መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ሉቃስ 21

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ኢየሱስ ቀና ብሎ ሲመለከት ሀብታም ሰዎች በመባ መሰብሰቢያ ሣጥን ውስጥ ገንዘብ ሲጨምሩ አየ።
2አንዲት ድኻ መበለት ደግሞ ሁለት ሳንቲሞችን ስትጨምር አየ።
3ስለዚህ እንዲህ አለ፣ "እውነት እላችኋለሁ፣ ይህች ድኻ መበለት ከሁሉም የበለጠ ሰጠች።
4እነዚህ ሁሉ የሰጡት ስጦታ ከተትረፈረፈ ሀብታቸው ነው። ይህች መበለት ግን በድኽነቷ መተዳደሪያዋን ሁሉ ሰጠች።"
5አንዳንዶች ቤተ መቅደሱ በተዋቡ ድንጋዮች እንዴት እንዳማረና እንዳጌጠ ሲናገሩ ሰምቶ እንዲህ አለ፣
6"እነዚህ የምታዩአቸው ነገሮች፣ እንዲህ እንደተነባበሩ የማይቆዩበትና የሚፈራርሱበት ጊዜ ይመጣል" አለ።
7ስለዚህ፣ "መምህር ሆይ፣ እነዚህ ነገሮች የሚሆኑት መቼ ነው? እነዚህ ነገሮች እንደሚፈጸሙ ምልክቱስ ምንድን ነው?" በማለት ጠየቁት።
8ኢየሱስ፣ "እንዳትስቱ ተጠንቀቁ። ምክንያቱም ብዙዎች 'እኔ ኢየሱስ ነኝ፣ ደግሞም 'ጊዜው አሁን ነው' እያሉ በስሜ ይመጣሉ። አትከተሏቸው።
9ስለ ጦርነቶችና ሁከቶች ስትሰሙ አትሸበሩ፣ እነዚህ ነገሮች አስቀድመው መፈጸም ይኖርባቸዋል፣ ነገር ግን መጨረሻው ወዲያው አይሆንም" ብሎ መለሰ።
10ከዚያም እንዲህ አላቸው፣ "ሕዝብ በሕዝብ ላይ ይነሣል፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣል።
11ታላቅ የመሬት መንቀጥቀጥ ይሆናል፣ ደግሞም በተለያዩ ቦታዎች ራብና ቸነፈር ይከሠታል። አስፈሪ ሁነቶችና ታላላቅ ምልክቶች ከሰማይ ይገለጣሉ።
12ነገር ግን ከእነዚህ ሁሉ ነገሮች አስቀድሞ እናንተን ይይዟችኋል፣ ያሳድዷችኋል፣ ለምኩራቦችና ለወህኒ ቤቶች አሳልፈው በመስጠት ስለ ስሜ በገዦችና በነገሥታት ፊት ያቆሟችኋል።
13ይህም ለእናንተ ለመመስከር ዕድልን ይሰጣችኋል።
14ስለዚህ፣ አስቀድማችሁ ምን መከላከያ እናቀርባለን በማለት አትናወጡ፣
15ምክንያቱም በዚያን ጊዜ ጠላቶቻችሁ ሊቋቋሙትና ሊቃወሙት የማይችሉትን ቃልና ጥበብ እሰጣችኋለሁ።
16ነገር ግን በወላጆች፣ በወንደሞች፣ በዘመዶችና በጓደኞች ተላልፋችሁ ትሰጣላችሁ፣ ከእናንተም አንዳንዶቹን ይገድላሉ።
17በስሜ ምክንያት በሰው ሁሉ ትጠላላችሁ።
18ነገር ግን ከራሳችሁ ጠጒር አንዲቱ እንኳ አትጠፋም።
19በትዕግሥታችሁም ነፍሳችሁን ታተርፋላችሁ።
20ኢየሩሳሌም በሠራዊት ተከብባ ስታዩ ጥፋቷ መቃረቡን እወቁ።
21በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፣ በከተማይቱ መካከል ያሉትም ለቀው ይሂዱ፣ በገጠር ያሉት ደግሞ ወደ ከተማይቱ አይግቡ።
22የተጻፈው እንዲፈጸም እነዚህ ጊዜያት የበቀል ጊዜያት ናቸውና።
23በእነዚያ ቀኖች ለእርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው! በምድሪቱ ላይ ታላቅ መከራ፣ በዚህ ሕዝብም ላይ ቊጣ ይወርዳል።
24በሰይፍም ስለት ይወድቃሉ፤ ወደ ተለያዩ ሕዝቦች ሁሉ ምርኮኞች ተደርገው ይወሰዳሉ፤ የአሕዛብ ዘመን እስኪፈጸም ድረስ፣ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።
25በፀሐይ፣ በጨረቃና በከዋክብት ምልክቶች ይታያሉ። በምድር ላይ ያሉ ሕዝቦች ከባሕርና ከማዕበል ድምፅ የተነሣ ተስፋ በመቊረጥ ይጨነቃሉ።
26ከፍርሃትና በዓለም ላይ ሊከሰቱ ያሉትን ነገሮች ከመሥጋት የተነሣ የሚዝሉ ሰዎችም ይኖራሉ። ምክንያቱም የሰማያት ኅይላት ይናወጣሉና።
27ከዚያም የሰው ልጅ በኅይልና በታላቅ ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል።
28ነገር ግን እነዚህ ነገሮች መፈጸም ሲጀምሩ፣ መዳናችሁ ስለ ቀረበ ንቁ፣ ቀና ብላችሁ ተመልከቱ።
29ኢየሱስ አንድ ምሳሌ ነገራቸው፤ “የበለስ ዛፍና ሌሎች ዛፎችን ተመልከቱ።
30ቀንበጥ ሲያወጡ፣ በጋ እንደተቃረበ ታውቃላችሁ።
31ልክ እንደዚሁም እነዚህ ነገሮች መፈጸማቸውን ስታዩ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ።
32እውነቱን እነግራችኋለሁ፣ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ከመፈጸማቸው በፊት ይህ ትውልድ አያልፍም።
33ሰማይና ምድር ያልፋሉ፣ ቃሌ ግን አያልፍም።
34ልቅ በሆነ አኗኗር፣ በስካርና በጭንቀት ልባችሁ እንዳይከብድ ተጠንቀቁ። ምክንያቱም ያ ቀን እንደ ወጥመድ በድንገት ይመጣባችኋል።
35በምድር በሚኖሩት ሁሉ ላይም ይመጣባቸዋል።
36ነገር ግን ከሚከሠቱት ከአነዚህ ነገሮች ሁሉ እንድታመልጡና በሰው ልጅም ፊት ለመቆም እንድትበረቱ ሁልጊዜ ነቅታችሁ ጸልዩ።
37ስለዚህ ኢየሱስ በየቀኑ በቤተ መቅደስ ያስተምር፣ ሌሊቱን ደግሞ ወደ ደብረ ዘይት ተራራ እየወጣ ያሳልፍ ነበር።
38በቤተ መቅደስም ሲያስተምር ሰዎች ሁሉ ሊሰሙት በማለዳ ይመጡ ነበር።
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።