መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘሌዋውያን 24

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
2“የእስራኤል ሰዎች መቅረዞች ሁልጊዜም እንዲነዱና ብርሃን እንዲሰጡ ከወይራ ፍሬ የተጠመቀ ንጹኅ ዘይት ለመቅረዞችህ ወደ አንተ እንዲያመጡ እዘዛቸው፡፡
3አሮን ያለማቋረጥ ከምሽት እስከ ማለዳ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከመጋረጃው ውጭ በቃልኪዳኔ ድንጋጌ ፊት መቅረዙን በያህዌ ፊት ያለማቋረጥ ያብራ፡፡ ይህ በትወልዳች ሁሉ ቋሚ ስርዓት ይሆናል፡፡
4ሊቀ ካህኑ በንጹኅ ወርቅ በተሰራው የመቅረዝ መያዣ ላይ መቅረዞቹ ሁልጊዜም በያህዌ ፊት እንዲበሩ ያደርጋል፡፡
5መልካም ዱቄት ወስደህ አስራ ሁለት ዳቦዎች ጋግር፡፡ ለእያንዳንዱ ዳቦ የኢፍ ሁለት እስረኛ መጠን ተጠቀም፡፡
6ከዚያ በሁለት ረድፍ ደርድራቸው፣ በአንዱ መስመር ስድስቱን በንጹኅ ወርቅ በተሰራ ጠረጴዛ ላይ በያህዌ ፊት ደርድር፡፡
7በእያንዳንዱ የዳቦዎቹ ረድፍ እንደ ዳቦዎቹ ምልክት ንጹኅ ዕጣን አድርግበት፡፡ ይህ ዕጣን ለያህዌ በእሳት የሚቀርብ መስዋእት ይሆናል፡፡
8በእያንዳንዱ የሰንበት ዕለት ሊቀ ካህኑ የእስራኤልን ህዝብ ወክሎ የዘላለም ቃልኪዳን ምልክት አድርጎ ህብስቱን በመደበኛነት ለያህዌ ያቀርባል፡፡
9ይህ መስዋዕት የአሮንና የልጆቹ ድርሻ ይሆናል፡፡ ሙሉ ለሙሉ ለእርሱ የተለየና ለያህዌ በእሳት ከሚቀርበው መስዋዕት የተወሰደ ስለሆነ ቅዱስ በሆነው ስፍራ ይብሉት፡፡”
10እናቱ እስራኤላዊ የሆነች እና አባቱ ግብፃዊ የሆነ ልጅ በእስራኤል ህዝብ መሀል ወጣ፡፡ ይህ እስራኤላዊት ሴት ልጅ በሰፈር ውስጥ ከእስራኤላዊ ሰው ጋር ተጣላ፡፡
11የእስራኤላዊቷ ሴት ልጅ የያህዌን ስም ሰደበ እግዚአበሔርንም ረገመ፣ ስለዚህም ህዝቡ ወደ ሙሴ አመጡት፡፡ የእናቱ ስም ሰሎሚት ነበር፣ የደብራይ ልጅ ስትሆን ከዳን ወገን ነበረች፡፡
12ያህዌ ራሱ ፈቃዱን እስኪገልጽላቸው ድረስ በጥበቃ ስር አቆዩት፡፡
13ከዚያ ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣
14“እግዚአብሔርን የተሳደበውን ሰው ከሰፈር አውጡት የሰሙት ሁሉ እጆቻቸውን በላዩ ይጫኑ፣ ከዚያም መላው ጉባኤ በድንጋይ ይውገረው፡፡
15ለእስራኤል ሰዎች ብለህ ግለጽላቸው፣ ‹አምላኩን የተሳደበ ማንኛውም ሰው በደሉን ይሸከም፡፡
16ተወላጅ የሆነ እስራኤላዊም ቢሆን ወይም መጻተኛ የያህዌን ስም በስድብ ያቃለለ መላው ጉባኤ በድንጋይ ይውገሩትና ይገደል፡፡ ማንም ሰው የያህዌን ስም ቢሳደብ፣ ይገደል፡፡
17ሌላ ሰው የገደለ ይገደል፡፡
18የሌላውን ሰው እንስሳ የገደለ በገደለው ፈንታ ይክፈል፣ ህይወት ስለ ህይወት ነው፡፡
19አንድ ሰው ጎረቤቱን ቢጎዳ፣ እርሱ በጎረቤቱ ላይ ያደረገው ነገር ይደረግበት፡፡
20ስብራት ስለ ስብራት፣ አይን ስለ አይን፣ ጥርስ ስለ ጥርስ፡፡ በአንድ ሰው ላይ ጉዳት እንዳደረሰ፣ በእርሱም ላይ እንደዚያው ይደረግበት፡፡
21ማንም እንስሳ የገደለ ሰው መልሶ ይክፈል ማንም ሰው የገደለ ይገደል፡፡
22ለመጻተኛውም ይሁን ለተወላጅ እስራኤላዊው አንድ አይነት ህግ ይኑራችሁ፣ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝና፡፡”
23ሙሴ ለእስራኤል ሰዎች ይህን ነገራቸው፣ ሰዎቹም ያህዌን የተሳደበውን ሰው ከሰፈር ውጭ አመጡት፡፡ በድንጋይ ወገሩት፡፡ የእስራኤል ሰዎች የያህዌን ትዕዛዝ ሙሴ ባዘዘው መሠረት ፈጸሙ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።