1ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
2“ለእስራኤል ህዝብ እንዲህ በላቸው፣ ‹ለያህዌ የተለዩ የተቀደሱ ባዕሎቻችሁ፣ እንደ ቅዱስ ጉባኤዎቻችሁ የምታውጇቸው፣ የእኔ መደበኛ በዓላት ናቸው፡፡
3ስድስት ቀናት ትሰራላችሁ፣ ሰባተኛው ቀን ግን ሙሉ እረፍት የሚደረግበት ሰንበት ነው፣ የተቀደሰ ጉባኤ ዕለት ነው በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ለያህዌ ሰንበት ስለሆነ ምንም ስራ አትስሩበት፡፡
4እነዚህ ለያህዌ የተመረጡ በዓላት ብላችሁ በተወሰነላቸው ጊዜ የምታውጇቸው የተቀደሱ ስብሰባዎች ናቸው፡፡
5በመጀመሪያው ወር በወሩ በአስራ አራተኛው ቀን ጸሀይ ስትጠልቅ የያህዌ ፋሲካ ነው፡፡
6በዚያው ወር በአስራ አምስተኛው ቀን የያህዌ የቂጣ በዓል ነው፡፡ ለሰባት ቀናት እርሾ ያልገባበት ቂጣ ትበላላችሁ፡፡
7በመጀመሪያው ቀን ለያህዌ የተለየ ጉባኤ ይኖራችኋል፣ የተለመደ ተግባራችሁን አትሰሩበትም፡፡
8ለሰባት ቀናት በእሳት የሚቀርብ መስዋዕት ለያህዌ ታቀርባላችሁ ሰባተኛው ቀን የተለመደ ተግባራችሁን የማታከናውኑበት ለያህዌ የተለየ ጉባኤ የሚደረግበት ነው›”
9ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
10”ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ ብለህ ንገራቸው ‹ወደምሰጣችሁ ምድር ስትገቡ፣ እና የመጀመሪያውን አዝመራ ስትሰበስቡ፣ ከበኩራቱ ፍሬዎች ለካህኑ አንድ ነዶ ታመጣላችሁ፡፡
11ነዶው ተቀባይነትን እንዲያገኝ ካህኑ በያህዌ ፊት ይወዘውዘውና ለእርሱ ያቀርበዋል፡፡ ካህኑ ነዶውን የሚወዘውዘውና ለእኔ የሚያቀርበው በሰንበት ቀን ማግስት ነው፡፡
12ነዶውን በምትወዘውዙበትና ለእኔ በምታቀርቡበት ቀን ለያህዌ ነውር የሌለበት የአንድ አመት ወንድ ጠቦት የሚቃጠል መስዋዕት ታቀርባላችሁ፡፡
13የእህል ቁርባን ለያህዌ መልካም መዓዛ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የኢፍ ሁለት አስረኛ መልካም ዱቄት፣ በእሳት የተዘጋጀ መስዋዕት፣ እና ከነዚህም ጋር የኢን አንድ አራተኛ ወይን የመጠጥ ቁርባን መቅረብ አለበት፡፡
14ለአምላካችሁ ይህን መስዋዕት እስከምታቀርቡበት ቀን ድረስ ምንም ዓይነት ዳቦ፣ አሊያም የተጠበሰ እሸት ወይም ለምለሙን እሸት አትብሉ፡፡ ይህ ለትወልዳችሁ ሁሉ በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ቋሚ መታሰቢያ ይሆናል፡፡
15ከዚያ ሰንበት ቀን ማግስት አንስቶ ነዶውን ለመወዝወዝና ለያህዌ ለማቅረብ ካመጣችሁት ቀን ጀምራችሁ ሰባት ሙሉ ሳምንታት፣ ሰባት ሰንበት ትቆጥራላችሁ፣
