1ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው “ለካህናቱ፣ ለአሮን ልጆች እንዲህ በላቸው፣ ‹ከእናንተ መሃል ማንም በመካከላችሁ በሞተ ሰው አይርከስ፣
2ለቅርብ ዘመድ ካልሆነ በስተቀር ማንም አይርከስ ለእናቱ እና አባቱ፣ ለወንድ ልጁና ለሴት ልጁ፣ ወይም ለወንድሙ
3ወይም በቤቱ ከምትኖር ባል ካላገባች ልጃገረድ እህቱ በስተቀር አይርከስ፡፡ ለእርሷ ግን ራሱን ንጹህ ላያርግ ይችላል፡፡
4ለሌሎች ዘመዶቹ ግን እስኪረክስ ድረስ ራሱን ማርከስ የለበትም፡፡
5ካህናት ራሳቸውን አይላጩ ወይም የጺማቸውን ዳርቻ አይላጩ፣ አሊያም ሰውነታቸውን በስለት አይቁረጡ፡፡
6እነርሱ ለአምላካቸው የተለዩ ይሆኑ፣ የአምላካቸውን ስም አያቃሉ፣ ምክንያቱም ካህናቱ የአምላካቸውን “ምግብ” መስዋዕቱን ለያህዌ በእሳት ያቀርባሉ፡፡ ስለዚህም እነርሱ የተለዩ ይሁኑ፡፡
7ለአምላካቸው የተለዩ ስለሆኑ ማናቸውንም ጋለሞታ እና የረከሰች ሴት እንደዚሁም ከባሏ የተፋታችን ሴት ማግባት የለባቸውም፡፡
8የአምላክህን “ምግብ” የሚያቀርብ ነውና እርሱን መለየት አለብህ፡፡ በፊትህ ቅዱስ መሆን አለበት፣ ምክንያቱም ለራሴ የለየሁህ እኔ፣ ያህዌ ቅዱስ ነኝ፡፡
9ማንኛዋም የማንኛውም ካህን ሴት ልጅ ጋለሞታ ብትሆን አባቷን ታሳፍራለች፡፡ በእሳት ትቃጠል፡፡
10ከወንድሞቹ መሃል ሊቀ ካህን የሆነው፣ የሹመቱ ዘይት በራሱ ላይ የፈሰሰበት፣ ደግሞም የሊቀ ካህኑን ልዩ ልብሶች ለመልበስ የተጾመ ጸጉሩን ይሸፍን ልብሱን አይቅደድ፡፡
11ለአባቱ ወይም ለእናቱም ቢሆን እንኳን የሞተ ሰው በሚገኝበትና ራሱን በሚያረክስበት ማናቸውም ስፍራ አይሂድ፡፡
12ሊቀካህኑ የቤተ መቅደሱን የተቀደሰ ስፍራ ትቶ አይሂድ ወይም የአምላኩን ቅድስና አያቃል፣ ምክንያቱም በአምላኩ የቅባት ዘይት ሊቀ ካህን ሆኖ ተሾሞ ነበርና፡፡እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
13ካህኑ ድንግሊቱን ሚስቱ አድርጎ ያግባት፡፡
14ባሏ የሞተባትን ሴት፣ የተፋታችን ሴት፣ ወይም ጋለሞታን ሴት አያግባ፡፤ እንዲያ ካሉት ሴቶች መሃል አያግባ፡፡ ከራሱ ህዝብ መሃል ድንግሊቱን ብቻ ማግባት ይችላል፡፡
15እነዚህን ህጎች ይጠብቅ፣ በህዝቡ መሃል ልጆቹን እንዳያረክስ ህግጋቱን ይጠብቅ፣ እርሱን ለራሴ የለየሁት እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
16ያህዌ እንደህ ሲል ሙሴን ተናገረው፣
17“አሮንን እንዲህ ብለህ ንገረው፣ ማናቸውም ከወገንህ መሀል በትወልዳቸው ውስጥ አካላዊ ጉድለት ያለበት፣ የአምላኩን ‹ምግብ› ለመሰዋት መቅረብ የለበትም፡፡
18ማናቸውም አካላዊ እንከን ያለበት ሰው ወደ ያህዌ መቅረብ የለበትም፣ እንደ ዐይነ ስውር፣ ሽባ የሆነ ሰው፣ አካሉ የጎደለ ወይም አካሉ የተወላገደ፣
19እጆቹ ወይም እግሮቹ ሽባ የሆነ፣
20መጻጉ ወይም ድንክ ሰው፣ ወይም በዐይኖቹ ላይ እንከን ያለበት ሰው፣ ወይም በሽታ የያዘው፣ ሞጭሟጫ፣ እከክ ያለበት ወይም ጃንደረባ ወደ ያህዌ አይቅረብ፡፡
21ከካህኑ ከአሮን መሃል ምንም አካላዊ ጉድለት ያለበት ሰው ለያህዌ የእሳት መስዋዕቶች ለመሰዋት አይቅረብ፡፡ አካላዊ ጉድለት ያለበት እንዲህ ያለው ሰው የአምላኩን ‹ምግብ ለማቅረብ መቅረብ የለበትም፡፡
22ከቅድስተ ቅዱሳኑም ሆነ ከቅዱሱ የአምላኩ ምግብ ሊበላ ግን ይችል፣
23ሆኖም፣ ወደ መጋረጃው መግባት የለበትም ወይም ወደ መሰዊያው አይቅረብ፣ ምክንያቱም አካላዊ ጉድለት ያለበት፣ ስለዚህም ቅዱሱን ስፍራዬን አያርክስ፣ ለራሴ የለየኋቸው እኔ ያህዌ ነኝ፡፡”
24ሙሴ እነዚህን ቃላት ለአሮን፣ ለልጆቹ፣ እና ለእስራኤል ሰዎች ሁሉ ተናገረ፡፡