መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (Door43 ULB 7.2, 2020)

ኦሪት ዘሌዋውያን 20

መጽሐፍ ቅዱስን በአማርኛ ያንብቡ። የDivine Threads ጥናት በቅርቡ ይቀርባል።

1ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
2“ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‹ከእስራኤል ሰዎች መሃል ማንም ሰው፣ ወይም ማንኛውም በእስራኤል የሚኖር መጻተኛ ከልጆቹ መሃል አንዱን ለሞሎክ ቢሰጥ በዕርግጥ ይገደል፡፡ በምድሪቱ የሚኖሩ ሰዎች በድንጋይ ይውገሩት፡፡
3እኔም በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አዞርበታለሁ፣ ከህዝቡም መሃል እቆርጠዋለሁ ምክንያቱም የተቀደሰውን ስፍራዬን ለማርከስና ቅዱሱን ስሜን ለማቃለል ልጁን ለሞሎክ ሰጥቷል፡፡
4ያ ሰው ከልጆቹ አንዱን ለሞሎክ ሲሰጥ ዚያች ምድር ሰዎች እንዳላዩ ቢሆን፣ ባይገድሉት፣
5እኔ ራሴ በዚያ ሰውና በቤቱ ላይ ፊቴን አዞራለሁ፣ እኔ ቆርጬ እጥለዋለሁ እንደዚሁም ከሞሎክ ጋር በሚያመነዝረው በማንኛውም ላይ ይህን አደርጋለሁ፡፡
6ወደ ሙታን ጠሪዎች ዘወር የሚል፣ ወይም ከመናፍስት ጋር ከሚነጋገሩ ጋር የሚመነዝርን ሰው ፊቴን አዞርበታለሁ፤ ከህዝቡም መሃል አጠፋዋለሁ፡፡
7ስለዚህ ራሳችሁን ለያህዌ ስጡ ተቀደሱም፣ ምክንያቱም እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡
8ትዕዛዛቴን ጠብቁ አድርጓቸውም፡፡ ለራሴ የመረጥኳችሁ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
9ወይም እናቱን የሚረግም ሁሉ ይገደል፡፡ አባቱን ወይም እናቱን ረግሟልና በደለኛ ነው ሞት ይገባዋል፡፡
10ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ዝሙት የፈጸመ ሰው፣ ከጎረቤቱ ሚስት፣ ጋር ያመነዘረ ይገደል አመንዝራውና አመንዝራይቱም ሁለቱም ይገደሉ፡፡
11ከአባቱ ሚስት ጋር ሊተኛት የወደቀ የገባ አባቱን ያዋርዳል፡፡ ልጅየውም የአባቱ ሚስትም ሁለቱም ይገደሉ፡፡ በደለኞች ናቸው ሞት ይገባቸዋል፡፡
12አንድ ሰው ከልጁ ሚስት ጋር ቢተኛ፣ ሁለቱም ሊገደሉ ይገባል ያልገባ ፍትወት ፈጽመዋል በደለኞች ናቸው ሞት ይገባቸዋል፡፡
13አንድ ወንድ ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከሌላ ወንድ ጋር ቢተኛ፣ ሁለቱም ጸያፍ ነገር አድርገዋል፡፡ በእርግጥ ሞት ይገባቸዋል፡፡ ይገደሉ፡፡ በደለኞች ናቸው ሞት ይገባቸዋል፡፡
14አንድ ሰው አንዲትን ሴትና እናቲቱንም ቢያገባ፣ ይህ አሳፋሪ ነው፡፡ እርሱና ሴቲቱ ሁለቱም በእሳት ይቃጠሉ፣ ይህ ሲደረግ በመሀላችሁ ክፋት አይኖርም፡፡
15አንድ ሰው ከእንስሳ ጋር ቢተኛ፣ በእርግጥ ይገደል፣ እንስሳይቱንም ግደሏት፡፡
16አንዲት ሴት ለመገናኘት ወደ ማንኛውም አይነት እንስሳ ብተቀርብ ሴትየዋንም እንስሳውንም ግደሏቸው፡፡ በእርግጥ ሊገደሉ ይገባል፡፡ በደለኞች ናቸው ሞት ይገባቸዋል፡፡
17አንድ ሰው የአባቱ ልጅ ከሆነችውም ሆነ የእናቱ ልጅ ከሆነች እህቱ ጋር ቢተገኛ እህትም ከእርሱ ጋር ብትተኛ ይህ አሳፋሪ ነገር ነው፡፡ ከህዝባቸው መሃል ተለይተው ይውጡ፤ ምክንያቱም ከእህቱ ጋር ተኝቷል፡፡ በደሉን ይሸከማል፡፡