16እስከ ሰባተኛው ሰንበት ማግስት ድረስ ትቆጥራላሁ፡፡ ያም ማለት ሀምሳ ቀናት ትቆጥራላችሁ፡፡ ከዚያ ለያህዌ የአዲስ አዝመራ መስዋዕት ታቀርባላችሁ፡፡
17ከየቤቶቻችሁ ከኢፍ ሁለት አስረኛ የተጋገሩ ሁለት ዳቦዎች ታመጣላችሁ፡፡ ከመልካም ዱቄት የሚዘጋጅና በእርሾ የተጋገሩ ይሁኑ፤ ከበኩራት ፍሬዎች የሚቀርቡ የሚወዘወዙና ለያህዌ የሚቀርቡ መስዋዕቶች ይሆናሉ፡፡
18ከዳቦው ጋር ነውር የሌለባቸው የአንድ ዓመት እድሜ ያላቸው ሰባት ጠቦቶች፣ አንድ ወይፈን በሬ፣ እና ሁለት አውራ በጎች ታቀርባላችሁ፡፡ እነርሱም ለያህዌ የሚቃጠል መስዋዕት ይሆናሉ፣ ከእህል ቁርባን ከመጠጥ ቁርባን ጋር፣ በእሳት የተዘጋጀ መስዋዕት እና ለያህዌ መልካም መዓዛ ያለው መስዋዕት ይሆናሉ፡፡
19ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ታቀርባላሁ፣ እንዲሁም ለህብረት መስዋዕት የአንድ አመት ዕድሜ ያላቸው ሁለት ወንድ ጠቦቶች ለመስዋዕት ታቀርባላችሁ፡፡
20ካህኑ ከበኩራት ፍሬዎች ዳቦ ጋር በያህዌ ፊት ይወዘወዛቸው፣ እነርሱንም መስዋዕት አድርጎ ለእርሱ ከሁለት ጠቦቶች ጋር ያቅርብ፡፡ ለያህዌ ቅዱስ መስዋዕቶች ሲሆኑ የካህኑ ድርሻ ናቸው፡፡
21በዚያው ቀን ማወጅ አለባችሁ፡፡ የተቀደሰ ጉባኤ ይኖራል፣ እናም የተለመደ ስራችሁን አትሰሩም፡፤ ይህ የህዝባችሁ በትውልዶች ሁሉ በምትኖሩበት ሥፍራ ሁሉ ቋሚ መታሰቢያ ይሆናል፡፡
22የምድራችሁን ፍሬ ስትሰበስቡ፣ የእርሻችሁን ጥግጋት ሁሉ ሙሉ ለሙሉ አትሰብስቡ፣ የሰብላችን ቃርሚያ ሁሉ አትሰብስቡ፡፡ እነዚህን ለድሆችና ለመጻተኛው ተዉላቸው፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡”
23ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
24”ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‹በሰባተኛው ወር፣ የወሩ የመጀመሪያው ቀን ለእናንተ ታላቅ እረፍት ይሆናል፣ በመለኮት ድምጽ መታሰቢያ የሚደረግበት፣ እና የተቀደሰ ጉባኤ ይሆናል፡፡
25የተለመደ ሥራ አትሰሩበትም፣ ለያህዌ የእሳት መስዋዕት አቅርቡበት፡፡›”
26ከዚያ ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
27“አሁን የዚህ የሰባተኛው ወር አስረኛ ቀን የስርየት ቀን ይሆናል፡፡ ለያህዌ የተለየ ጉባኤ መሆን አለበት፣ ራሳችሁን ማዋረድና ለያህዌ በእሳት መስዋዕት መሰዋት አለባችሁ፡፡
28በዚያን ቀን ምንም ሥራ አትስሩ ምክንያቱም በአምላካችሁ በያዌ ፊት ለራሳች ማስታሰርያ የምታቀርቡበት የስርየት ቀን ነው፡፡
29በዚያን ቀን ራሱን የማያዋርድ ማንም ቢሆን ከህዝቡ ተለይቶ ይጥፋ፡፡
30በዚያን ቀን ማናቸውንም ሥራ የሚሰራውን ማንንም ቢሆን፣ እኔ ያህዌ ከህዝቡ መሀል አጠፋዋለሁ፡፡
