1ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
2“አሮንንና ልጆቹን፣ የክህነት ልብሶቹን፣ የቅባት ዘይቱን፣የኃጢአት መስዋዕቱን ወይፈኖች፣ ሁለቱን ጠቦቶች፣ እርሾ የሌለበትን ህብስት መሶብ ከእርሱ ጋር ውሰድ፡፡
3በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ ሁሉንም ጉባኤ ሰብስብ፡፡”
4ስለዚህም ሙሴ ያህዌ እንዳዘዘው አደረገ፣ ጉባኤውም በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ ተሰበሰበ፡፡
5ከዚያም ሙሴ ለጉባኤው እንዲህ አለ፣ “ያህዌ እንዲደረግ ያዘዘው ይህ ነው፡፡”
6ሙሴ አሮንንና ልጆቹን አቀረበና በውሃ አጠባቸው፡፡
7አሮንን እጀ ጠባብ አለበሰውና በወገቡ ዙሪያ መቀነት አስታጠቀው፣ ቀሚ አጠለቀለትና ኤፉድ ደረበለት፣ ከዚያም ኤፉዱን በጥበብ በተጠለፈ መቀነት አስታጠቀው፡፡
8በቀሚሱ ላይ ደረት ኪስ አደረገለት፣ በደረት ኪሱ ውስጥ ኡሪምና ቱሚም አደረገበት፡፡
9ሙሴ ያህዌ እንዳዘዘው በራሱ ላይ ጥምጥሙን ጠመጠመለት፣ በጥምጥሙ ላይ ከፊት በኩል ወርቃማ ቅብና ቅዱስ አክሊል አደረገለት፡፡
10ሙሴ የቅባቱን ዘይት ወሰደ፣ ማደሪያ ድንኳኑንና በውስጡ ያለውን ሁሉ ቀባው፤ እናም ለያህዌ ቀደሳቸው፡፡
11በመሰዊያው ላይ ዘይቱን ሰባት ጊዜ ረጨው፣ እናም መሰዊያውንና መገልገያዎቹን ሁሉ ቀባቸው፣ እንዲሁም የመታጠቢያ ሳህኑንና ማስቀመጫውን፣ ለያህዌ ቀደሳቸው፡፡
12አሮንን ያህዌ ለመለየት ከቅባቱ ዘይት ጥቂቱን በአሮን ራስ ላይ አፈሰሰው፡፡
13ሙሴ ያህዌ እንዳዘዘው የአሮንን ወንድ ልጆች አቅርቦ እጀጠባብ አለበሳቸው፣ በወገባቸው ዙሪያ መታጠቂያ አሰረላቸው፣ በራሳቸው ላይ በፍታ ጨርቅ ጠቀለለላቸው፡፡
14ሙሴ ለኃጢአት መስዋዕት በሬ አመጣ፣ አሮንና ልጆቹ ለኃጢአት መስዋዕት ባመጡት በሬ ላይ እጆቻቸውን ጫኑ፡፡
15በሬውን አርዶ ደሙን በመሰዊያው ቀንዶች ውስጥ በጣቱ ጨመረ፣ በመሰዊያው ስር ደሙን አፈሰሰ፣ ለማስተስረይ ለእግዚአብሔር ለየው፡፡
16በመስዋዕቱ ሆድ ዕቃ ውስጥ ያለውን ስብ ሁሉ አወጣ፣ በጉበቱ መሸፈኛና በሁለቱ ኩላሊቶች ላይ ያለውን ስብ ወስዶ በመሰዊያው ላይ ሁሉንም አቃጠለው፤
17ነገር ግን በሬውን፣ ቆዳውን፣ ስጋውን እና ፈርሱን ያህዌ እንዳዘዘው ከሰፈር አውጥቶ አቃጠለው፡፡
18ሙሴ ለሚቃጠል መስዋዕት ጠቦቱን አቀረበ፣ አሮንና ልጆቹ በጠቦቱ ራስ ላይ እጃቸውን ጫኑ፡፡
19ሙሴም ጠቦቱን አርዶ በመሰዊያው ዙሪያ ደሙን ረጨ፡፡
20ጠቦቱን ቆራርጦ ራሱንና ቁርጥራጩን እንዲሁም ስቡን አቃጠለ፡፡
21የሆድ ዕቃውን ክፍሎችና እግሮቹን በውሃ አጠበ፣ ከዚያም ጠቦቱን በሙሉ በመሰዊያው ላይ አቃጠለ፡፡ ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው ይህ የሚቃጠል መስዋዕት ነው፤ ደግሞም ለያህዌ በእሳት የተዘጋጀ ጣፋጭ መዓዛ ነው፡፡