18አንድ ሰው አንዲትን ሴት በወር አበባዋ ወቅት አብሯት ቢተኛና ቢገናኛት፣ የደሟ ምንጭ የሆነውን የደም መፍሰሷን ገልጧል፡፡ ወንዱም ሴቷም ሁለቱም ከህዝባቸው መሃል ተለይተው ይውጡ፡፡
19ከእናትህ ወይም ከአባትህ እህት ጋር አትተኛ፣ ምከንያቱም የቅርብ ቤተ ዘመድህን ታዋርዳለህ፡፡ በደልህን ልትሸከም ይገባሃል፡፡
20አንድ ሰው ከአጎቱ ሚስት ጋር ቢተኛ አጎቱን አዋርዷል፡፡ በደላቸውን ሊሸከሙ ይገባል ያለ ልጅ ይቀራሉ፡፡
21አንድ ሰው የወንድሙን ሚስት ቢያገባ ይህ እርኩስ ነው ምክንያቱም ዘመዱ ሆኖ ሳለ የወንድሙን ትዳር አፍርሷል፣ ልጅ አልባ ይሆናሉ፡፡
22ስለዚህም ስርአቶቼንና ህግጋቶቼን ሁሉ መጠበቅ አለባችሁ፤ እንድትኖርባት ያመጣኋቸው ምድር እንዳትተፋችሁ ህግጋቴንና ሥርዓቶቼን ጠብቁ፡፡
23ከፊታችሁ በማባርራቸው ህዝቦች ልምዶች አትመላለሱ፣ እነርሱ እነዚህን ነገሮች ሁሉ አድርገዋል፣ እኔም እነርሱን ጠላሁ፡፡
24እኔ እንዲህ እላችኋለሁ፣ “ምድራቸውን ትወርሳላችሁ፣ ምድሪቱን እንድትወርሷት ለእናንተ እሰጣችኋለሁ፣ ወተትና ማር የምታፈስ ምድር ናት፡፡ ከሌላው ህዝብ የለየኋችሁ፣ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ”
25ስለዚህ እናንተ ንጹህ በሆኑና ንጹኅ በሆኑ እንስሳት መሃል፣ ንጹኅ በሆኑና ንጹህ ባልሆኑ ወፎች መሃል ልዩነት አድርጉ፡፡ ለእናንተ ርኩስ ናቸው ብዬ በለየኋቸው ንጹኅ ባልሆኑ እንስሳት ወይም ወፎች ወይም በማንኛውም በምድር ላይ በሚሳብ ፍጥረት ራሳችሁን አታርክሱ፡፡
26እኔ ያህዌ ቅዱስ እንደሆንኩ፣ ደግሞም ለእኔ ትሆኑ ዘንድ ከሌሎች ህዝቦች እንደለየኋችሁ ቅዱሳን ሁኑ፡፡
27ከሙታን ጋር የሚነጋገር አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት ወይም ከመናፍስት ጋር የሚነጋገር በእርግጥ ይገደል፡፡ ህዝቡ በድንጋይ ወግፎ ይግደላቸው በደለኞች ናቸውና ሞት ይገባቸዋል፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ — Amharic Unlocked Literal Bible (am_ulb), version 7.2 (2020) — Door43 World Missions Community contributors. Original work available at door43.org. Source: pinned 2020 USFM source. License: Creative Commons Attribution-ShareAlike 4.0 (CC BY-SA 4.0). Changes to presentation: USFM verse-only rendering, layout and line-break flattening, omission of Scripture footnotes, editorial text and source-empty verse markers; original combined verse ranges are preserved. This Scripture presentation is offered under CC BY-SA 4.0, separately from independently authored Divine Threads study content. No endorsement by Door43 is implied. የDivine Threads ጥናቶች በአማርኛ በቅርቡ ይቀርባሉ።