1የበደል መስዋዕት ህግ ይህ ነው፡፡ እጅግ ቅዱስ ነው፡፡
2የበደል መስዋዕቱን በሚታረድበት ስፍራ የበደሉንም መስዋዕ ይረዱት፣ ደሙን በመሰዊያው እያንዳንዱ ጎን ይርጩት፡፡
3በመስዋዕቱ ከብት ውስጥ ያለው ስብ ሁሉ ይቃጠል፤ ላቱ፣የሆድ ዕቃውን ክፍሎች የሸፈነው ስብ በመሁሉ፣
4በጎድኑ አጠገብ ያለው ስብ፣ ሁለቱ ኩላሊቶችና በላያቸው ያለው ስብ፣ ጉበቱን የሸፈነው ስብ፣ ከኩላሊቶቹ ጋር - እነዚህ ሁሉ ይቅረቡ፡፡
5ካህኑ እነዚህን ክፍሎች በእሳት የተዘጋጀ መስዋዕት አድርጎ በመሰዊያው ላይ ለያህዌ ያቃጥል፡፡ ይህ የበደል መስዋዕት ነው፡፡
6እያንዳንዱ ካህን ከዚህ መስዋዕት መብላት ይችላል፡፡ በተቀደሰ ስፍራ ይበላ ምክንያቱም እጅግ ቅዱስ ነው፡፡
7የኃጢአት መስዋዕት ልክ እንደ በደል መስዋዕት ነው፡፡ የሁለቱም ህግ ተመሳሳይ ነው፡፡ እነዚህ ህጎች የማስተስረይ አገልግሎት ለሚሰጡ ካህናት ያገለግላሉ፡፡
8የየትኛውንም ሰው የሚቃጠል መስዋዕት የሚያቀርብ ካህን የመስዋዕቱን ቆዳ መውሰድ ይችላል፡፡
9በምድጃ የሚዘጋጅ እያንዳንዱ የእህል ቁርባን፣ እና በመጥበሻ የሚዘጋጅ እንዲህ ያለው እያንዳንዱ መስዋዕት ወይም በመጋገሪያ መጥበሻ ላይ የሚዘጋጅን መስዋዕት፣ መስዋዕቱን የሚያሳርገው ካህን ይወስደዋል፡፡
10ደረቅም ሆነ በዘይት የተለወሰ እያንዳንዱ የእህል ቁርባን ለአሮን ትውልዶች እኩል የእነርሱ ነው፡፡
11ይህ ሰዎች ለያህዌ የሚያቀርቡት የሰላም መስዋዕት ህግ ነው፡፡
12ማንም ሰው ምስጋና ለማቅረብ ይህን ቢያደርግ፣ እርሾ የሌለበት መስዋዕት አድርጎ ያቅርበው፣ ነገር ግን ቂጣውን በዘይት ይለውሰው፣ ቂጣው በመልካም ዱቄት የተዘጋጀ በዘይት የተለወሰ ይሁን፡፡
13ደግሞም ምስጋና ለማቅረብ፣ ከሰላም መስዋዕቱ ጋር በእርሾ የተዘጋጀ ህብስት ያቅርብ፡፡
14ከእነዚህ መስዋዕቶች ከእያንዳንዳቸው አንድ አይነት መስዋዕት ለያህዌ ያቅርብ፡፡ ይህ የሰላም መስዋዕቱን ደም በመሰዊያው ላይ ለሚረጩት ካህናት ይሰጥ፡፤
15ምስጋና ለማቅረብ የሰላም መስዋዕት የሚያቀርበው ሰው መስዋዕቱ በሚቀርብበት ዕለት የመስዋዕቱን ስጋ ይብላ፡፡ ከስጋው እስከ ማግስቱ አይደር፡፡
16ነገር ግን መስዋዕቱ የሚያቀርበው ለስዕለት ከሆነ፣ ወይም በበጎ ፈቃድ የሚቀርብ መስዋዕት ከሆነ ስጋው መስዋዕቱን ባቀረበበት ዕለት ባያልቅ በማግስቱ ሊበላ ይችላል፡፡
17ሆኖም፣ ከመስዋዕቱ የተረው ስጋ በሶስተኛው ቀን ይቃጠል፡፡
18አንድ ሰው ካቀረበው የበጎ ፈቃድ መስዋዕት አንዳች ስጋ በሶስተኛው ቀን ቢበላ ይህ ተቀባይነት የለውም፤ መስዋዕቱን ላቀረበውም ዋጋ የለውም፡፡ ደስ የማያሰኝ ነገር ይሆናል፣ ስጋውን ለሚበላውም ሰው የበደል ዕዳ ይሆንበታል፡፡
19ንጹህ ያልሆነ ነገር የነካ ከዚህ ስጋ አይበላም፡፡ ስጋው መቃጠል ይኖርበታል፡፡ የተረውን ስጋ፣ ማንኛውም ንጹህ የሆነ ሰው ሊበላው ይችላል፡፡
20ሆኖም፣ ለያህዌ የሚቀርበውን የሰላም መስዋዕት ስጋ የበላ ንጹህ ያልሆነ ሰው ከህዝቡ ተለይቶ ይወገድ፡፡
