መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ትንቢተ ሚልክያስ 4

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1“እብሪተኞችና ክፉ አድራጊዎች በሙሉ ገለባ የሚሆኑበት እንደምድጃ እሳት የሚነድ ቀን ይመጣል። የሚመጣው ቀን ያነዳቸዋል” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ፤ “ሥርም ሆን ቅርንጫፍ አይተውላቸውም።
2ስሜን ለምትፈሩ ለእናንተ ግን ፈውስ በክንፎቹ የያዘ የጽድቅ ፀሐይ ይወጣላቸዋል። እናንተም ከጋጥ እንደተለቀቁ እንቦሳ እየቦረቃችሁ ትወጣላችሁ።
3እኔ በምሠራበት ቀን ዐመፀኛውን ትረግጣላችሁ፤ ከእግራችሁ ጫማ በታች ዐመድ ይሆናሉ” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ።
4ለእስራኤል ሁሉ ሕጎችና ሥርዐቶች ይሆኑ ዘንድ ለአገልጋዬ ለሙሴ በኮሬብ የሰጠሁትን ትምህርቶች አስታውሱ።
5ታላቁና አስፈሪው የያህዌ ቀን ከመምጣቱ በፊት ነቢዩ ኤልያስን እልክላችኋለሁ።
6መጥቼ ምድርን ፈጽሜ እንዳላጠፋ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የልጆችንም ልብ ውደ አባቶች ይመልሳል።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።