መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘሌዋውያን 5

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ማንም ሰው ያየውንም ሆነ የሰማውን አንዳች ነገር መምስከር ሲገባው ባለመመስከር ኃጢአት ቢሰራ፣ ይጠየቅበታል፡፡
2ወይም ማንም ሰው እግዚአብሔር ንጹህ አይደለም ያለውን ማናቸውንም ነገር ቢነካ፣ ይህ ንጹህ ያልሆነ ነገር የዱር እንስሳ ስጋ ወይም የሞተ የቤት እንስሳ ቢሆን፣ ወይም ማናቸውንም ያልነጻ ሰው ቢነካ፣ ደግሞም ይህን ማድረጉን ባያውቅ፣ ስለ ነገሩ ባወቀ ጊዜ ኃጢአጠኛ ይሆናል፡፡
3ቁጥር 3 (?)
4ወይም ማንም ሰው በችኮላ ክፉ ወይም በጎ ለማድረግ በከንፈሮቹ ቢምል፣በችኮላ የማለው መሀላ ምንም አይነት ይሁን፣ ስለ ነገሩ ባያውቅ እንኳን፣ ነገሩን ባወቀ ጊዜ ከእነዚህ በማናቸውም ነገር ኃጢአተኛ ይሆናል፡፡
5አንድ ሰው ከእነዚህ ነገሮች በማንኛውም በደለኛ ሆኖ ሲገኝ፣የሰራውን ማንኛውንም ኃጢአት መናዘዝ አለበት፡፡
6ከዚያም ለሰራው ኃጢአት የበደል መስዋዕቱን ወደ ያህዌ ማምጣት አለበት፣ ለኃጢአት መስዋዕት ሴት ጠቦት በግ ወይም ሴት ፍየል ያቀርባል፤ ካህኑም ስለ ሰራው ኃጢአት ያስተሰርይለታል፡፡
7ጠቦት መግዛት ካልቻለ፣ ለኃጢአቱ የበደል መስዋዕት ለያህዌ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት እርግቦች ማምጣት ይችላል፤ አንዱ ለኃጢአት መስዋዕት እና ሌላኛው ለሚቃጠል መስዋዕት ያመጣል፡፡
8እነዚህን ወደ ካህኑ ያመጣል፣ እርሱም በመጀመሪያ አንዱን ለኃጢአት መስዋዕት ያቀርባል - እርሱም የመስዋዕቱን ራስ ከአንገቱ ይቆለምማል ነገር ግን ሙሉ ለሙሉ አይለያየውም፡፡
9ከዚያ ከኃጢአት መስዋዕቱ ጥቂት ደም ወስዶ በመሰዊያው ጎን ይረጫል፣ ከዚያ የቀረውን ደም በመሰዊያው ስር ደሙን ያንጠፈጥፈዋል፡፡ ይህ የኃጢአት መስዋዕት ነው፡፡
10ከዚያ ሁለተኛውን ወፍ በህጉ መሰረት የሚቃጠል መስዋዕት አድርጎ ያቀርበዋል፣ እናም ካህኑ ሰውየው ለሰራው ኃጢአት ማስተስረያ ያደርገዋል፤ ይቅር ይባላል፡፡
11“ነገር ግን ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት እርግቦች መግዛት ሳይችል ቢቀር፣ ለሰራው ኃጢአት የኢፍ መስፈሪያ አንድ አስረኛ መልካም ዱቄት መስዋዕት ያቅርብ፡፡ ያኃጢአት መስዋዕት ስለሆነ ዘይት ወይም ዕጣን አይጨምርበት፡፡
12መስዋዕቱን ወደ ካህኑ ያቅርበው፣ካህኑም ለያህዌ በጎነት ምስጋና ለማቅረብ ከዱቄቱ እፍኝ ይወስዳል፣ ከዚያም በመሰዊያው ላይ ለያህዌ በመስዋዕቱ ላይ በእሳት ያቃጥለዋል፡፡ ይህ የኃጢአት መስዋዕት ነው፡፡
13ካህኑ ሰውየው የሰራውን ማንኛውንም ኃጢአት ያስተሰርይለታል፤ይቅር ይባላል፡፡ ከመስዋዕት የተረፈው እንደ እህል ቁርባኑ ሁሉ የካህኑ ይሆናል፡፡’”
14ከዚያም ያህዌ እንዲህ ሲል ሙሴን ተናገረው፣
15“ማንም ሰው የያህዌን ትዕዛዝ በመጣስ እርሱ ካለው ውጭ ሆኖ ኃጢአት ቢሰራ፣ ነገር ግን ይህንን ሁን ብሎ ባያደርግ ለያህዌ የበደል መስዋዕት ያቅርብ፡፡ ይህ መስዋዕት ከመንጋው ውስጥ ነውር የሌለበት ዋጋውም ለኃጢአት መስዋዕት በቤተ መቅድስ ገንዘብ በጥሬ ብር መገመት አለበት፡፡
16ቅዱስ ከሆነው በማጉደል ለሰራው በደል ዕዳውን በመክፈል ያህዌን ደስ ማሰኘት አለበት፣ እናም አንድ አምስተኛውን በዚህ ላይ ጨምሮ ለካህኑ ይስጥ፡፡ ከዚያ ካህኑ ከበደል መስዋዕቱ ጠቦት ጋር ያስተሰርይለታል፤ እናም ይቅር ይባላል፡፡
17ማንም ሰው ኃጢአት ቢሰራና ያህዌ እንዳይደረግ ያዘዘውን ማናቸውንም ነገር ቢያደርግ፣ ምንም እንኳን ነገሩን ሳያውቅ ቢያደርገውም በደለኛ ነው፤ ስለዚህም በበደሉ ጥፋተኛ ነው፡፡
18ከመንጋው ውስጥ ነውር የሌለበት ጠቦት ያቅርብ ለካህኑ ለበደል መስዋዕት ተመጣጣኝ ዋጋ ያምጣ፡፡ ከዚያም ካህኑ ሳያውቅ ከሰራው ኃጢአት ያስተሰርይለታል፤ ይቅር ይባላል፡፡
19ይህ የበደል መስዋዕት ነው፣ በያህዌ ፊት በእርግጥ ኃጢአተኛ ነው፡፡”
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።