31በዚያ ቀን ማናቸውንም ዐይነት ሥራ አትሰሩም፡፡ ይህ በህዝባችሁና ትውልዶቻችሁ ሁሉ በምትኖሩባቸው ስፍራዎች ሁሉ ቋሚ መታሰቢያ ይሆናል፡፡
32ይህ ቀን ለእናንተ የከበረ የሰንበት ዕረፍት ይሁንላችሁ፣ እናንተም በወሩ በዘጠነኛው ቀን ራሳችን አዋርዱ፡፡ ከምሽት እስከ ምሽት ሰንበትን ጠብቁ፡፡”
33ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
34“ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‹በሰባተኛው ወር አስራ አምስተኛው ቀን ለያህዌ የዳስ በዓል ይሆናል፡፡ ይህም ሰባት ቀናት ይወስዳል፡፡
35በመጀመሪያው ቀን ቅዱስ ጉባኤ ይኖራል፡፡ የተለመደውን ሥራ አትስሩበት፡፡
36ለሰባት ቀናት ለያህዌ የሚቃጠል መስዋዕት አቅርቡበት፡፡ በስምንተኛው ቀን ቅዱስ ጉባኤ ይሁን፣ እናንተም ለያህዌ የሚቃጠል መስዋዕት አቅርቡ፡፡ ይህ ክቡር ጉባኤ ነው፣ እናም አንዳች የተለመደ ሥራ አትስሩበት፡፡
37እነዚህ ለያህዌ የተለዩ በአላት ናቸው፣ ለያህዌ የሚቃጠል መስዋዕት ለማቅረብ ቅዱስ ጉባኤ የምታውጁበት፣ የሚቃጠል መስዋዕትና የእህል ቁርባን፣ የመስዋዕቶችና የመጠጥ ቁርባች እያንዳንዱን በየራሱ ቀን ለይታችሁ ለእግዚአብሔር የምታውጁባቸው በዓላት ናቸው፡፡
38እነዚህ በአላት ከያህዌ ሰንበታትና ከእናንተ ስጦታዎች ተጨማሪ ናቸው፣ ስጦቻችሁ ሁሉ፣ እና ለያህዌ የምትሰጧቸው የበጎ ፈቃድ መስዋዕቶቻችሁ ሁሉ ናቸው፡፡
39የዳስ በዓልን በሚመለከት፣ በሰባተኛው ወር በአስራ አምስተኛው ቀን፣ እናንተ የምድሪቱን ፍሬዎች ስትሰበስቡ ይህን የያህዌ በዓል ለሰባት ቀናት ማክበር አለባችሁ፡፡ የመጀመሪያው ቀን የፍፁም ዕረፍት ቀን ይሆናል፣ ስምንተኛው ቀንም እንደዚሁ የፍጹም ዕረፍት ቀን ይሆናል፡፡
40በመጀመሪያው ቀን ከዛፎቹ መልካሞቹን ፍሬዎች ውሰዱ፣ የዘንባባ ዛፎች ዝንጣፊዎች፣ እና የለምለሙ ዛፎች ቅርንጫፎች፣ ከወንዝ ዳርቻ ለምለም ዛፎች ቅርንጫፎች ወስዳችሁ በአምላካችሁ በያህዌ ፊት ለሰባት ቀናት ሃሴት ታደርጋላችሁ፡፡
41በየአመቱ ለሰባት ቀናት፣ ይህን በዓል ለያህዌ ታከብራላችሁ፡፡ ይህ በትውልዳችሁ ሁሉ በምትኖሩባቸው ስፍራዎች ሁሉ ቋሚ መታሰቢያ ይሆናል፡፡ ይህን በዓል በሰባተኛው ወር አክብሩ፡፡
42ለሰባት ቀናት በትንንሽ ዳሶች ውስጥ ትኖራላችሁ፡፡ እስራኤላዊ የሆነ ሁሉ ለሰባት ቀናት በትንንሽ ዳሶች ውስጥ ይቀመጥ፣
43ከእናንተ በኋላ የሚመጣው ትውልድ፣ የልጅ ልጆቻችሁ፣ እስራኤላውያንን ከግብጽ ምድር ሳወጣ በእንደዚህ ዐይነት ዳሶች ውስጥ እንዴት እንዲኖሩ እንዳደረግኩ ያውቃሉ፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡›”
44በዚህ መንገድ፣ ሙሴ ለእስራኤል ህዝብ ለያህዌ የተለዩትን በዓላት አስታወቁ፡፡