22ከዚያም ሙሴ ሌላውን ጠቦት ያቀርባል፣ ይህም የክህነት ሹመት መስዋዕት ነው፣ እናም አሮንና ልጆቹ በጠቦቱ ራስ ላይ እጃቸውን ይጭናሉ፡፡
23አሮን ጠቦቱን ያርዳል፣ ሙሴም ከደሙ ጥቂት ወስዶ በአሮን ቀኝ ጆሮ ጫፍ ላይ፣ በቀኝ እጁ አውራ ጣት እና በቀኝ እግሩ አውራ ጣት ላይ ያደርጋል፡፡
24የአሮንን ልጆች አቅርቦ፣ በቀኝ ጆሯቸው ጫፍ ላይ፣ በቀኝ እጃቸው አውራ ጣት ላይ እና በቀኛ እግራቸው አውራ ጣት ላይ ከደሙ ጥቂት ወስዶ ያደርጋል፡፡ ከዚያ ሙሴ የበጉን ደም በመሰዊያው ጎኖች ሁሉ ይረጫል፡፡
25ስቡን፣ ላቱን፣ በሆድ ዕቃ ክፍሎች ውስጥ ሁሉ የሚገኘውን ስብ፣ የጉበቱን መሸፈኛ፣ ሁለቱን ኩላሊቶች እና በላያቸው የሚገነውን ስብ እንዲሁም ቀኝ ወርቹን ወሰደ፡፡
26በያህዌ ፊት ከነበረው መሶብ እርሾ የሌለበት አንድ ህብስት ይወስዳል፣ደግሞም በዘይት ተለውሶ ከተሰራው ዳቦ አንዱን እና አንድ ስስ ቂጣ ይውሰድና በስቡና በቀኝ ወርች ላይ ያኖረዋል፡፡
27ሁሉንም በአሮን እጆችና በአሮን ወንድ ልጆች እጆች ላይ ያስቀምጠዋል፣ ይህንንም ለሚወዘወዝ መስዋዕት በያህዌ ት ያቀርባሉ፡፡
28ከዚያም ሙሴ ከእጃቸው ይወስድና የሚቃጠል መስዋዕት አድርጎ ያቀርበው፡፡ እነዚህ የክህነት ሹመት መስዋዕት ናቸው፤ ጣፋጭ መዓዛ ሆነው ይቀርባሉ፡፡ ይህ በእሳት ለያህዌ የሚቀርብ መስዋዕት ነው፡፡
29ሙሴ ፍርምባውን ወስዶ ለያህዌ መስዋዕት አድርጎ ይወዝውዘው፡፡ ያህዌ እንዳዘዘው ይህ ከጠቦቱ የክህነት ሹመት የሙሴ ድርሻ ነው፡፡
30ሙሴ በመሰዊያው ላይ ካለው ከቅባት ዘይቱና ከደሙ ጥቂት ወስዶ እነዚህን በአሮን ላይ፣ በልብሶ ላይ፣ በወንድ ልጆቹ ላይ እና ከእርሱ ጋር በልጆቹ ልብሶች ላይ ይረጫል፡፡ በዚህ መንገድ አሮንና የክህነት ልብሱን እንዲሁም ልጆቹንና ልብሳቸውን ለያህዌ ይቀድሳል፡፡
31ደግሞም ሙሴ ለአሮንና ለልጆቹ እንዲህ አለ፣ “በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ስጋውን ቀቅሉት፣ በዚያም ስፍራ በሹመት መስጫው መሶብ ውስጥ ያለውን ህብስትም ‘አሮንና ልጆቹ ይብሉት’ ብዬ እንዳዘዝኩት ብሉት፡፡
32ከስጋውና ከህብስቱ የተረፈውን በሙሉ አቃጥሉት፡፡
33የሹመት ስርዓቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ለሰባት ቀናት ከመገናኛው ከመገናኛው ድንኳን መግቢያ አትለፉ፡፡ ያህዌ በሰባት ቀናት ውስጥ ይሾማችኋል፡፡
34በዚህ ቀን የሚሆነው እናንተን ለማስተረይ ያህዌ እንዲደረግ ያዘዘው ነው፡፡
35ለሰባት ቀናት ቀንም ሆነ ሌሊት በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ትቆያላችሁ፣ ደግሞም የያህዌን ትዕዛዝ ትጠብቃላችሁ፣ ይህን ካደረጋችሁ አትሞቱም፣ ምክንያቱም የታዘዝኩት ይህንን ነው፡፡”
36ስለዚህም አሮንና ልጆቹ ያህዌ በሙሴ በኩል እንዲያደርጉት ያዘዛቸውን ሁሉንም ነገር አደረጉ፡፡