1በስምንተኛው ቀን ሙሴ አሮንንና ልጆቹን እንዲሁም የእስራኤልን ሽማግሌዎች ጠራ፡፡
2አሮንን እንዲህ አለው፣ “ለኃጢአት መስዋዕት ከመንጋው እምቦሳ እና ነውር የሌለበትን አውራ በግ ወስደህ በያህዌ ፊት ሰዋቸው፡፡
3እስራኤል ሰዎች እንዲህ ባላቸው፣ ‘ለኃጢአት መስዋዕት ወንድ ፍየል ውሰድ እንደዚሁም ነውር የሌለባቸው የአንድ አመት እምቦሳና ጠቦት ለሚቃጠል መስዋዓት ውሰድ፤
4እንዲሁም በያህዌ ፊት የሰላም መስዋት ለመስዋዕት አንድ በሬና አንድ አውራ በግ ውሰድ፣ በዘይት የተለወሰ የእህል ቁርባንም አቅርብ፣ ምክንያቱም ዛሬ ያህዌ ይገለጥላችኋል፡፡”
5ስለዚህም ሙሴ ያዘዘውን ሁሉ ወደ መገናኛው ድንኳን አመጡ፣ የእስራኤል ጉባኤም ሁሉ ቀርበው በያህዌ ፊት ቆሙ፡፡
6ከዚያም ሙሴ እንዲህ አለ፣ “ያህዌ እንድታደርጉት ያዘዘው ይህንን ነው፣ስለዚህም ክብሩ ይገለጥላችኋል፡፡”
7ሙሴ አሮንን እንዲህ አለው፣ “ወደ መዊያው ቀርበህ የኃጢአት መስዋዕትህንና የሚቃጠል መስዋዕትህን አቅርብ፣ ደግሞም ያህዌ እንዳዘዘው ለራስህና ለህዝቡ አስተስርይ፣ ለህዝቡ ማስተስረያ ለማቅረብ መስዋዕቱን ሰዋ፡፡” 8ስለዚህም አሮን ወደ መሰዊያው ቀርቦ ለራሱ የሆነውን መስዋዕት ለኃጢአት መስዋዕት እምቦሳውን አረደ፡፡
8ስለዚህም አሮን ወደ መሰዊያው ቀርቦ ለራሱ የሆነውን መስዋዕት ለኃጢአት መስዋዕት እምቦሳውን አረደ፡፡
9የአሮን ልጆቸ ደሙን አቀረቡለት፣ እርሱም ጣቱን ደሙ ውስጥ እየነከረ በመሰዊያው ቀንዶች ውስጥ ጨመረ፤ ከዚያም በመሰዊያው ስር ደሙን አፈሰሰ፡፡
10ሆኖም ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው ስቡን፣ ኩላሊቶቹን እና በመሰዊያው ላይ የጉበቱን ሽፋን የኃጢአት መስዋዕት አድርጎ አቃጠላቸው፡፡
11ስጋውንና ቆዳውን ከሰፈር ውጭ አቃጠለው፡፡
12አሮን የሚቃጠለውን መስዋዕት አረደ፣ ልጆቹ በመሰዊያው ዙሪያ የሚረጨውን ደም ሰጡት፡፡
13ከዚያ የሚቃጠለውን መስዋዕት ከከብቱ ራስ ጋር እየቆራረጡ ሰጡት፣ እርሱም በመሰዊያው ላይ አቃጠለው፡፡
14የሆድ ዕቃዎቹንና እግሮቹን አጥቦ በመሰዊያው ላይ በሚቃጠል መስዋዕቱ ላይ አቃጠላቸው፡፡
15አሮን አንድ ፍየል የህዝቡን መስዋዕት አቀረበ፣ ከዚያ ለኃጢአታቸው መስዋዕት አድርጎ አረደው፤ በመጀመሪያው ፍየል ላይ እንዳደረገው ሁሉ ለኃጢአት መስዋዕትነት ሰዋው፡፡
16ያህዌ እንዳዘዘው የሚቃጠል መስዋዕቱን አቅርቦ ሰዋው፡፡
17የእህል ቁርባኑን፣ ከእህል ቁርባኑ እፍኝ ሙሉ ወስዶ ከማለዳው የሚቃጠል መስዋዕት ጋር በመሰዊያው ላይ አቃጠለው፡
18እንዲሁም ለህዝቡ የሰላም መስዋዕት የሆነውን መስዋዕት በሬውንና አውራ በጉን አረደ፡፡ የአሮን ልጆች በመሰዊያው ዙሪያ የሚረጨውን ደሙን ሰጡት፡፡
19ሆኖም፣ የበሬውንና የአውራ በጉን ስብ፣ ላቱን፣ ሆድ ዕቃውን ክፍሎች የሸፈነውን ስብ፣ ኩላሊቶቹን፣ የጉበቱን ሽፋን
20እነዚህን በፍርምባው ላይ አደረጉ፣ ከዚያም አሮን ሙሴ ባዘዘው መሰረት ስቡን በመሰዊያው ላይ አቃጠለው፡፡
21አሮን ፍርምባውንና የቀኝ ወርቹን መስዋዕት አድርጎ በያህዌ ፊት ይወዝስዘውና እነዚህን ለያህዌ ያቅርብ፡፡
22ከዚያ አሮን አጆቹን ወደ ህዝቡ አንስቶ ይባርካቸው፤ ቀጥሎ የኃጢአት መስዋዕቱን፣ የሚቃጠል መስዋዕቱንና የሰላም መስዋዕቱን አቅርቦ ይወርዳል፡፡
23ሙሴና አሮን ወደ መገናኛው ድንኳን ይሂዱ፣ ከዚያ ተመልሰው ይውጡና ህዝቡን ይባርኩ፣ እናም የያህዌ ክብር ለህዝቡ ሁሉ ይገለጣል፡፡
24ከያህዌ ዘንድ እሳት ወጥቶ የሚቃጠል መስዋዕቱንና በመሰዊያው ላይ ያለውን ስብ ሁሉ በላ፡፡ ህዝቡ ሁሉ ይህንን ባዩ ጊዜ ጮኸው በፊታቸው ተደፉ፡፡