21ማንኛውም ሰው ንጹህ ያልሆነ ነገር ቢነካ - ንጹህ ያልሆነን ሰው፣ ወይም ንጹህ ያልሆነን አውሬ፣ ወይም ንጹህ ያልሆነ እና ደስ የማያሰኝ ነገር ቢነካ፣ እና ከዚያም ለያህዌ ከቀረበው የሰላም መስዋዕት ስጋ ቢበላ ያሰው ከህዝቡ ተለይቶ ይወገድ፡፡
22ቀጥሎም ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
23“የእስራኤልን ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‘የበሬ ወይም የበግ ወይም የፍየል ስብ አትብሉ፡፡
24ሳይታረድ ሞቶ የተገኘ እንስሳ ስብ፣ ወይም በዱር አውሬ የተገደለ እንስሳ ስብ ለሌላ ተግባር ሊውል ይችላል፣ ነገር ግን የዚያን እንስሳ ስብ በፍጹም አትብሉ፡፡
25ሰዎች በእሳት ለያህዌ መስዋዕት አድርገው ሊያቀርቡ የሚችሉትን እንስሳ ስብ የሚላ ማንኛውም ሰው፣ ከህዝቡ ተለይቶ ይወገድ፡፡
26በቤቶቻችሁ የወፍም ሆነ የእንስሳ ማናቸውም ዐይነት ደም አትብሉ፡፡
27ማናቸውንም ደም የበላ ማንም ሰው፣ ከህዝቡ ተለይቶ ይጥፋ፡፡’”
28ደግሞም ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
29“የእስራኤልን ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‘ለያህዌ የሰላም መስዋዕት የሚያቀርብ ከመስዋዕቱ ላይ ወስዶ ለያህዌ ያቅርብ፡፡
30ለያህዌ በእሳት የሚዘጋጀውን መስዋዕት፣ በእርሱ በራሱ እጅ ያቅረበው፡፡ ስቡን ከፍርምባው ጋር ያቅርበው፣ ስለዚህ ፍርምባውን በያህዌ ፊት ለመስዋዕት ያቅርበው፡፡
31ካህኑ ስቡን በመሰዊያ ላይ ያቃጥለው፣ ነገር ግን ፍርምባው የአሮንና የትውልዱ ነው፡፡
32የቀኙን ወርች ከሳለም መስዋዕታችሁ የቀረበ ስጦታ አድርጋችሁ ለካህኑ ስጡት፡፡
33የሰላም መስዋዕቱንና ስቡን ደም የሚያቀርበው ከአሮን ትውልድ ውስጥ የሆነው ካህን ከመስዋዕቱ ውስጥ የቀኝ ወርቹ የእርሱ ድርሻ ነው፡፡
34ለእኔ የተወዘወዘውንና የቀረበውን የፍርምባውንና የወርቹን መስዋዕት እኔ ስለ ወሰድኩ፣ እነዚህን ሊቀካህን ለሆነው ለአሮንና ለዘሩ ሰጥቻለሁ፣ ይህ ሁልጊዜም በእስራኤል ህዝብ ከሚዘጋጀው የሰላም መስዋዕት ድርሻቸው ይሆናል፡፡
35ሙሴ በካህናት አገልግሎት ያህዌን እንዲያገለግሉ እነርሱን ባቀረበ ቀን ይህ ለአሮንና ለዘሮቹ በእሳት ለያህዌ ከሚቀርበው መስዋዕት ድርሻቸው ነው፡፡
36እርሱ ካህናትን በቀባ ቀን ያህዌ ከእስራኤል ህዝብ ድርሻቸው ሆኖ ለእነርሱ እንዲሰጥ ያዘዘው ይህ ነው፡፡ ይህ ሁልጊዜም በትውልዶች ሁሉ ድርሻቸው ይሆናል፡፡
37ይህ የሚቃጠል መስዋዕት፣ የእህል ቁርባን፣ የኃጢአት መስዋዕት፣ በደል መስዋዕት፣ የክህነት ሹመት መስዋዕት እና የሰላም መስዋዕት ስርዓት ነው፤
38ይህ ያህዌ ለሙሴ በሲና ተራራ ላይ የእስራኤል ህዝብ መስዋዕታቸውን በሲና ምድረበዳ የሚያቀርቡበትን ህግጋት ለሙሴ በሰጠበት ቀን የተሰጠ ስርዓት ነው፡፡