መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘሌዋውያን 3

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ማንኛውም ሰው ከመንጋው መሃል ወንድም ሆነ ሴት እንስሳ የህብረት መስዋዕት እንስሳ ቢያቀርብ፣በያህዌ ፊት ነውር የሌለበት እንስሳ ያቅርብ፡፡
2እጁን በመስዋዕቱ እንስሳ ራስ ላይ ይጭናል፣ ከዚያም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ያርደዋል፡፡ ከዚያ ካህናቱ የአሮን ልጆች በመሰዊያው ዙሪያ ደሙን ይረጩታል፡፡
3የህብረት መስዋዕቱን ለያህዌ በዕሳት ያቀርባል፡፡ ሆድቃውን የሸፈነውን ወይም ከዚያ ጋር የተያያዘውን ስብ፣
4እና ሁለቱን ኩላሊቶች እንዲሁም በጎድኑ አጠገብ የሚገኘውን ስብ፣ እና የጉበቱን መረብ ከኩላሊቶቹ ጋር እነዚህን ሁሉ አውጥቶ ያቀርባል፡፡
5የአሮን ልጆች ከሚቃጠለው መስዋዕት ጋር እነዚህን በዕሳቱ ላይ በሚገኘው እንጨት በመሰዊያው ላይ ያቃጥሉታል፡፡ ይህም ለያህዌ ጣፋጭ ማዕዛ ይሆናል፣ ይህ በእሳት ለያህዌ የሚቀርብ መስዋዕት ይሆናል፡፡
6ለያህዌ የሚያቀርበው የህብረት መስዋዕት ወንድም ይሁን ሴት እንስሳ ነውር የሌለበት ይሁን፡፡
7መስዋዕቱ የበግ ጠቦት ከሆነ፣ በያህዌ ፊት ያቅርበው፡፡
8እጁን በመስዋዕቱ ራስ ላይ ይጫንና በመገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት ይረደው፡፡ ከዚያ አሮን ልጆች በመሰዊያው ጎንና ጎኖች ደሙን ይረጩታል፡፡
9የህብረት መስዋዕቱን በእሳት እንደሚቀርብ መስዋዕት አድርጎ ለያህዌ ያቀርባል፡፡ ስቡን፣ላቱን እስከ ጀርባ አጥንቱ ድረስ፣እንዲሁም የሆድ እቃውን የሸፈነውን ስብ ሁሉ፣በሆድ እቃው ዙሪያ የሚገኘውን ስብ ሁሉ፣
10እና ሁለቱን ኩላሊቶችና ከእነዚህ ጋር ያለውን ስብ፣ በጎድኑ አጠገብ የሚገኘውን እና የጉበቱን መሸፈኛ ከኩላሊቶቹ ጋር እነዚህን ሁሉ አውጥቶ ያቀርባል፡፡
11ከዚያም ካህኑ ሁሉንም ለያህዌ በመሰዊያው ላይ በእሳት የመበል ቁርባን አድርጎ ያቃጥላል፡፡
12የሚያቀርበው መስዋዕት ፍየል ከሆነ፣በያህዌ ፊት ያቅርበው፡፡
13እጁን በፍየሉ ራስ ላይ መጫንና በመገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት ማረድ ይኖርበታል፡፡ ከዚያ አሮን ልጆች በመሰዊያው ጎንና ጎኖች ደሙን ይረጩታል፡፡
14በእሳት የተዘጋጀውን መስዋእቱን ለያህዌ ያቀርባል፡፡ የሆድ እቃውን የሸፈነውንና በሆድ እቃው ዙሪያ የሚገኘውን ስብ ሁሉ አውጥቶ ያቀርባል፡፡
15እንዲሁም ሁለቱን ኩላሊቶችና ከእነዚህ ጋር የሚገኘውን ስብ፣ በጎድኖች እና ከኩላሊቶቹ ጋር በጉበቱን መሸፈኛው ላይ የሚገኘውን ስብ እነዚህን ሁሉ አውጥቶ ያቀርባል፡፡
16ካህኑ እነዚህን ሁሉ በመሰዊያው ላይ መልካም መዓዛ እንዲሆን እንደ መብል መስዋዕት አድርጎ ሁሉንም ያቃጥለዋል፡፡ ስቡ ሁሉ የያህዌ ነው፡፡
17“‘ይህ ለእናንተ ከትውልድ እስከ ትውልድ በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ቀዋሚ መታሰቢያ ነው፣ እናንተ ስብ ወይም ደም አትብሉ፡፡’”
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።