1ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣
2“ ማንም ሰው ኃጢአት ቢሰራና የያህዌን ትዕዛዝ ቢተላለፍ፣ ታማኝነቱን አፍርሶ ሃሰተኛ ቢሆን፣ ወይም ጎረቤቱ በአደራ የሰጠውን ቢክድ፣ ወይም ቢያታልል ወይም ቢሰርቀው፣ወይም ጎረቤቱን ቢበድል
3ወይም ከጎረቤቱ የጠፋ ነገር አግኝቶ ቢዋሽ፣ እናም በሃሰት ቢምል፣ ወይም እነዚህን በመሰሉ ሰዎች በሚበድሉባቸው ጉዳዮች ኃጢአት ቢሰራና፣
4በደለኛ ሆኖ ቢገኝ፣ በስርቆት የወሰደውን ይመልስ ወይም የበደለውን ይካስ፣ ወይም ታማኝነቱን አጉድሎ የወሰደውን ጠፍቶ ያገኘውን ነገር ይመልስ፡፡
5ወይም በማንኛውም ጉዳይ ላይ ቢዋሽ፣ ሙሉ ለሙሉ ይመልስ፤ እንዲሁም ጥፋተኛ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ለባለንብረቱ አንድ አምስተኛውን ጨምሮ ይክፈል፡፡
6ከዚያም የበደል መስዋዕቱን ዋጋው ተመጣጣኝ የሆነ ነውር የሌለበት ጠቦት ከመንጋው የኃጢአት መስዋእት ለያህዌ ወደ ካህኑ ያምጣ፡፡
7ካህኑ የኃጢአት ማስተስረያ በያህዌ ፊት ያቀርባል፣ እናም በዳዩ ለሰራው በደል ሁሉ ይቅር ይባላል፡፡”
8ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
9“አሮንን እና ልጆቹን እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፣ ‘የሚቃጠል መስዋዕት ህግ ይህ ነው፡ የሚቃጠለው መስዋዕት በመሰዊያው ምድጃ ላይ ሌሊቱን ሁሉ እስከ ማለዳ ይገኝ፣ ደግሞም የመሰዊያው እሳት ሳያቋርጥ ይንደድ፡፡
10ካህኑ የበፍታ ልብሱን ይልበስ፣ እንዲሁም የበፍታ ቀሚን ይልበስ፡፡ እሳቱ በመሰዊያው ላይ ያለውን የሚቃጠለውን መስዋዕት ከበላ በኋላ አመዱን ይፈስ፣ ከዚያም አመዱን ከመሰዊያው ጎን ይድፋው፡፡
11አመዱን ከሰፈር ውጭ ንጹህ ወደ ሆነ ስፍራ ለመውሰድ የለበሰውን አውልቆ ሌላ ልብስ ይልበስ፡፡
12በመሰዊው ላይ ያለው እሳት ሳያቋርጥ ይንደድ፡፡ መጥፋት የለበትም፣ እናም ካህኑ በየማለዳው እንጨት ይጨምርበት፡፡ እንደ አስፈላጊነቱ በላዩ የሚቃጠል መስዋዕት ያድርግበታል፣ ደግሞም የሰላም መስዋዕት ስብ በላዩ ያቃጥልበታል፡፡
13እሳቱ ሳያቋርጥ በመሰዊያው ላይ ይንደድ፤መጥፋት የለበትም፡፡
14የእህል ቁርባን ህግ ይህ ነው፡፡ የአሮን ልጆች ከያህዌ ፊት በመሰዊያው ላይ ያቀርቡታል፡፡
15ካህኑ የእህል ቁርባን አድርጎ እፍኝ መልካም የእህል ዱቄትና ዘይት እንዲሁም ዕጣን ለመስዋዕት ይውሰድና የያህዌን በጎነት ምስጋና ለማቅረብ በመሰዊያው ላይ ያቃጥለው፡፡
16አሮንና ልጆቹ ከመስዋዕቱ የቀረውን ይመገቡት፡፡ ይህም እርሾ ሳይገባበት በተቀደሰው ስፍራ ይብላ፡፡ በመገናኛው ድንኳን ቅጽረ ግቢ ይመገቡት፡፡
17በእርሾ መጋገር የለበትም፡፡ እኔ በእሳት የተዘጋጀ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ፡፡ የኃጢአት መስዋዕትና የበደል መስዋዕት እጅግ የተቀደሰ ነው፡፡
18ለሚመጣው ተውልድ ሁሉ ለዘመናት ሁሉ ወንድ የሆነ የአሮን ትውልድ ድርሻው አድርጎ ከያህዌ ከሚቀርበው የእሳት ቁርባን ሊበላው ይችላል፡፡ ማናቸውም እርሱን የሚነካ ቅዱስ ይሆናል፡፡”
19ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣
20“ይህ አሮንና ልጆቹ የሚያቀርቡት መስዋዕት ነው፣ እያንዳንዳቸው የአሮን ልጆች በሚቀቡበት ቀን ለያህዌ የሚያቀርቡት መስዋዕት ነው፡፡ እንደ ተለመደው የእህል ቁርባን የኢፍ አንድ አስረኛ ክፍል መልካም ዱቄት፤ በጠዋት ግማሹን የተቀረውን ግማሽ ደግሞ ምሽት ያቀርቡታል፡፡
21በመጥበሻ ላይ በዘይት ይጋገራል፡፡ በእርጥቡ ሳለ፣ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ እንዲሆን ታቀርበዋለህ፡፡ የእህል ቁርባኑን ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ እንዲሆን ቆራርሰህ ታቀርበዋለህ፡፡
22ከሊቀ ካህኑ ልጆች መሃል ተተኪ ካህን የሚሆነው ወንድ ልጅ መስዋዕቱን ያቀርባል፡፡ ለዘለዓለም እንደታዘዘው፣ መስዋዕቱ በሙሉ ለያህዌ ይቃጠላል፡፡
23ካህኑ የሚያቀርበው እያንዳንዱ የእህል ቁርባን ሙሉ ለሙሉ ይቃጠላል፤አይበላም፡፡”
24ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
25“አሮንና ወንዶች ልጆቹን እንዲህ በላቸው፣ ‘የኃጢአት መስዋዕት ህግ ይህ ነው፡ የኃጢአት መስዋዕት የሚታረደው የሚቃጠል መስዋዕት በሚታረድበት ስፍራ ያህዌ ፊት ነው፡፡ እጅግ ቅዱስ ነው፡፡
26የኃጢአት መስዋዕት የሚያቀርበው ካህን ይመገበዋል፡፡ በመገናኛው ድንኳን ቅጽረግቢ በተቀደሰው ስፍራ ይበላ፡፡
27የመስዋዕቱን ስጋ የሚነካ ሁሉ ይቀደሳል፣ደሙ በየትኛውም ልብስ ላይ ቢረጭ ደሙ የነካውን የጨርቁን ስፍራ በተቀደሰ ቦታ እጠበው፡፡
28የተቀቀለበት የሸክላ ማሰሮ ግን ይሰበር፡፡
29ከካህናቱ መሀል ማናቸውም ወንድ ከዚህ መብላት ይችላል ምክንያቱም እጅግ ቅዱስ ነው፡፡
30በተቀደሰው ስፍራ ወደ መገናኛው ድንኳን ለማስተስረይ ደሙ ከቀረበው የኃጢአት መስዋዕት ምንም አይበላ፡፡