1ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣
2“ለእስራኤል ህዝብ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ ‘ማንም ሰው ያህዌ እንዳይደረግ ያዘዘውን ማናቸውንም ነገር በማድረግ ኃጢአት መስራት ሳይፈልግ ኃጢአት ቢሰራ፣ ደግሞም የተከለከለ አንዳች ነገር ቢያደርግ፣ እንዲህ ይደረግ፡፡
3ኃጢአት የሰራው ሊቀ ካህኑ ቢሆንና በህዝቡ ላይ በደል የሚያስከትል ኃጢአት ቢሰራ ስለ ሰራው ኃጢአት ለያህዌ ነውር የሌለበት ወይፈን የኃጢአት መስዋእት አድርጎ ያቅርብ፡፡
4ወይፈኑን በያህዌ ፊት ወደ መገናኛው ድንኳን ያምጣ፤ ካህኑ እጆቹን በወይፈኑ ራስ ላይ ይጫንና በያህዌ ፊት ይረደው፡፡
5የተቀባው ካህን ከወይፈኑ ጥቂት ደም ይውድና ወደ መገናኛው ድንኳን ያምጣው፡፡
6ካህኑ ጣቱን ደሙ ውስጥ እየነከረ ሰባት ጊዜ በቅድስተ ቅዱሳኑ መጋረጃ ላይ ከደሙ ጥቂት በያህዌ ፊት ይረጫል፡፡
7ደግሞም ካህኑ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በያህዌ ፊት ከደሙ ጥቂት ወስዶ መልካም መዓዛ ያለውን ዕጣን በመሰዊያው ቀንዶች ይጨምራል፤ የቀረውን ወይፈኑን ደም ሁሉ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ ለሚቃጠል መስዋዕት በመሰዊያው ስር ያፈሰዋል፡፡
8የሆድ ዕቃውን የሸፈነውንና ከሆድ ዕቃው ጋር የተያያዘውን የበደል መስዋዕቱን የሆነውን ወይፈን ስብ ሁሉ አውጥቶ ያቀርባል፡፡
9(ቁጥር 9?)
10ለህብረት መስዋዕት ከሚቀርበው ወይፈን አውጥቶ እንዳቀረበ ሁሉ ይንንም አውጥቶ ያቀርባል፡፡ ከዚያም ካህኑ እነዚህን ክፍሎች ለሚቃጠል መስዋዕት በመሰዊያው ላይ ያቃጥላል፡፡
11የወይፈኑን ቆዳና ማንኛውንም ስጋ ከጭንቅላቱና ከእግሮቹ እንዲሁም ከሆድዕቃው ክፍሎችና ከፈርሱ ጋር፣
12የቀረውን የወይፈኑን ክፍሎች ሁሉ ከእነዚህ ክፍሎች ሁሉ ከመንደር ተሸክሞ አመዱን ወደ ደፉበት ለእኔ ወደሚነጹበት ስፍራ ወስዶ እነዚያን ክፍሎች በእንጨት ላይ ያቃጥላቸው፡፡ እነዚያን የከብቱን ክፍሎች አመዱን በደፉበት ስፍራ ያቃጥለው፡፡
13መላው የእስራኤል ጉባኤ ኃጢአት መስራት ሳይፈልግ ኃጢአት ቢሰራ፣ ጉባኤውም ኃጢአት መስራቱን ባያውቅና ያህዌ እንዳይደረግ ያዘዘውን ማናቸውንም ነገር ፈጽሞ ቢገኝና በደለኛ ቢሆን፣
14ከዚያም፣ የፈጸሙት በደል በታወቀ ጊዜ፣ ጉባኤው ለኃጢአት መስዋዕት ወይፈን ይሰዋና ወደ መገናኛው ድንኳን ፊት ያምጣው፡፡
15የጉባኤው ሽማግሌዎች በያህዌ ፊት በወይፈኑ ላይ እጃቸውን ይጫኑና በያህዌ ፊት ይረዱት፡፡
16የተቀባው ካህን ከወይፈኑ ደም ወደ መገናኛው ድንኳን ያመጣል፣
17ከዚያ ካህኑ ጣቱን በደሙ ውስጥ ነክሮ በመጋረጃው ላይ በያህዌ ፊት ሰባት ጊዜ ይረጨዋል፡፡
18በመገናኛው ድንኳን ውስጥ፣በያህዌ ፊት በመሰዊያው ቀንዶች ውስጥ ከደሙ ጥቂት ይጨምርበታል፤ ደግሞም ለሚቃጠል መስዋዕት በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ በመሰዊያው ታች ደሙን በሙሉ ያፈሳል፡፡
