መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘሌዋውያን 2

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ማንኛውም ሰው ለያህዌ የእህል ቁርባን ሲያቀርብ፣ መባው መልካም ዱቄት ይሁን፣ ዘይት ያፈስበታል ደግሞም ዕጣን ያድርግበት፡፡
2ቁርባኑን ወደ ካህናቱ ወደ አሮን ልጆች ይወስደዋል፣ ካህኑ ከዘይቱና በላዩ ካለው ዕጣን ጋር ከመልካሙ ዱቄት እፍኝ ይወስዳል፡፡ ከዚየም ካህኑ የያህዌን በጎነት ለማሰብ መስዋዕቱን በመሰዊያው ላይ ያቃጥለዋል፡፡ ይህም ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ ነው፣ ለእርሱ በዕሳት የቀረበ መስዋዕት ይሆናል፡፡
3ከእህል መስዋዕቱ የተረፈው ሁሉ ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናል፡፡ ይህ ሙሉ ለሙሉ ለያህዌ በዕሳት ከተዘጋጀው መስዋዕት ለእርሱ የተለየ ነው፡፡
4በምድጃ የተጋገረ እርሾ የሌለበት የእህል ቁርባን ስታቀርብ፣ በዘይት የተለወሰ ከመልካም ዱቄት የተዘጋጀ ለስላሳ ዳቦ መሆን አለበት፣ ወይም እርሾ የሌለበት በዘይት የተቀባ ቂጣ መሆን አለበት፡፡
5የእህል ቁርባንህ በመጥበሻ ላይ የተጋገረ ከሆነ፣ እርሾ ያልገባበት በዘይት የተለወሰ ከመልካም ዱቄት የተዘጋጀ ይሁን፡፡
6ቆራርሰህ በላዩ ዘይት ጨምርበት፡፡ ይህ የእህል ቁርባን ነው፡፡
7የእህል ቁርባንህ በመጥበሻ የሚዘጋጅ ከሆነ ከመለካም ዱቄትና ዘይት ይዘጋጅ፡፡
8ከእነዚህ ነገሮች የተዘጋጀውን የእህል ቁርባን ወደ ያህዌ ማቅረብ አለብህ፣ እናም ይህ ወደ መሰዊያው ወደሚያመጣው ወደ ካህኑ ይቅረብ፡፡
9ከዚያም የያህዌን በጎነት ለማሰብ ካህኑ ከእህል ቁርባኑ ጥቂት ይወስዳል፣ ቀጥሎም በመሰዊያው ላይ ያቃጥለዋል፡፡ ይህ በዕሳት የተዘጋጀ መስዋዕት ይሆናል፣ እናም ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ ይሆናል፡፡
10ከእህል ቁርባኑ የሚተርፈው ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናል፡፡ ይህ ለያህዌ በዕሳት ከሚዘጋጀው ቁርባን ሙሉ ለሙሉ ለእርሱ የተለየ ነው፡፡
11ለያህዌ በምታቀርቡት የእህል ቁርባን ውስጥ እርሾ አይግባበት፣ ለያህዌ በዕሳት በምታዘጋጁት ቁርባን ውስጥ ምንም እርሾ፣ ወይም ማር አታቃጥሉ፡፡
12እነዚህን እንደ በኩራት ፍሬዎች ለያህዌ ታቀርባላችሁ፣ ነገር ግን በመሰዊያው ላይ መልካም መዓዛ ለመስጠት አታቀርቧቸውም፡፡
13የእህል ቁርባንህን ሁሉ በጨው አጣፍጠው፡፡ ከእህል ቁርባንህ በፍጽም የአምላክህ የቃል ኪዳን ጨው አይታጣ፡፡ በመስዋዕቶችህ ሁሉ ጨው ማቅረብ አለብህ፡፡
14ለያህዌ ከፍሬህ በኩራት የእህል ቁርባን ስታቀርብ ከእሸቱ በእሳት የተጠበሰውንና የተፈተገውን አቅርብ፡፡
15ከዚያ በላዩ ላይ ዘይትና እጣን ጨምርበት፡፡ ይህ የእህል ቁርባን ነው፡፡
16ከዚያ ካህኑ የተፈተገውን እህል እና ዘይት እንዲሁም ዕጣን የያህዌን በጎነት በአንክሮ ለማሰብ ከፊሉን ያቃጥለዋል፡፡ ይህም ለያህዌ የሚቀርብ የዕሳት መስዋዕት ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።