ መልእክተፍኛ ለመጣ ነው” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ።
2እርሱ የሚመጠበትን ቀን ማን መቋቋም ይችላል? እርሱ ሲገለጥ ማን ፊቱ መቆም ይችላል? ምክናቱም እርሱ እንደ አንጥረኛ እሳት፣ እንደ ለብስ አጠቢ ሳሙና ነው።
3ብር እንደሚያጠራና እንደ እንደሚያነጻ ሰው ይቀመጣል፤ የሌዊንም ልጆች ያጠራል እንደወርቅና እንደብር ያጠራቸዋል፤ እነርሱም የጽድቅን ቁርባን ለያህዌ ያመጣሉ።
4ያኔ የይሁዳና የኢየሩሳሌም ቁርባን እንደ ቀድሞ ዘመን፣ እንደጥንቱም ዘመን ያህዌን ደስ ያሰኘዋል።
5“በዚያ ጊዜ እኔ ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ። በመተተኞችና በአመንዝራዎች ላይ፣ በሐሰተኛ ምስክሮችና የሠራተኞቻቸውን ደመወዝ በሚከለክሉ ላይ፣ መበለቶችንና ድኻ አደጉን በሚጨቁን ላይ፣ መጻተኞችን ፍትሕ በሚነፍጉ ላይ፣ እኔንም በማያከብሩ ላይ በፍጥነት እመሰክርባቸዋለሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ።
6እኔ ያህዌ አልተለወጥሁም፤ ስለዚህ እናንተ የያዕቆብ ልጆች አልጠፋችሁም።
7ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከትእዛዞቼ ፈቀቅ ብላችኋል፤ እነርሱንም አልጠበቃችሁም። ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ። እናንተ ግን፣ “የምንመለሰው እንዴት ነው?” ብላችኋል።
8ሰው ከእግዚአብሔር ይሰርቃልን? እናንተ ግን ከእኔ ሰርቃችኋል፤ ያም ሆኖ ግን፣ “ከአንተ የሰረቅነው እንዴት ነው?” ብላችኋል። በዐሥራትና በበኩራት ነው።
9እናንተም ሆናችሁ መላው ሕዝብ ከእኔ ሰርቃችኋልና የተረገማችሁ ናችሁ።
10በቤቴ መብል እንዲኖር ሙሉ አስራት ወደጎተራ አስገቡ። “በቂ ቦታ እስከማይኖራችሁ ድረስ የሰማይን መስኮት ከፍቼ በረከትን ባላፈስስላችሁ በዚህ አሁን ፈትኑኝ” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ።
11የምድራችሁን ፍሬ እንዳያጠፋ እህላችሁን የሚያጠፉትን እገሥጻለሁ። እርሻ ላይ ያለው የወይን ተክላችሁም ፍሬ አልባ አይሆንም” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ።
12የምድር ደስታ ስለምትሆኑ ሕዝቦች ሁሉ ቡሩካን ብለው ይጠሯችኋል” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ።
13“እኔ ላይ የድፍረት ቃል ተናግራችኋል” ይላል ያህዌ። እናንተ ግን፣ “በአንተ ላይ የተናገርነው ምንድነው?” ትላላችሁ።
14“እግዚአብሔርን ማገልገል ከንቱ ነው ብላችኋል። የእርሱን ትእዛዞች መጠበቅ፣ ወይም በሠራዊት ጌታ በያህዌ ፊት ሐዘንተኞች ሆነን መመላለሳችን ጥቅሙ ምንድነው?” ብላችኋል።
15ስለዚህም አሁን እብሪተኞችን ቡሩካን እንላቸዋለን። ክፉ አድራጊዎችን መበልጸግ ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔርን የሚፈታተኑትም ያመልጣሉ።
16ከዚያም ያህዌን የሚፈሩ እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ። እግዚአብሔርም ሰማ፤ አደመጠም፤ ያህዌን ስለሚፈሩትና ስሙንም ስለሚያከብሩት ሰዎች በፊቱ መታሰቢያ እንዲሆን ተጻፈ።
17“እነርሱ የእኔ ይሆናሉ” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ፣ “እኔ በምሠራበት ቀን ርስቴ ይሆናሉ። ለሚያገለግለው ልጁ እንደሚራራ ሰው እኔም እራራላቸዋለሁ።
18በጻድቁና በዐመፀኛው መካከል፣ እግዚአብሔርን በሚያመልኩና እርሱን በማያመልኩ መካከል እንደገና ትለያላችሁ።