19ስቡን ሁሉ ከእንስሳው ቆርጦ ያወጣና በመሰዊያው ላይ ያቃጥላል፡፡
20ወይፈኑን በዚህ መልክ ለመስዋዕት ያቀርባል፡፡ ለኃጢአት መስዋዕት እንዳቀረበው ወይፈን ሁሉ፣ በዚህኛውም ወይፈን ይህንኑ ያደርጋል፣ እናም ካህኑ ለህዝቡ ማስተስረያ ያደርጋል፣ እናም ጉባኤው ይቅር ይባላል፡፡
21ካህኑ ወይፈኑን ከመንደር ያወጣና የመጀመሪያውን ወይፈን እንዳቃጠለ ይህኛውንም ያቃጥለዋል፡፡ ይህ ለጉባኤው የኃጢአት መስዋዕት ነው፡፡
22የህዝቡ መሪ ኃጢአት ለመስራት ሳያስብ ኃጢአት ቢሰራ፣ አምላኩ ያህዌ እንዳይደረግ ካዘዘው ማናቸውም ነገሮች አንዱን አድርጎ ቢገኝና በደለኛ ቢሆን፣
23ከዚያም የሰራው ኃጢአት ቢታወቀው፣ ነውር የሌለበት ተባዕት ፍየል ለመስዋዕት ያቀርባል፡፡
24እጁን በፍየሉ ራስ ላይ ይጭንና የሚቃጠል መስዋዕት በሚያርዱበት ስፍራ በያህዌ ፊት ይረደው፡፡ ይህ የኃጢአት መስዋዕት ነው፡፡
25ካህኑ ያኃጢአት መስዋዕቱን ደም በጣቱ ይውሰድና ለሚቃጠል መስዋዕት በመሰዊያው ቀንዶች ውስጥ ይጨምረው፣ ደግሞም ደሙን ለሚቃጠል መስዋዕት በመሰዊያው ስር ያፍስሰው፡፡
26ልክ እንደ ሰላም መስዋዕት ሁሉ ስቡን በሙሉ በመሰዊያው ላይ ያቃጥለው፡፡ ካህኑ የህዝቡ መሪ ለሰራው ኃጢአት ማስተስረያ ያድርግለታል፣ መሪውም ይቅር ይባላል፡፡
27ከተራው ህዝብ መሃል አንድ ሰው ኃጢአት ለማድረግ ሳያስብ ኃጢአት ቢሰራ፣ያህዌ እንዳይደረግ ካዘዘው ከእነዚህ ነገሮች መሃል አንዱን ቢፈጽም፣ እናም በደለኛ ሆኖ ቢገኝ፣
28ከዚያም የፈጸመው በደል ቢታወቀው፣ ለበደሉ መስዋዕት ነውር የሌለበት ሴት ፍየል ያቅርብ፡፡
29በኃጢአት መስዋዕቱ ራስ ላይ እጁን ይጭናል ከዚያም በሚቃጠል መስዋዕቱ ስፍራ የኃጢአት መስዋዕቱን ያርዳል፡፡
30ካህኑ በጣቱ ጥቂት ደም ወስዶ ለሚቃጠል መስዋዕት በመሰዊያው ቀንዶች ውስጥ ይጨምረዋል፡፡ የተቀረውን ደም ሁሉ በመሰዊያው ስር ያፈሰዋል፡፡
31መስዋዕቱ በተወሰደበት ሁኔታ ከዚህኛውም ሁሉንም ስብ ይወስዳል፡፡ ካህኑ ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ ለማቅረብ በመሰዊያው ላይ ያቃጥለዋል፣የሰውየውንም ኃጢአት ያስተሰርያል፡፡
32ለኃጢአት መስዋዕቱ የበግ ጠቦት ቢያቀርብ ነውር የሌለባት ሴት ጠቦት ያምጣ፡፡
33በኃጢአት መስዋዕቱ ራስ ላይ እጁን ይጫንና የሚቃጠል መስዋዕት በሚያርድበት ስፍራ ለኃጢአት መስዋዕት ያርዳል፡፡
34ካህኑ ከኃጢአት መስዋዕቱ ጥቂት ደም ይወስድና ለሚቃጠል መስዋዕት በመሰዊያው ቀንዶች ውስጥ ይጨምረዋል፡፡ ከዚያም በመሰዊያው ስር ደሙን ሁሉ ያፈሰዋል፡፡
35ከሰላም መስዋዕቱ የጠቦቱ ስብ በወጣበት ሁኔታ፣ከዚህኛውም ሁሉንም ስብ ይወስዳል፣ከዚያ ካህኑ በያህዌ መስዋዕቶች ላይ በእሳት በሚቀርበው መሰዊያ ላይ ያቃጥለዋል፡፡ ካህኑ መስዋእት አቅራቢው የሰራውን ኃጢአት ያስተሰርይለታል፣ እናም ሰውየው ይቅር ይባላል፡፡