1ሕዝቡ በጠቅላላ ተነሥተው ቆሙ፣ ኢየሱስንም በጲላጦስ ፊት አቀረቡት።
2“ይህ ሰው ራሱን ክርስቶስ፣ ንጉሥ ነኝ ሲልና ለቄሣር ግብር እንዳይከፈል በመከልከል አገር ሲበጠብጥ አግኝተነዋል” በማለት ይከሱት ጀመር።
3ጲላጦስ፣ “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?” በማለት ጠየቀው። ኢየሱስም፣ “አንተ አልህ” ብሎ መለሰለት።
4ጲላጦስ የካህናት አለቆችንና የተሰበሰቡትን ሕዝብ፣ “በዚህ ሰው ምንም ስሕተት አላገኘሁበትም” አላቸው።
5እነርሱ ግን፣ “ከገሊላ ጀምሮ በመላው ይሁዳ፣ እስከዚህ ስፍራም እንኳ እያስተማረ ሕዝቡን ያነሣሣል” በማለት አጥብቀው ተናገሩ።
6ስለዚህ ጲላጦስ ይህን በሰማ ጊዜ ሰውየው ገሊላዊ እንደ ሆነ አጠያየቀ።
7ከሄሮድስ ሥልጣን በታች እንደ ሆነ ተረድቶ በዚያው ሰሞን ኢየሱስን በኢየሩሳሌም ወደ ነበረው ሄሮድስ ላከው።
8ሄሮድስ ኢየሱስን ባየው ጊዜ በጣም ደስ አለው፣ ምክንያቱም ለረጅም ጊዜ ሊያየው ሲፈልግ ነበር። ስለ እርሱ ሰምቶ የነበረ ሲሆን፣ አንዳንድ ተአምራት ሲያደርግ ለማየትም ተስፋ ነበረው።
9ሄሮድስ ኢየሱስን በብዙ ቃሎች ቢጠይቅም፣ ኢየሱስ ግን ምንም መልስ አልሰጠውም።
10በዚህ ጊዜ የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን ተነሥተው ቆሙና በኅይለ ቃል ከሰሱት።
11ሄሮድስ ከወታደሮቹ ጋር በመሆን ኢየሱስን ሰደበው፣ አላገጠበትም፤ ጥሩ ልብስ ካለበሰው በኋላ መልሶ ወደ ሄሮድስ ላከው።
12ከዚያን ቀን ጀምሮ ሄሮድስና ጲላጦስ ወዳጆች ሆኑ (ከዚያ በፊት አንዱ የአንዱ ጠበኞች ነበሩ)።
13ከዚያም ጲላጦስ የካህናት አለቆችን፣ ገዢዎችንና ሕዝቡን አንድ ላይ ጠራ፤
14እንዲህም አላቸው፤ “ ይህን ሰው ሰዎችን ለክፉ ድርጊት የሚያነሣሣ አድርጋችሁ ወደ እኔ አመጣችሁት፣ እኔም በፊታችሁ ከጠየቅሁት በኋላ ፣ እነሆ፣ እርሱን በምትከሱባቸው ነገሮች ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም።
15ሄሮድስም ቢሆን ምንም ነገር አላገኘበትም፤ ምክንያቱም መልሶ ወደ እኛ ልኮታልና፤ እነሆ፣ እርሱን ለሞት የሚያደርስ በዚህ ሰው የተፈጸመ ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም።
16ስለዚህ ቀጥቼው እለቀዋለሁ።" ጲላጦስም በበዓሉ ለአይሁድ አንድ እስረኛ የመፍታት ግዴታ ነበረበት።
18ነገር ግን እነርሱ በአንድነት፣ “ይህን ሰው አስወግደው፣ በርናባስን ለእኛ ፍታልን!" በማለት ጮኹ።
19በርናባስ በከተማይቱ ውስጥ አንድ ዐይነት ዐመፅና ግድያ በመፈጸም የታሰረ ሰው ነበር።
20ጲላጦስ ኢየሱስን ሊፈታ ፈልጎ እንደ ገና ሕዝቡን አነጋገራቸው።
21ነገር ግን ሕዝቡ፣ “ስቀለው፣ ስቀለው” እያሉ ጮኹ።
22ለሦስተኛ ጊዜም እንዲህ አላቸው፤ “ለምን? ይህ ሰው የሠራው ክፋት ምንድን ነው? ለሞት ቅጣት የሚያበቃ ነገር አላገኘሁበትም። ስለዚህ ቀጥቼው እለቀዋለሁ።”
23እነርሱ ግን ኢየሱስ እንዲሰቀል በመጠየቅ ሳያቋርጡ አብዝተው ጮኹ። ጩኸታቸውም ጲላጦስን አሳመነው።
24ስለዚህ ጲላጦስ ፍላጎታቸውን ለማሟለት ወሰነ።
25እንዲፈታላቸው የጠየቁትን፣ በዐመፅና በግድያ ምክንያት የታሰረውን ሰው ለቀቀላቸው። ኢየሱስን ግን ለፈቃዳቸው አሳልፎ ሰጠው።
26እየወሰዱት ሳሉ፣ ከገጠር ይመጣ የነበረ ስምዖን የተባለ የቀሬናን ሰው ያዙና ኢየሱስ ይሸከመው የነበረውን መስቀል አሸከሙት።
27እጅግ ብዙ ሕዝብና ለእርሱ የሚያዝኑና የሚያለቅሱ ሴቶች ይከተሉት ነበር።
28ኢየሱስም ወደ እነርሱ ዞር ብሎ፣ “የኢየሩሳሌም ሴቶች ሆይ፣ ለእኔ ሳይሆን ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ አልቅሱ” አለ።
29እነሆ፣ 'መካን የሆኑና ያልወለዱ ማኅፀኖች እንዲሁም ያላጠቡ ጡቶች የተባረኩ ናቸው' የሚሉባቸው ቀኖች ይመጣሉና።
30ከዚያም ተራሮችን፣ 'በላያችን ውደቁ፣ ኮረብቶችንም ክደኑን ማለትይጀምራሉ።'
31ዛፉ እርጥብ እያለ ይህን ነገር ካደረጉ፣ በሚደርቅበት ጊዜ ምን ይሆናል?"
32ሌሎች ሁለት ወንጀለኞችም ከእርሱ ጋር ሊገደሉ ተወሰዱ።
33የራስ ቅል ወደሚባል ቦታ በደረሱ ጊዜ፣ እርሱን ከሌሎች ሁለት ወንጀለኞች ጋር ሰቀሉት፥ አንደኛው በቀኙ ሌላኛው በግራው ነበሩ።
34ኢየሱስ፣”አባት ሆይ፣ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” አለ። ዕጣ ተጣጥለውም ልብሱን ተከፋፈሉ።
35“ሌሎችን አዳነ፣ እርሱ በእግዚአብሔር የተመረጠ ክርስቶስ ከሆነ አስኪ ራሱን ያድን” በማለት ገዢዎቹ እየዘበቱበት ሳለ ሕዝቡ ቆመው ያዩ ነበር።
36ወታደሮቹም ወደ እርሱ ቀርበው፣
37“አንተ ንጉሥ ከሆንህ ራስህን አድን” በማለት እያሾፉበት ኮምጣጤ ሰጡት።
38“የአይሁድ ንጉሥ” የሚል ምልክትም ከበላዩ ተደርጎ ነበር።
39ከተሰቀሉት ወንጀለኞች አንዱ፣ "አንተ ክርስቶስ ነህን? ራስህንም እኛንም አድን” በማለት ሰደበው።
40ሌላኛው ግን እየገሠጸው፣ “ከፍርድ በታች ሆነህ እግዚአብሔርን አትፈራምን? እኛ በዚህ ያለነው እንደ ሥራችን ስለ ሆነ፣ ትክክል ነው፣
41ነገር ግን ይህ ሰው ምንም ጥፋት አላደረገም” ብሎ መለሰለት።
42ቀጥሎም፣ “ኢየሱስ ሆይ፣ በመንግሥትህ ስትመጣ አስታውሰኝ” አለ።
43ኢየሱስ፣ “እውነት እልሃለሁ፣ ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ትሆናለህ” አለው።
44ጊዜው ስድስት ሰዓት ገደማ ነበር፣ የፀሐይ ብርሃን በመቋረጡ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ላይ ጨለማ ሆነ።
45ከዚያም የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከመሐል ተቀደደ።
46ኢየሱስ፣ “አባት ሆይ፣ ነፍሴን በእጅህ አኖራለሁ” በማለት በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህን ከተናገረ በኋላ ሞተ።
47መቶ አለቃው የተደረገውን ነገር ባየ ጊዜ፣ “ይህ ሰው በእውነት ጻድቅ ነበር” በማለት እግዚአብሔርን አከበረ።
48ሁኔታውን ለማየት እጅግ ብዙ ሰዎች በመጡ ጊዜ፣ የተደረጉትን ነገሮች አይተው ደረታቸውን እየደቁ ተመለሱ።
49ነገር ግን ከገሊላ ጀምሮ የተከተሉት አንዳንድ ወንዶችና ሴቶች ከርቀት ቆመው ይህን ድርጊት ይከታተሉ ነበር።
50እነሆ፣ የእግዚአብሔርን መንግሥት መምጣት የሚጠባበቅ፣ ከአይሁድ ከተማ፣ ከአርማቲያ የሆነ ዮሴፍ የሚባል
51(በውሳኔያቸውና በድርጊታቸው ያልተስማማ) አንድ መልካምና ጻድቅ ሰው ነበረ።
52ይህ ሰው ወደ ጲላጦስ በመቅረብ የኢየሱስን አስከሬን እንዲሰጠው ጠየቀው።
53አስክሬኑን አውርዶ በጥሩ የተልባ እግር ጨርቅ ከፈነውና ማንም ባልተቀበረበት ከድንጋይ በተወቀረ መቃብር ውስጥ አኖረው።
54ጊዜው የዝግጅት ቀን የነበረ ሲሆን፣ ሰንበትም እየገባ ነበር።
55ከእርሱ ጋር ከገሊላ የመጡ ሴቶች ተከትለውት በመሄድ መቃብሩንና አስከሬኑ እንዴት እንዳረፈ አዩ።
56ከዚያም ተመልሰው ቅመማ ቅመምና ቅባቶችን አዘጋጁ። ሰንበት ስለ ነበር በሕጉ መሠረት ዐረፉ።